በ3ተኛው ሳምንት ሁለተኛ ቀን ውሎ የተገናኙት ፋሲል ከነማ እና ስሑል ሽረ ያለግብ አቻ ተለያዩ። አፄዎቹ ከመቐለ 70 እንደርታ ጋር አቻ ከተለየየው ስብስብ ብሩክ አማኑኤል፣ ቃልኪዳን ዘላለም እና ኤፍሬም ሀይሉ ወጥተው እዮብ ማቲየስ፣ በረከት ግዛው እና አሚር ሙደሲር ሲገቡ: ስሑል ሽረዎች ሀዋሳ ከተማን ከገጠመው ቡድን ምንም ቅየሪ ሳያደርጉ ገብተዋል።
የመጀመርያው አጋማሽ ሁለቱም ቡድኖች የጠራ የግብ እድል ለመፍጠር የተቸገሩበት ነበር። ፋሲል ከነማ የመሃል ሜዳውን ብልጫ ለመውሰድ ተደጋጋሚ አጫጭር ቅብብሎችን ለማድረግ ሲሞክሩ የታዩበት እና የኳስ ቁጥጥር ብልጫም መያዝ የቻሉበት ሁኔታዎች ፈጥረዋል። ሆኖም እነዚህ አጫጭር ቅብብሎች የሜዳው መጨረሻ ክፍል ሲደርሱ የነበራችው መቆራረጥና የውሳኔ አሰጣጥ ችግር ለግብ የቀረቡ ሙከራዎችን እንዳይፈጥሩ ምክንያት ሆኖባቸዋል።
ስሑል ሽረዎችም ከኃላ ለመውጣት ተደጋጋሚ ሙከራዎችን ቢያደርጉም: የፋሲሎችን ጫና መቋቋም ሲየቅታቸውና ተደጋጋሚ ረጃጅም ኳሶችም ከፋሲል ከነማ ተከላካይ ክፍል ኃላ ሲጥሉ ታይተዋል። አብዛኞቹ ቅብብላቸውም በራሳቸው ሜዳ ክፍል መሆኑ እድሎችን መፍጠር እንዳይችሉ አድርጓቸዋል።
ሁለተኛው አጋማሽ በተመሳሳይ መልኩ በግብ ሙከራዎች እጥረት ታጅቦ የተካሄደ ነበር። ፋሲሎች ቃልኪዳን ዘላለም ቀይረው በማስገባት በግራ መስመር በኩል በፍጥነት ጥቃቶችን ለመሰንዘር ጥረት ቢየደርጉም ይህ ሚባል የግብ ዕድል ሊፈጥሩ አልቻሉም። አፍቅሮት ሰለሞን ግራ መስመር ላይ የተገኘውን ቅጣት ምት በቀጥታ ከርቀት ከሞከረው ኳስ ውጪ ይህ ሚባል ሞይስ ፖዎቲን የፈተኑ ሙከራዎችን ማድረግ አልቻሉም።
- ማሰታውቂያ -
ስሑል ሽረዎችም ከመጀመርየው አጋማሽ አንፃር የተሻለ ፍጥነት ጨምረው በመልሶ ማጥቃት የግብ እድሎችን ለመግጠር ሙከራዎችን ቢያደርጉም የተሳኩ አልነበሩም። ፋሲሎች በራሳቸው ሳጥን ላይ በሚቀባበሉበት ጊዜ በፈጠሩት ስህተት የተገኘውን ኳስ እና ጃዕፈር ሙዳሲር በቀጥታ የመታው የስሑሎች በጨዋታው የፈጠሩት የተሻለ የግብ እድል ነበር።
በዚህም መሰረት ጨዋታው ግብ ሳይቆጠርበት በአቻ ውጤት ተጠናቋል። ውጤቱን ተከትሎ ሁለቱም ቡድኖች ነጥባቸውን ወደ 5 ከፍ ማድረግ ችለዋል።