የዲሲፕሊን ውሳኔዎች በወልቂጤ ከተማ
- ወልቂጤ ከተማ ከ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጋር በነበረው የ2ኛ ሳምንት የእግርኳስ ጨዋታ ወደሜዳ ቀርቦ ስላለመጫወቱ ሪፖርት ቀርቦበታል ። ስለሆነም
- በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የዲሲፕሊን መመሪያ ክፍል 3 አንቀፅ 69 ተቁ 1(ሀ) መሰረት ወልቂጤ ከተማ በፎርፌ ተሸናፊ እንዲሆን
- ከመቻል ስፖርት ክለብ ጋር ሊያደርገው የነበረውን የIኛ ሳምንት ጨዋታ ጨምሮ ወልቂጤ ከተማ በውድድር አመቱ ወደሜዳ ባለመምጣቱ ፎርፌ የተሰጠበት ጨዋታ ለሁለተኛ ጊዜ በመሆኑ በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የዲሲፕሊን መመሪያ ክፍል 3 አንቀፅ 69 በንዑስ አንቀጽ 3 ተራ ቁጥር 14 መሰረት ከኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የ2017 ውድድር እንዲሰረዝ
- በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የዲሲፕሊን መመሪያ ክፍል 3 አንቀፅ 69 በንዑስ አንቀጽ 3 ተራ ቁጥር 10(ለ) መሰረት የመቻል ክለብ ከወልቂጤ ከተማ ጋር ባደረገው የIኛ ሳምንት ግጥሚያ በፎርፌ የተመዘገበለት ውጤት እንዲሰረዝ
- በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የዲሲፕሊን መመሪያ ክፍል 3 አንቀፅ 69 በንዑስ አንቀጽ 3 ተራ ቁጥር 10(ለ) መሰረት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የወልቂጤ ከተማ በሜዳ ላይ አለመገኘትን ተከትሎ በ2ኛ ሳምንት ሊያገኘው የነበረው የፎርፌ ውጤት እንዳይመዘገብ
የውድድርና ስነስርዓት ኮሚቴ ወስኗል።
ሌሎች የዲሲፕሊን ውሳኔዎች
- ዋንጫ ቱት(ኢትዮጵያ መድን ) የመታወቂያ ቁጥር ረቡዕ መስከረም 15 2017 ዓ.ም. ክለቡ ከአርባምንጭ ከተማ ጋር ባደረገው የ2ኛ ሳምንት እግርኳስ ጨዋታ በ 90+4 ኛ ደቂቃ ላይ ሆን ብሎ የተጋጣሚ ቡድንን ተጫዋች በክርን በመማታት በቀይ ካርድ ከጨዋታ ሜዳ የተወገደ ስለመሆኑ ሪፖርት ቀርቦበታል ። ስለሆነም ተጫዋቹ ለፈፀመው ጥፋት በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ ክፍል 3 ምዕራፍ 3 አንቀፅ 63 በተቁ 1 (ሠ) እና በተቁ 2 መሰረት 4 ጨዋታ እንዲታገድ ና በተጨማሪ የገንዘብ ቅጣት ብር 3000 /ሶስት ሺ/ እንዲከፍል የ ውድድር አመራርና ስነ-ስርዓት ኮሚቴ ወስኗል።
- አማኑኤል ኤረቦ (ቅዱስ ጊዮርጊስ-ተጫዋች ክለቡ ከወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርስቲ ጋር ባደረገው የ2ኛ ሳምንት እግር ኳስ ጨዋታ መለያውን ከፍ በማድረግ ከመለያው ስር በለበሰው ልብስ ላይ የነበረውን ሃይማኖታዊ መልእክት የሚያስተላልፍ ምስል ስለማሳየቱ ሪፖርት ተደርጎበታል። ስለሆነም በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የውድድር ደንብ ክፍል 1 አንቀፅ 9 የተጫዋች መለያ በግጥሚያ ወቅት (ተቁ 4 እና 5) መሰረት ተጫዋቹ የገንዘብ ቅጣት ብር 3000 /ሶስት ሺህ ብር/ እንዲሁም ክለቡ የገንዘብ ቅጣት ብር 10000 /አስር ሺህ ብር/ እንዲከፍሉ የውድድርና ስነስርዓት ኮሚቴ ወስኗል፡፡
- ይገዙ ቦጋለ (ሲዳማ ቡና-ተጫዋች ክለቡ ከመቻል ጋር ባደረገው የ2ኛ ሳምንት እግር ኳስ ጨዋታ መለያውን ከፍ በማድረግ ከመለያው ስር በለበሰው ልብስ ላይ የነበረውን ሃይማኖታዊ መልእክት የሚያስተላልፍ ጽሁፍ ስለማሳየቱ ሪፖርት ተደርጎበታል። ስለሆነም በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የውድድር ደንብ ክፍል 1 አንቀፅ 9 የተጫዋች መለያ በግጥሚያ ወቅት (ተቁ 4 እና 5) መሰረት ተጫዋቹ የገንዘብ ቅጣት ብር 3000 /ሶስት ሺህ ብር/ እንዲሁም ክለቡ የገንዘብ ቅጣት ብር 10000 /አስር ሺህ ብር/ እንዲከፍሉ የውድድርና ስነስርዓት ኮሚቴ ወስኗል፡፡
- ማሰታውቂያ -