መነሻ ገጽ ሰበታ ከተማ የጨዋታ ዘገባ | የስድስተኛ ሳምንት የመጀመሪያ ጨዋታ ያለምንም ግብ ተጠናቋል
ሰበታ ከተማዜናዎችየጨዋታ ዘገባድሬዳዋ ከተማ

የጨዋታ ዘገባ | የስድስተኛ ሳምንት የመጀመሪያ ጨዋታ ያለምንም ግብ ተጠናቋል

አጋራ
አጋራ

የቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ በዛሬው ዕለት ሲጀመር በቅድሚያ የተገናኙት ሰበታ ከተማ እና ድሬዳዋ ከተማ ጨዋታቸውን 0 ለ 0 በሆነ ውጤት አጠናቀዋል ።

በአምስተኛው ሳምንት ሽንፈት ያጋጠማቸው ሁለቱ ክለቦች በጨዋታዎቹ ከተጠቀሟቸው ቋሚ አስራ አንድ ተጫዋቾች የተወሰኑ ለውጦችን ያደረጉ ሲሆን ። ሰበታ ከተማ ምንተስኖት አሎ ፤ ክሪስቶዝም ንታምቢ ፤ ታፈሰ ሰረካ ጁንየስ ናኝጄቦ እና ዘካሪያስ ፍቅሬን ወደ ቋሚ አሰላለፍ ሲመልሱ በድሬዳዋ ከተማ በኩል ካለፈው ጨዋታ አብዱራህማን ሙባረክን ብቻ ቀይረው በማስገባት ጨዋታውን ጀምረዋል ።

ለኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ጭብጨባ በማድረግ የተጀመረው ጨዋታ ቀዝቀዝ ያለ እንቅስቃሴ ያስመለከት ነበር ።

ሰበታ ከተማ ኳሱን ተቆጣጥረው በመጫወት የመጀመሪያ ደቂቃዎች ላይ ብልጫ ቢያሳዩም ቀስ በቀስ ድሬዳዋ ከተማዎች በተሻለ ለመጫወት የቻሉበት ነበር ።

ይህ ነው ሊባል የሚችል የግብ ሙከራ ባላሰየው አጋማሽ 20ኛ ደቂቃ ላይ አብዱራህማን ሙባረክ ከግራ መስመር የተሻገረለትን ኳስ በሳጥን ውስጥ አረጋግቶ ወደ ግብ የሞከረው ኳስ በአንተነህ ተስፋዬ በእጅ ተመልሶ ወደ ውጪ ቢወጣም የዕለቱ የመሀል ዳኛ በዝምታ አልፈውታል ።

ቀሪዎቹ ደቂቃዎችም ቀዝቀዝ ብለው ቀጥለው የመጀመሪያው አጋማሽ ያለምንም ግብ ሊጠናቀቅ ችሏል ።

በሁለተኛው አጋማሽ ድሬዳዋ ከተማ በተሻለ መልኩ በተለያዩ አጋጣሚዎች አስቆጪ የሆኑ የግብ ሙከራዎችን ያደረጉበት ሲሆን በሰበታ ከተማ በኩል ግን ወደ ግብ በመሄድ ረገድ የረባ እንቅስቃሴን ማድረግ አልቻሉም ።

በአጋማሹ ለግብ የቀረበ የመጀመሪያ ሙከራ የተደረገው በ68ኛው ደቂቃ ላይ ነበር ። በዚህ ደቂቃ ላይ የድሬዳዋ ከተማው መሀመድ አብዱልለጢፍ ከግራ መስመር ወደ ግብ ያሻገረውን ኳስ ተቀይሮ የገባው ሳሙኤል ዘሪሁን ለግቡ ቅርብ ሆኖ ቢያገኘውም ሳይጠቀምበት ቀርቷል ።

ድሬዳዋ ከተማ በተደጋጋሚ በግራ መስመር በመሀመድ አብዱልጢፍ አማካኝነት የማጥቃት ጥረቶችን አድርገዋል ። በዚሁ መስመር 76ኛው ደቂቃ ላይ መሀመድ ያሻገረውን ኳስ ማማዱ ሲዲቤ ለግቡ በቅርበት ሆኖ መቶት ለአለም የመለሰበት ሳሆን የተመለሰውን ኳስ ተከላካዩ እንየው ካሳሁን ደርሶ በድጋሚ ወደ ግብ ቢሞክረውም በድጋሚ በግብ ጠባቂው ተመልሶበታል ።

ከአንድ ደቂቃ በኋላ በሰበታ ከተማ በኩል ተቀይሮ የገባው ዱሬሳ ሹቢሳ ከግራ መስመር ከርቀት ወደ ግብ የሞከረው ኳስ በግብ ጠባቂው ተይዞበታል ።

ሰበታ ከተማዎች አልፎ አልፎ ኳሱን ይዘው ወደ ፊት ለመሄድ የሚያደርጉት ጥረት ብዙም ሳይጓዝ ይበላሽባቸው ነበር ። የሚገኙ ዕድሎችን መጠቀም ያልቻሉት ድሬዳዋ ከተማዎች 80ኛው ደቂቃ ላይ ማማዱ ሲዲቤ ከአቤል ከበደ የደረሰውን ኳስ ከሳጥኑ በቀኝ በኩል ሆኖ ወደ ግብ የመታው ኳስ በምንተስኖት አሎ ተመልሶ የማዕዘን ምት ሆኗል ።

የጨዋታው የመጨረሻ ደቂቃዎች ሲቃረቡ ሰበታ ከተማዎች በተሻለ ለመንቀሳቀስ ቢሞክሩም በሁለቱም በኩል ግብ ሳይቆጠር ጨዋታው ተጠናቋል ።

ውጤቱን ተከትሎም ሰበታ ከተማ ነጥቡን ወደ 4 ሲያሳድግ ድሬደዋ ከተማ በበኩሉ 8 ነጥብ ላይ ደርሷል ።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየዲሲፕሊን ውሳኔዎችዲሲፕሊን ውሳኔ

የዲሲፕሊን ውሳኔዎች

ገዛኸኝ ደሳለኝ (ሸገር ከተማ) : ክለቡ ከ ኢትዮጵያ ቡና ጋር ባደረገው የ26ኛ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

የሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና በዝናባማው ጨዋታ በመቻል ሲረታ የጣናው ሞገድም አሸንፏል

እጅግ በከባድ ዝናብ ታጅቦ በተደረገው ጨዋታ መቻል የሊጉን መሪ ሲዳማ ቡናን 3ለ1...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሀድያ ሆሳዕና ፣ ፋሲል ከነማ እና ወላይታ ድቻ ወሳኝ ድል አግኝተዋል

በሊጉ የሳምንቱ የሁለተኛ ቀን መርሀግብር ሀዋሳ ከተማ ወደ ሊጉ መሪ የሚጠጋበትን ዕድል...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ፈረሰኞቹ በድል ሲቀጥሉ ንግድ ባንክ እና ድሬዳዋም አሸንፈዋል

ቅዱስ ጊዮርጊስ ተከታታይ ድሉን ወደ ቋቱ ሲከት ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከጨዋታ ብልጫ...