በዕለቱ ሁለተኛ ጨዋታ በሀድያ ሆሳዕና እና በአዲስ አበባ ከተማ መካከል ተደርጎ በተከታታይ ጨዋታዎች ጠንካራ አቋም በማሳየት ላይ የሚገኘው የመዲናዋ ክለብ በሪችሞንድ ኦዶንጎ አስደናቂ ግብ 1 ለ 0 አሸንፈዋል ።
ሀድያ ሆሳዕና በአምስተኛ ሳምንት ከሀዋሳ ከተማ ጋር ባደረጉት ጨዋታ ከተጠቀሙት ቋሚ 11 ሶስት ቅያሪዎችን በማድረግ መላኩ ወልዴን ሳምሶን ጥላሁን እና ሀብታሙ ታደሰን ጨዋታውን እንዲጀምሩ አድርገዋል ። በአዲስ አበባ ከተማ በኩል ግን አዳማ ከተማ የገጠመውን ቋሚ አሰላለፍ ምንም ቅያሪ ሳያደርጉ ወደ ጨዋታው ገብተዋል ።
ጨዋታው ገና ከጅምሩ ፈጣን እንቅስቃሴ የነበረው እና በሁለቱም ክለቦች በኩል ቶሎ ወደ ተጋጣሚ የግብ ክልል በመድረስ ጫና ለመፍጠር የሞከሩበት ነበር ።

የጨዋታው የመጀመሪያ ሙከራ በሁለተኛው ደቂቃ ላይ በሀድያ ሆሳዕናው አምበል የተደረገ ነበር ። በተጠቀሰው ደቂቃ ላይ ተስፋዬ አለባቸው ከሳጥን ውጪ መሬት ለመሬት አክርሮ የመታው ኳስ በግብ ጠባቂው ዳንኤል ተሾመ ለጥቂት ተመልሷል ። ከሶስት ደቂቃዎች በኋላ ኡመድ ኡክሪ በሳጥን ውስጥ ሆኖ ያገኘውን ኳስ ወደ ግብ ሊመታው ሲል በአስረሳኸኝ ጴጥሮስ በተሰራበት ጥፋት ምክንያት ሀድያ ሆሳዕናዎቾ የፍፁም ቅጣት ምት ማግኘት ችለዋል ። የፍፁም ቅጣት ምቱ ራሱ ጥፋት የተሰራበት ኡመድ ቢመታውም በአምስተኛው ሳምንተ አዲስ አበባ ከተማ ከአዳማ ከተማ አቻ በተለያያበት ጨዋታ ድንቅ ብቃቱን ማሳየት የቻለው ግብ ጠባቂው ዳንኤል ተሾመ በቀላሉ ይዞታል ።

ሁለቱም ክለቦች አጥቅተው ለመጫወት ማሰባቸውን በሚያሳብቅ መልኩ በተደጋጋሚ ወደ ግብ ክልሎች ይደርሱ ነበር ። ነገር ግን በሶስተኛው የማጥቃት ክፍል ደርሰው የሚያደርጉት ቅብብል በተጋጣሚ ተከላካዮች እየተመለሱባቸው የግብ ሙከራዎች በቀላሉ ማድረግ አልቻሉም ። በተለይም ከውሀ እረፍት በኋላ በተሻለ ወደ ግብ መድረስ የቻሉት አዲስ አበባ ከተማዎች ጥሩ ጥሩ የግብ ሙከራዎችን ማድረግ ችለዋል ።

42ኛው ደቂቃ ላይ አዲስ አበባ ከተማዎቾ ያገኙትን የቅጣት ምት ፍፁም ጥላሁን መሬቴ ለመሬት ወደ ግብ ሞክሮት የነበረው ቢሆንም ግብ ጠባቂው.. መልሶበታል ። እንዲሁም የመጀመሪያው ኢጋማሽ መጠናቀቂያ ላይ አዲስ አበባ ከተማዎች ከቀኝ መስመር ያገኙትን የቅጣት ምት አስረሳኸኝ ጴጥሮሰ ወደ ግብ አሻምቶት እንዳለ ከበደ ነፃ ሆኖ አግኝቶ በግንባሩ ቢገጨውም ኢላማውን ሳይጠብቅለት ቀርቷል ።

በሁለተኛው አጋማሽ ልክ እንደ መጀመሪያው አጋማሽ ጅማሮ በፈጣን እንቅስቃሴ የተጀመረ ነበር ። በ46ኛው ደቂቃ ላይ ሀብታሙ ታደሰ ከጨረቃዋ አካባቢ የሞከረው ኳስ ለጥቂት ወደ ውጪ ወቶበታል ። ከሶሰት ደቂቃዎች በኋላም ኡመድ ኡክሪ ለግቡ ጀርባውን ሰጥቶ የተቀበለውን ኳስ ዞሮ ቢሞክረውም ምቱ ጠንካራ ስላልነበር ዳንኤት ተሾመ በቀላሉ ይዞታል ። አዲስ አበባ ከተማዎቾ በአጋማሹ የመጀመሪያ ሙከራቸውን ያደረጉት በ… ነበር ። 54ኛው ደቂቃ ላይ ከሳጥን ውጪ ያገኘውን ኳስ ወደ ግብ ሞክሮት በሶሆሆ ሜንሳህ ተይዟል ።

ቀስ በቀስ ከተጋጣሚያቸው በተሻለ ለመንቀሳቀስ የቻሉት አዲስ አበባ ከተማዎች 73ኛ ደቂቃ ላይ መሪ የሆኑበትን ግብ አስቆጠሩ ። ሪችሞንድ ኦዶንጎ ከቀኝ መስመር በአየር ላይ ያሻገረለትን ኳስ ተከላካዮችን አምልጦ በመሄድ ኳሱ አየር ላይ እንዳለ ሁኔታ ግሩም ግብ አስቆጠረ ።

በቀጣዮቹ ደቂቃዎች ሀድያ ሆሳዕናዎች የአቻነቷን ግብ ለማግኘት ጥረቶችን ቢያደርጉም አዲስ አበባ ከተማዎች ያስቆጠሩትን ግብ ይዘው መረባቸውን ሳያስደፍሩ ወተዋል ።
ውጤቱን ተከትሎም አሸናፊው አዲስ አበባ ነጥቡን 10 ያደረሰ ሲሆን ሀድያ ሆሳዕና በበኩሉ ባለበት 3 ነጥብ የሚቆይ ይሆናል ።
አስተያየት ይስጡ