መነሻ ገጽ ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የጨዋታ ዘገባ | በሊጉ መሪዎች መካከል የተደረገው ጨዋታ ግብ ሳያስተናግድ ተጠናቋል
ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግወላይታ ድቻዜናዎችየጨዋታ ዘገባፋሲል ከነማ

የጨዋታ ዘገባ | በሊጉ መሪዎች መካከል የተደረገው ጨዋታ ግብ ሳያስተናግድ ተጠናቋል

አጋራ
አጋራ

የስድስተኛ ሳምንት ሁለተኛ ቀን ውሎ የመጀመሪያ ጨዋታ ሊጉን በ13 ነጥብ እየመራ የነበረውን ወላይታ ድቻ ከተከታዩ ፋሲል ከተማ አገናኝቶ በሁለቱም በኩል ምንም ግብ ሳያስተናግድ 0 ለ 0 ተጠናቋል ።

የጦና ንቦቹ ሰበታ ከተማ ባሸነፉበት ጨዋታ የተጠቀሙትን ቋሙ አሰላለፍ ምንም ሳይቀይሩ የገቡ ሲሆን አፄዎቹ በበኩላቸው ከአርባ ምንጭ ከተማ አቻ በተለያዩበት ጨዋታ በቋሚነት ከተጠቀሟቸው ተጫዋቾች አስቻለው ታመነን እና ኦኪኪ አፎላቢን በመቀየር ወደ ጨዋታው ገብተዋል ።

ጨዋታው ለሀገር መከላከያ ሰራዊት ክብር በመስጠት የተጀመረ ሲሆን ፋሲል ከተማዎች የኳስ ቁጥጥር ብልጫ በመውሰድ እና በተለይም ከመስመር በሚነሱ ኳሶች የግብ ዕድሎችን ለመፍጠር የጣሩ ሲሆን ወላይታ ድቻዎች ደግሞ በተፈጠረባቸው የኳስ ቁጥጥር ብልጫ ወደ በሜዳቸው በዛ ብለው የነበረ ሲሆን አልፎ አልፎ የሚነጥቋቸወን ኳሶች በረጅም ወደ ተጋጣሚ የግብ ክልል ለመድረስ ሙከራዎቸን አድርገዋል ።

ምንም እንኳን ኳሶች በተደጋጋሚ ወደ ግብ ክልል አካባቢ ቢደረሱም የግብ ሙከራዎችን ግን መመልከት አልቻልንም ። በአጋማሹ መጠናቀቂያ ላይ በዛብህ መለዮ በሳጥን ውስጥ ሆኖ ከኦኪኪ የተቀበለውን ኳስ ወደ ግብ ሞክሮት ኢላማውን ሳይጠብቅ ወደ ውጪ ወቶበታል ።

በሁለተኛው አጋማሽ አፄዎቹ ሙሉ ለሙሉ የጨዋታ ብልጫ በመውሰድ እና በተጋጣሚያቸው ሜዳ ላይ ተገኝተው ጫና በመፍጠር ግብ ለማግኘት የሞከሩበት ሲሆን የጦና ንቦቹ ውጤቱን አስጠብቀው ለመውጣት በሚመስል መልኩ አፈግፍገው የተጫወቱ ሲሆን ከደቂቃዎች በኋላ በማጥቃት መስመር ላይ የነበሩ ተጫዋቾች የተቀየሩበት መንገድ ይህን ሀሳብ የሚያጠናክር ነበር ። የፋሲል ከተማዎ ማጥቃት በአብዛኛው በግራ መስመር በተለይም በአምሳሉ ጥላሁን አማካኝነት የተደረገ ነበር ።

በጨዋታው 54ኛ ደቂቃ ላይ አምሳሉ ጥላሁን ከኦኪኪ አፎላቢ የደረሰውን ኳስ አክርሮ ቢመታውም ከግቡ አናት በላይ ወቶበታል ። በ65ኛው ደቂቃ ላይም ሽመክት ጉግሳ ወደ ሳጥን ይዞት የገባውን ኳስ ለበረከት ደስታ አቀብሎት የነበረ ቢሆንም በረከት ኳሱን ጠንከር አድርጎ ባለመምታቱ ፅዮን መርዕድ በቀላሉ ይዞበታል ። አፄዎቹ ከክንፍ በአየር ላይ ኦኪኪን ኢላማ ያደረጉ ኳሶችን በተደጋጋሚ ቢያሻግሩም ኦኪኪ አፎላቢ ሊጠቀምባቸው አልቻለም ። በ77ኛ ደቂቃ ላይም ናትናኤል ገብረጊዮርጊስ ከማዕዘን ምት የተነሳውን ኳስ አግኝቶ ወደ ግብ ክልል አሻሞቶት ተቀይሮ የገባው ሳሙኤል ተስፋዬ ጋር ደርሶ ወደ ግብ ቢሞከርም በግብ ጠባቂዝ ፅዮን መርዕድ ተመልሶ ወደ ውጪ ወጥቷል ።

ከስድስት ያህል ደቂቃዎች በኋላ ከማዕዘን ተነስቶ የተመለሰውን ኳስ በዛብህ መለዮ ከሳጥን ውጪ መቶ ቢሞክረውም ግቦ ጠባቂው ይዞበታል ። ጨዋታውም ምንም ግብ ሳያስተናግድ ፍፃሜውን አገኘ ።

ውጤቱን ተከትሎም ወላይታ ድቻ በ13 ነጥብ መሪነቱን ሲያጠናክር ፋሲል ከተማ ነጥቡን ወደ 11 አሳድጓል ።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

የሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና በዝናባማው ጨዋታ በመቻል ሲረታ የጣናው ሞገድም አሸንፏል

እጅግ በከባድ ዝናብ ታጅቦ በተደረገው ጨዋታ መቻል የሊጉን መሪ ሲዳማ ቡናን 3ለ1...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሀድያ ሆሳዕና ፣ ፋሲል ከነማ እና ወላይታ ድቻ ወሳኝ ድል አግኝተዋል

በሊጉ የሳምንቱ የሁለተኛ ቀን መርሀግብር ሀዋሳ ከተማ ወደ ሊጉ መሪ የሚጠጋበትን ዕድል...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ፈረሰኞቹ በድል ሲቀጥሉ ንግድ ባንክ እና ድሬዳዋም አሸንፈዋል

ቅዱስ ጊዮርጊስ ተከታታይ ድሉን ወደ ቋቱ ሲከት ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከጨዋታ ብልጫ...

ዋልያዎቹዜናዎችየኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን

አንጋፋው አሰልጣኝ በስማቸው የእግር ኳስ ማሰልጠኛ አካዳሚ ሊገነባላቸው ነው

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የቀድሞ አሰልጣኝ ኢንስትራክተር ሰውነት ቢሻውን ለማመስገን እና ዕውቅና ለመስጠት...