By using this site, you agree to the Privacy Policy and Terms of Use.
Accept
ሀትሪክ ስፖርት ኢትዮጵያሀትሪክ ስፖርት ኢትዮጵያ
  • መነሻ ገፅ
  • ዜናዎች
  • ፕሪሚየር ሊግ
    • ባህርዳር ከተማ
    • ወላይታ ዲቻ
    • ድሬዳዋ ከተማ
    • ፋሲል ከነማ
    • ሲዳማ ቡና
    • አዳማ ከተማ
    • ሀዋሳ ከተማ
    • ቅዱስ ጊዮርጊስ
    • ኢትዮጵያ ቡና
    • ጅማ አባጅፋር
    • ወልቂጤ ከተማ
    • ሰበታ ከተማ
    • ሀዲያ ሆሳዕና
  • ዋልያዎቹ
  • ውድድሮች
  • English Article
  • French Articles
  • ስለ እኛ
Reading: ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለዋንጫዉ የተቃረበበትን ድል ሲያስመዘግብ ፤ ቅዱስ ጊዮርጊስም ከ7 ጨዋታዎች በኋላ ወደ አሸናፊነት ተመልሷል !!
Share
Notification Show More
Latest News
ወላይታ ድቻ የሊጉን መሪ አሸንፏል
ዜናዎች ቅዱስ ጊዮርጊስ ኢትዮ-ኤሌክትሪክ ሲዳማ ቡና የጨዋታ ዘገባ መቻል የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ኢትዮጵያ ቡና ወልዋሎ
ኢትዮጵያ ቡና የፋይናስ ችግር እንገጠመው ተገለፀ
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ኢትዮጵያ ቡና ዜናዎች
“ኢትዮዽያ ቡናን ብትነኩ ከመቃብሬ ተነስቼ አጠፉቹሀለው” መቶ አለቃ ፍቃደ ማሞ
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ኢትዮጵያ ቡና ዜናዎች
ኢንተርናሽናል አርቢትር ማኑኤ ወ/ጻዲቅ ከአዳማ ተሰናበተ
የኢትዮጵያ እግርኳስ ዳኞች ማህበር የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ዜናዎች
በረከት አማረ ወደ ቀደመ ክለቡ ሊመለስ ይችላል ?
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የዝውውር ዜናዎች ኢትዮጵያ ቡና ዜናዎች
Aa
ሀትሪክ ስፖርት ኢትዮጵያሀትሪክ ስፖርት ኢትዮጵያ
Aa
  • መነሻ ገፅ
  • ዜናዎች
  • ፕሪሚየር ሊግ
  • ዋልያዎቹ
  • ውድድሮች
  • English Article
  • French Articles
  • ስለ እኛ
  • መነሻ ገፅ
  • ዜናዎች
  • ፕሪሚየር ሊግ
    • ባህርዳር ከተማ
    • ወላይታ ዲቻ
    • ድሬዳዋ ከተማ
    • ፋሲል ከነማ
    • ሲዳማ ቡና
    • አዳማ ከተማ
    • ሀዋሳ ከተማ
    • ቅዱስ ጊዮርጊስ
    • ኢትዮጵያ ቡና
    • ጅማ አባጅፋር
    • ወልቂጤ ከተማ
    • ሰበታ ከተማ
    • ሀዲያ ሆሳዕና
  • ዋልያዎቹ
  • ውድድሮች
  • English Article
  • French Articles
  • ስለ እኛ
Have an existing account? Sign In
Follow US
  • Advertise
© 2023 Hatrick Spoert. Design by Tech-ethiopia.com All Rights Reserved.
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግዜናዎችቅዱስ ጊዮርጊስኢትዮጵያ ንግድ ባንክሲዳማ ቡናየጨዋታ ዘገባፋሲል ከነማ

ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለዋንጫዉ የተቃረበበትን ድል ሲያስመዘግብ ፤ ቅዱስ ጊዮርጊስም ከ7 ጨዋታዎች በኋላ ወደ አሸናፊነት ተመልሷል !!

Ermias Misganaw
Ermias Misganaw 2 years ago
Share
SHARE

በሀያ ስድስተኛዉ ሳምንት ሶስተኛ ዕለት ቀዳሚ ጨዋታ ኢትዮጵያ ንግድ ባንኮች ፋሲል ከነማን በማሸነፍ የሊጉን መሪነታቸዉን አጠናክረዋል።

በዋና ዳኛ ሔኖክ አበበ ፊሽካ ቀን ዘጠኝ ሰዓት ሲል በጀመረዉ ጨዋታ ሁለቱም ክለቦች ቶሎ ቶሎ ወደ ግብ ከመድረስ እና ሙከራዎችን ከማድረግ ይልቅ በአብዛኛዉ ጥንቃቄ በተሞላበት እና በመሐል ሜዳ ላይ በተወሰነ እንቅስቃሴ ጨዋታቸውን ጀምረዋል።

ከተጠበቀዉ በተቃራኒዉ እምብዛም ሙከራዎች ባልተደረጉበት የጨዋታዉ የመጀመሪያ አጋማሽ በ16ተኛዉ ደቂቃ ላይ ሙከራ ተመልክተንበታል ፤ በዚህም ከግራ መስመር በኩል ኤፍሬም ታምራት ያሻገረዉን ኳስ ያገኘዉ ኪቲካ ጀማ ኳሷን በጭንቅላቱ ወደ ግብ ሞክሮ የነበረ ቢሆንም ነገር ግን ኳሷ ኢላማዋን ሳትጠብቅ ወጥታለች።

በ40ኛዉ ደቂቃ ላይ በተመሳሳይ ከግራ መስመር በኩል ኤፍሬም ታምራት ያሻማዉን ኳስ ባሲሩ ዑመር ሲጨርፈዉ ከኋላ ይገኝ የነበረዉ ፉዓድ ፈረጃ ኳሷን አግኝቶ በቀጥታ ወደ ግብ ሞክሮ የነበረ ቢሆንም ነገር ግን ኳሷ ለጥቂት በግቡ የቀኝ ቋሚ በኩል ወጥታለች። እምብዛም ሙከራ ባላስመለከተን የመጀመሪያው አጋማሽ ሁለቱም ክለቦች ጥንቃቄ በተሞላበት መንገድ ጨዋታቸዉን ሲከዉኑ ቆይተዉ አንድ ኢላማዉን የጠበቀ ሙከራ ብቻ አስመልክተዉን ለዕረፍት ወደ መልበሻ ክፍል አምርተዋል።

- ማሰታውቂያ -

ከዕረፍት መልስ ሁለቱም ክለቦች ቅያሪዎችን በማድረግ የጨዋታዉን ቴምፖ ለመቆጣጠር ጥረት ማድረግ ቢቀጥሉም ነገር ግን በተቃራኒው በሙከራ ረገድ እንደ መጀመሪያዉ አጋማሽ ሁሉ ቀዝቃዛ አጋማሽ አሳልፈዋል። በዚህ ሂደት የቀጠለዉ ጨዋታም በመሐል ሜዳ ከሚታየዉ ፍትጊያ በዘለለ ያን ያህል ተጠቃሽ ሙከራ ሳያስመለክተን ቀጥሎ በ82ተኛዉ ደቂቃ ላይ ግን ግብ ተቆጥሮበታል። በዚህም በዚሁ ደቂቃ ላይ ጋቶች ፓኖም ሱለይማን ላይ ጥፋት መስራቱን ተከትሎ በሁለተኛ ቢጫ በቀይ ካርድ ከሜዳ ሲወጣ ይህንኑ የቅጣት ምት ኳስም ፉዓድ ፈረጃ አሻምቶት ተቀይሮ የገባዉ አዲስ ግደይ ወደ ግብነት በመቀየር መርሐግብሩ በባንክ 1ለ0 አሸናፊነት እንዲጠናቀቅ አስችሏል።

በዕለቱ ሁለተኛ ጨዋታ ቅዱስ ጊዮርጊስ ሲዳማ ቡናን ማሸነፍ ችሏል ።

በኢንተርናሽናል ዋና ዳኛ አሸብር ሰቦቃ መሪነት አመሻሽ 12:00 ሰዓት ሲል በበርካታ ደጋፊዎች ታጅቦ በጀመረዉ ጨዋታ ሁለቱም ክለቦች የመሐል ሜዳዉን ፍትጊያ ተቆጣጥረዉ አደጋዎቸን ለመፍጠር ገና በጊዜ ጥረት ማድረግ የጀመሩ ሲሆን በ15ተኛዉ ደቂቃ ላይም ሲዳማዎች ቀዳሚ ሙከራ ማድረግ ችለዋል። በዚህም አጥቂዉ ማይክል ከአማኑኤል ተርፉ የቀማዉን ኳስ በቀጥታ ወደ ግብ ሞክሮ ግብ ጠባቂዉ ባህሩ ነጋሽ ሲመልስ በቅርብ ርቀት ላይ የነበረዉ ይገዙ ቦጋለ ሳይጠቀምባት የቀረችዉ ኳስ በሲዳማዎች በኩል የተደረገች አስቆጭ ሙከራ ነበረች ።

ያን ያህል ሙከራ ባላስመለከተን ጨዋታ በመጀመሪያዎቹ ደቂቃዎች ላይ መጠነኛ ብልጫ የተወሰደባቸዉ ፈረሰኞቹ በግማሽ ሰዓት አንድ ሙከራ ማድረግ ችለዋል። በዚህም ሞሰስ አዶ ለመስመር ተጫዋቹ ተገኑ ተሾመ ያቀበለዉን ኳስ ተጫዋቹ እየገፋ ከግብ ጠባቂዉ መክብብ ጋር ተገናኝቶ የነበረ ቢሆንም ነገር ግን ሳይሳካ ቀርቷል። ያን ያህል በሙከራ ባልታጀበዉ እና ለተመልካችም ሳቢ ባልነበረዉ የጨዋታዉ የመጀመሪያ አጋማሽ አንድም ኢላማዉን የጠበቀ ሙከራ ሳያስመለክተን ክለቦቹ ለዕረፍት ወደ መልበሻ ክፍል አምርተዋል።

በሁለተኛዉ አጋማሽ ሁለቱም ክለቦች የተጫዋቾች ለዉጥ በማድረግ ብልጫ ለመዉሰድ ጥረት ማድረግ የቀጠሉ ቢሆንም ነገር ግን ያን ያህል አዝናኝ ባልሆነ እንቅስቃሴ ጨዋታዉ ቀጥሎ በ77ተኛዉ ደቂቃ ላይ ከብዙ ጥረት በኋላ ፈረሰኞቹ ግብ አግኝተዋል። በዚህም ተቀይሮ የገባዉ አማኑኤል ኤረቦ ከበረከት ወልዴ የተቀበለዉን ኳስ በግሩም ብቃት ወደ ግብነት መቀየር ችሏል። ከግቧ መቆጠር በኋላ በተመሳሳይ መንገድ በቀጠለዉ ጨዋታዉ መርሐግብሩ ሊጠናቀቅ በጣት የሚቆጠሩ ደቂቃዎች በቀሩበት ወቅት ሲዳማ ቡናዎች በብርሀኑ በቀለ አማካኝነት ከቅጣት ምት ድንቅ ሙከራ ቢያደርጉም ነገር ግን የግብ ዘቡ ባህሩ ነጋሽ ኳሷን እንደምንም አውጥቶ ጨዋታዉ በፈረሰኞቹ 1ለ0 አሸናፊነት ተጠናቋል።

You Might Also Like

ወላይታ ድቻ የሊጉን መሪ አሸንፏል

ኢትዮጵያ ቡና የፋይናስ ችግር እንገጠመው ተገለፀ

“ኢትዮዽያ ቡናን ብትነኩ ከመቃብሬ ተነስቼ አጠፉቹሀለው” መቶ አለቃ ፍቃደ ማሞ

ኢንተርናሽናል አርቢትር ማኑኤ ወ/ጻዲቅ ከአዳማ ተሰናበተ

በረከት አማረ ወደ ቀደመ ክለቡ ሊመለስ ይችላል ?

Share this Article
Facebook Twitter Email Print
By Ermias Misganaw
Follow:
Writer at Hatricksport
Previous Article መቻል ከሻሸመኔ ከተማ እንዲሁም ባህርዳር ከተማ ከወላይታ ዲቻ ጨዋታቸውን በአቻ ዉጤት ደምድመዋል !!
Next Article ኢትዮጵያ ቡና ሀምበሪቾ ዱራሜን በሰፊ የግብ ልዩነት ሲያሸንፍ ፤ ሀዋሳ ከተማም ወሳኝ ድል ተቀዳጅቷል !!

Follow US

Find US on Social Medias
127k Like
2.9k Follow
1.6k Follow
19.7k Follow

Weekly Newsletter

Subscribe to our newsletter to get our newest articles instantly!

ተነባቢ ዜናዎች
ሲዳማ ቡናThe BiG Interviewቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግዜናዎች

ሲዳማ ቡና በእኛ ዘመን አይወርድም፤ ማሊያውን ለብሶ እንደተጫወተ ኢት.ቡና ስኬታማ በመሆኑ እደሰታለሁ እንጂ አልከፋም” ፈቱዲን ጀማል (ሲዳማ ቡና)

Yishak belay By Yishak belay 5 years ago
ፋሲል ከነማና ጅማ አባ ቡና ድል ቀንቷቸዋል
የብሄር ስም ያላቸው ክለቦች ስማቸውን ሳይቀይሩ ሊጉ መጀመሩ ፌዴሬሽኑና ሊግ ኩባንያውን አወዛግቧል..
ቅዱስ ጊዮርጊስ 3 የውጪ ተጫዋቾችን የግሉ አድርጓል
አሰልጣኝ ክፍሌ ቦልተና ከክለባቸው ሊለያዩ ነው
- Advertisement -
Ad imageAd image
Global Coronavirus Cases

Confirmed

0

Death

0

More Information:Covid-19 Statistics
about us

Phone: 0993808668 Email: [email protected] .

Find Us on Socials

© Hatrick Sport 2023 All Rights Reserved.

Removed from reading list

Undo
 

Loading Comments...
 

    Welcome Back!

    Sign in to your account

    Lost your password?