በዛሬው መርሀ ግብር በቅድሚያ የድሬዳዋ ከተማ ምክትል ስራ አስኪያጅ እና የማርኬቲንግ ዳይሬክተር አቶ ፍፁም ክንደሼ ከስፖርት ስፖንሰርሺፕ ጋር በተያያዘ ከትላንት የቀጠለ ገለፃ እና ልምዳቸውን በማካፈል ተጀምሯል ። በመቀጠልም ስለ ስፖርት ክለብ ብራንዲንግ እና ማርኬቲንግ ስትራቴጂ በተመሳሳይ ገለፃ አድርገዋል ።
ከገለፃው እና ልምድ ማካፈሉ በኋላ የአዲስ አበባ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ምክትል ስራ አስኪያጅ አት ደረጄ አረጋ ፤ የጎፈሬ ትጥቅ አምራች ስራ አስኪያጅ አቶ ሳሙኤል እና የቀድሞው የብሄራዊ ቡድን ተጫዋች እንዲሁም በተለያዩ ሀገራት ክለቦች መጫወት የቻለው ፍቅሩ ተፈራ መድረኩን ተቀላቅለው ከተሳታፊዎች የተነሱ የተለያዩ ጥያቄዎችን በመቀበል መልስ ሰተዋል ።
- ማሰታውቂያ -
የጎፈሬ የስፖርት ትጥቅ አምርች መስራች እና ስራ አስኪያጅ አቶ ሳሙኤል ስለ ድርጅታቸው አጀማመር እንዴት እዚህ ደረጃ ሊደርስ እንደቻለ እየሰራ ያላቸውን ስራዎች እንዲሁም በቀጣይ ለመስራት ስላቀዳቸው ተግባራት ለተሳታፊዎች ማብራሪያ ሰጥተዋል ።
አቶ ፍቃዱ አረጋ ከአዲስ አበባ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ጋር ተያይዘው ለተነሱ ጥያቄዎች መልስ የሰጡ ሲሆን ከፌዴሬሽኑ ጋር አብረው እየሰሩ ላሉት ፍቅሩ ተፈራ እና ለጎፈሬ ትጥቅ አምራች ምስጋናቸውን አቅርበዋል ። ፍቅሩ ተፈራም ያለውን ልምድ በተለያዩ ሀገራት በተጫወተበት ጊዜ የተመለከተውን ነገር ለመድረኩ ማቅረብ ችሏል ።
በፕሮግራሙ ላይ ለመከላከያ ሰራዊት ድጋፍ ለማድረግ ቃል የመግባት ስነስርአት ከተደረገ በኋላ ለተሳታፊዎች የምስክር ወረቀት በመስጥት ለሁለት ቀናት የተዘጋጀው የግንዛቤ ማስጨበጫና የልምድ ልውውጥ ተጠናቋል ።