By using this site, you agree to the Privacy Policy and Terms of Use.
Accept
ሀትሪክ ስፖርት ኢትዮጵያሀትሪክ ስፖርት ኢትዮጵያ
  • መነሻ ገፅ
  • ዜናዎች
  • ፕሪሚየር ሊግ
    • ባህርዳር ከተማ
    • ወላይታ ዲቻ
    • ድሬዳዋ ከተማ
    • ፋሲል ከነማ
    • ሲዳማ ቡና
    • አዳማ ከተማ
    • ሀዋሳ ከተማ
    • ቅዱስ ጊዮርጊስ
    • ኢትዮጵያ ቡና
    • ጅማ አባጅፋር
    • ወልቂጤ ከተማ
    • ሰበታ ከተማ
    • ሀዲያ ሆሳዕና
  • ዋልያዎቹ
  • ውድድሮች
  • English Article
  • French Articles
  • ስለ እኛ
Reading: “ከመቀሌ ጋር ስንጫወት የፊፋን እና የሊግ አክስዮን ማህበሩን ህግ የሚጋጭ ነው” “ጊፍት ፍሬድ የጡንቻ ጉዳት አጋጥሞታል” ፋሲል ተካልኝ ፦ የቅዱስ ጊዮርጊስ ክለብ ዋና አሰልጣኝ
Share
Notification Show More
Latest News
ኢንተርናሽናል አርቢትር ማኑኤ ወ/ጻዲቅ ከአዳማ ተሰናበተ
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ዜናዎች የኢትዮጵያ እግርኳስ ዳኞች ማህበር
በረከት አማረ ወደ ቀደመ ክለቡ ሊመለስ ይችላል ?
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የዝውውር ዜናዎች ኢትዮጵያ ቡና ዜናዎች
አርባምንጭ ከተማ ሴኔጋላዊ አማካይ አስፈረመ
የዝውውር ዜናዎች ዜናዎች አርባምንጭ ከተማ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ
አርባምንጭ ከተማ ጋናዊ አጥቂ አስፈረመ
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የዝውውር ዜናዎች ዜናዎች አርባምንጭ ከተማ
የ22ኛ ሳምንት የዲሲፕሊን ውሳኔዎች
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ዜናዎች የዲሲፕሊን ውሳኔዎች
Aa
ሀትሪክ ስፖርት ኢትዮጵያሀትሪክ ስፖርት ኢትዮጵያ
Aa
  • መነሻ ገፅ
  • ዜናዎች
  • ፕሪሚየር ሊግ
  • ዋልያዎቹ
  • ውድድሮች
  • English Article
  • French Articles
  • ስለ እኛ
  • መነሻ ገፅ
  • ዜናዎች
  • ፕሪሚየር ሊግ
    • ባህርዳር ከተማ
    • ወላይታ ዲቻ
    • ድሬዳዋ ከተማ
    • ፋሲል ከነማ
    • ሲዳማ ቡና
    • አዳማ ከተማ
    • ሀዋሳ ከተማ
    • ቅዱስ ጊዮርጊስ
    • ኢትዮጵያ ቡና
    • ጅማ አባጅፋር
    • ወልቂጤ ከተማ
    • ሰበታ ከተማ
    • ሀዲያ ሆሳዕና
  • ዋልያዎቹ
  • ውድድሮች
  • English Article
  • French Articles
  • ስለ እኛ
Have an existing account? Sign In
Follow US
  • Advertise
© 2023 Hatrick Spoert. Design by Tech-ethiopia.com All Rights Reserved.
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግዜናዎችቅዱስ ጊዮርጊስ

“ከመቀሌ ጋር ስንጫወት የፊፋን እና የሊግ አክስዮን ማህበሩን ህግ የሚጋጭ ነው” “ጊፍት ፍሬድ የጡንቻ ጉዳት አጋጥሞታል” ፋሲል ተካልኝ ፦ የቅዱስ ጊዮርጊስ ክለብ ዋና አሰልጣኝ

Habtamu Mitku
Habtamu Mitku 1 year ago
Share
SHARE

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ በብሔራዊ ቡድን ጨዋታዎች ምክንያት ከተቋረጠ በኋላ በመጪው ቅዳሜ በአራተኛ ሳምንት ጨዋታዎች ይመለሳል።

በሳምንቱ ከሚደረጉት ጨዋታዎች መካከል ዕሁድ የሚደረገው የቅዱስ ጊዮርጊስ እና ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጨዋታ ተጠባቂ ነው።

ቢሾፍቱ በሚገኘው የይድነቃቸው ተሰማ አካዳሚ ልምምዱን በማድረግ ላይ የሚገኘው የቅዱስ ጊዮርጊስ ክለብ ዋና አሰልጣኝ የሆኑት አሰልጣኝ ፋሲል ተካልኝ ከክለቡ የሬድዮ ፕሮግራም ጋር ስለነበራቸው የዝግጅት ጊዜ እና ተያያዥ ጉዳዮች ሀሳባቸውን ሰጥተዋል።

“የተወሰነ እረፍት ከወሰድን በኋላ አዳዲስ ተጫዋቾች ከቡድኑ ጋር የማዋሀድ እና ባለፉት ጨዋታዎች ላይ የታዩ ደካማ ጎኖች የማሻሻል ፤ በአካልም በአዕምሮ ተጫዋቾች የማዘጋጀት ስራዎች ሰርተናል” ሲሉ አሰልጣኝ ፋሲል ተካልኝ ተናግረዋል።

- ማሰታውቂያ -

አሰልጣኙ የቡድናቸውን አቅም ከፍ ያደርጋሉ ብለው ስለሚያስቧቸው እና ከውጪ ሀገራት ስለፈረሙት ተጫዋቾች መረጃ ሲሰጡም ፤ የኮትዲቯራዊው አጥቂ መሀመድ ኮኔ የወረቀት ስራዎች አለመጠናቀቁን ገልፀዋል።

“አንደኛው አጥቂያችን ኮኔ ዘግይቶ ቢሆንም የገባው ሶስቱም ተጫዋቾች በነበረው የእረፍት ጊዜ ከኛ ጋር ዝግጅታቸውን አድርገዋል።ከቡድኑ ጋር ለማዋሀድ እየሞከርን ነው። ኮኔ ከመኖሪያ ፈቃድ ጋር በተያያዘ አስተዳደራዊ ጉዳዩ አላለቀም። ምናልባት በዚህ ሁለት ቀናት ውስጥ ተጠናቆ ከኛ ጋር ወደ ድሬዳዋ እንደሚያመራ እጠብቃለሁ።”

ቅዱስ ጊዮርጊስ በሊጉ ካደረጋቸው ሶስት ጨዋታዎች ወልዋሎ አዲግራትን ሲያሸንፍ በፋሲል ከነማ እና መቀሌ 70 እንደርታ ሽንፈቶችን አስተናግዷል። አሰልጣኝ ፋሲል የተጫዋቾቻቸው ስነ ልቦና ላይ ክፍተቶች መኖራቸውን በማንሳት ይህንን ለማስተካከልም ጠንካራ ስራዎች በመስራት ላይ እንደሚገኙም ጠቁመዋል።

“ተጫዋቾችን በየጊዜው በአካል ብቃትም በአዕምሮም ለማዘጋጀት እንጥራለን። ወጣቶች ከመሆናቸው ጋር ተያይዞ የሚገጥሙንን ችግሮች በንግግር እና በስራ ለመፍታት እየሞከርን ነው።”

“አንዳንድ ጊዜ በሜዳ ላይ ያሰብነው ነገር ሳይሳካ ሲቀር በቀላሉ የመሰበር የመደንገጥ ነገር በተጫዋቾቻችን ላይ አለ። ይሄ እንግዲህ ከቅዱስ ጊዮርጊስ ታላቅነት እና ካለው ሀላፊነት ጋር ተያይዞ እሱን የመሸከም አቅም ነው።እንግዲህ በሂደት ይቀረፋል ብለን እናስባለን። ከዚህ ውጪ ተጫዋቾቹ ለመስራት ለማሸነፍ የሚጠበቅባቸውን ለማድረግ ያላቸው ጉጉት ከፍተኛ ነው።”

ቡድኑ በሶስተኛው ሳምንት ከመቀሌ 70 እንደርታ ጨዋታ ያደረጉበት ሰዓት ላይ ቅሬታ እንዳላቸው ያነሱት አሰልጣኙ ጉዳዩን አስቀደምውም ለሚመለከተው አካል በማሳወቅ መጠየቃቸውን ገልፀዋል።

“ከመቀሌ ጋር ስንጫወት የፊፋን እና የሊግ አክስዮን ማህበሩን ህግ የሚጋጭ ነው። አንድ ቡድን ከ72 ሰአታት በኋላ ነው መጫወት ያለበት ይላል ህጉ እኛ ደግሞ ስንጫወት 69 ሰዓት ነው።”

ከጨዋታዉ አስቀድሞ ቀርበው መጠየቃቸውን እና ማስረዳታቸውን ያነሱት አሰልጣኝ ፋሲል በነበረው ጠባብ ጊዜ ጨዋታውን ማድረጋቸው ለሽንፈቱ ዋነኛ ምክንያት እሱ ነው ባይባልም ተፅዕኖ ግን አልነበረውም ማለት አይቻልም ብለዋል።

ከመቼውም ጊዜ የበለጠ የክለቡ አባላቶች ደጋፊውን ይፈልጋሉ ያሉት አሰልጣኝ ፋሲል ደጋፊው በቀጣይ ጨዋታዎች ላይ ቡድኑን እንዲያበረታታ ጥሪ አቅርበዋል።

በቀጣይ ሶስት ጨዋታዎች ላይ ከአራት እስከ አምስት ቀናት ልዩነቶች አሉ ስለዚህ እነዚህን ሶስት ጨዋታዎች እየተመላለስን ነው የምንጫወተው።

አርብ ልምምዳችንን ከሰራን በኋላ ቅዳሜ ወደ ድሬዳዋ በማቅናት በጨዋታው ማግስት ሰኞ እንመለሳለንም ብለዋል።

ቅዱስ ጊዮርጊስ በሊጉ አራተኛ ሳምንት መርሐግብር በመጪው ዕሁድ ምሽት 1:00 ጀምሮ በድሬዳዋ ስታድየም ጨዋታውን ያደርጋል።

You Might Also Like

ኢንተርናሽናል አርቢትር ማኑኤ ወ/ጻዲቅ ከአዳማ ተሰናበተ

በረከት አማረ ወደ ቀደመ ክለቡ ሊመለስ ይችላል ?

አርባምንጭ ከተማ ሴኔጋላዊ አማካይ አስፈረመ

አርባምንጭ ከተማ ጋናዊ አጥቂ አስፈረመ

የ22ኛ ሳምንት የዲሲፕሊን ውሳኔዎች

Share this Article
Facebook Twitter Email Print
By Habtamu Mitku
Follow:
Writer at Hatricksport
Previous Article አሰልጣኝ ስዩም ከበደ ይቅርታ ጠየቀ…..
Next Article “አጨዋዋታችን ስህተት ስለነበረ አይደለም የተሸነፍነው” ገብረመድህን ኃይሌ ፦ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ

Follow US

Find US on Social Medias
127k Like
2.9k Follow
1.6k Follow
19.7k Follow

Weekly Newsletter

Subscribe to our newsletter to get our newest articles instantly!

ተነባቢ ዜናዎች
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግዜናዎችቅዱስ ጊዮርጊስቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ

የቅዱስ ጊዮርጊስ ምክትል አሰልጣኝ አዲስ ወርቁ ሀላፊነቱን መልቀቁን አሳዉቋል።

Biruk Hanchacha By Biruk Hanchacha 3 years ago
ፋሲልከተማ 2ተኛ ምክትል አሰልጣኝ አስፈርሟል
የጨዋታ ዘገባ | የሔኖክ አርፊጮ ብቸኛ ግብ ነብሮቹን ባለድል አድርጓል
ሀትሪክ በቀጠሮዋ ቀልድ አታውቅም
ነገም በሰአቷ ይጠብቋት…..
የጥሎ ማለፍ ሩብ ፍፃሜ |ፋሲል ከተማ ከ ወልዲያ ከተማ በቀጥታ /LIVESCORE/
- Advertisement -
Ad imageAd image
Global Coronavirus Cases

Confirmed

0

Death

0

More Information:Covid-19 Statistics
about us

Phone: 0993808668 Email: [email protected] .

Find Us on Socials

© Hatrick Sport 2023 All Rights Reserved.

Removed from reading list

Undo
 

Loading Comments...
 

    Welcome Back!

    Sign in to your account

    Lost your password?