የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር አመራርና ስነ-ስርዓት ኮሚቴ ሰኔ 17 2016 ዓ.ም ባደረገው ስብሰባ የተደረጉ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ግጥሚያ(ዎች)ከዳኞች እና ከታዛቢዎች የቀረቡለትን የዲሲፕሊን ሪፖርት ከመረመረ በኋላ ውሳኔዎችን አሳልፏል።
በሳምንቱ መርሃ ግብር በተደረጉ ጨዋታዎች አምስት በመሸናነፍ ቀሪ ሶስቱ በአቻ ውጤት ሲጠናቀቁ 26 ጎሎች በ23 ተጫዋቾች ተቆጥረዋል። 31 ቢጫ ካርድ ለተጫዋቾችና ቡድን አመራሮች ሲሰጥ አንድ ቀይ ካርድ ተመዝግቧል።
በሳምንቱ በአስራ አንድ ተጫዋቾች ላይ የዲሲፕሊን ውሳኔ ተላልፏል። ኬን ሳይዲ(ሻሸመኔ ከተማ)፣ የዓብስራ ሙሉጌታ(ሻሸመኔ ከተማ)፣ ማይክል ኔልሰን(ሻሸመኔ ከተማ)፣ ፍሬው ሰለሞን(ባህርዳር ከተማ)፣ ዮሴፍ ታረቀኝ(አዳማ ከተማ)፣ አብዱልከሪም መሐመድ(ኢትዮጵያ መድን) እና ከነአን ማርክነህ(መቻል) በአምስት ጨዋታዎች የቢጫ ማስጠንቀቂያ ካርድ በመመልከታቸው ለፈፀሙት ጥፋት በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ መሰረት 1 ጨዋታ እንዲታገዱና በተጨማሪ የገንዘብ ቅጣት ብር 1500 /አንድ ሺ አምስት መቶ/ እንዲከፍሉ ፥ ወጋየሁ ቡርቃ(ሻሸመኔ ከተማ) እና ብርሀኑ በቀለ(ሲዳማ ቡና) በ10 ጨዋታዎች የቢጫ ማስጠንቅቂያ ካርድ በመመልከታቸው በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ መሰረት 2 ጨዋታ እንዲታገዱና በተጨማሪ የገንዘብ ቅጣት ብር 2000 /ሁለት ሺህ/ እንዲከፍሉ፥ ሲሞን ፒተር(ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ) የተጋጣሚን ተጫዋች በመማታት በቀይ ካርድ ከጨዋታ ሜዳ የተወገደ ለፈፀመው ጥፋት በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ መሰረት 4 ጨዋታ እንዲታገድ ና በተጨማሪ የገንዘብ ቅጣት ብር 3000 /ሶስት ሺ/እንዲከፍል እንዲሁም ሚሊዮን ሰለሞን(ኢትዮጵያ መድን ተጫዋች) የ28ኛ ሳምንት እግር ኳስ ጨዋታ የተጋጣሚ ቡድን ተጫዋች ላይ ምራቁን ስለመትፋቱ ሪፖርት ቀርቦበት ለፈፀመው ጥፋት በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ ክፍል መሰረት 6/ስድስት/ ጨዋታ እንዲታገድና ብር 3000/ሶስት ሺ/ እንዲከፍል ተወስኗል።
ሻሸመኔ ከተማ ከፋሲል ከነማ ጋር ባደረገው ጨዋታ የሻሸመኔ ከተማ ቡድን ተጫዋች የሆኑት ማይክል ኔልሰን ፣ ኬን ሳይዲ ፣ የዓብስራ ሙሉጌታ ፣ ወጋየሁ ቡርቃ ፣ ሁዛፍ አሊ እና እዮብ ገ/ማርያም በተለያዩ ጥፋቶች ካርድ የተሰጣቸው በመሆኑ በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ መሰረት የገንዘብ ቅጣት ብር 5000 /አምስት ሺ/ እንዲከፍል ተወስኗል፡፡ አቶ ጥጋቡ ትኩበት(የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ስፖርት ክለብ ሰራተኛ) ሲዳማ ቡና ከ መቻል ግጥሚያቸውን በሚያከናውኑበት ወቅት የእለቱ የጨዋታ ታዛቢን ስራቸውን እንዳይሰሩ በተደጋጋሚ በመጮህ ስለመረበሻቸው እና በጥበቃ ሀይል ከቦታው እንዲነሱ ስለመደረጋቸው ሪፖርት የቀርበባቸው ግለሰቡ በፈጸሙት ጥፋት በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የውድድር ደንብ መሰረት የ29ኛና 30ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ውድድር ግጥሚያዎችን ስታድየም ገብተው እንዳይመለከቱ እንዲታገዱ ተወስኗል።
- ማሰታውቂያ -
የፕሮግራም ለውጥ
በ29ኛ የውድድር ሳምንት ከሚደረጉት ግጥሚያዎች መካከል
1. ሻሸመኔ ከተማ ከ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እሁድ ሰኔ 23 2016 በ 9:00 ሰዓት በሀዋሳ ዩኒቨርስቲ ስታድየም
2. ሀምበሪቾ ከ ወልቂጤ ከተማ እሁድ ሰኔ 23 2016 በ 9:00 ሰዓት በሀዋሳ አርተፊሻል ሜዳ
3.አዳማ ከተማ ከ መቻል እሁድ ሰኔ 23 2016 በ 12:00 ሰዓት በሀዋሳ ዩኒቨርስቲ ስታድየም
እንዲደረጉ የውድድርና ስነስርዓት ኮሚቴ ወስኗል።