“እንኳን ቡድኔ ውስጥ ከ20 አመት ሊግ ውስጥ ከ20 አመት በታች ተጨዋቾች የሉም”
“ከሀገሪቱ ምርጥ ሶስት አሰልጣኞች መሃል አንዱ እኔ ነኝ ሁለቱን ብትጠሩም አለሁበት ”
“በእድሜ ትልቅነት የሚገመቱና የሚጠረጠሩ ተጨዋቾች በሙሉ ፓስፖርታቸው ያጫውታቸዋል”
- ማሰታውቂያ -
ከ20 አመት በታች ውድድር ሳይሆን የቻን ውድድር በሚመስለው ሻምፒዮና ላይ ለተመዘገበው ደካማ ውጤት ሰፊውን የኢትዮጵያ ህዝብን ይቅርታ እጠይቃለሁ” ሲሉ አሰልጣኝ ስዩም ከበደ ተናገሩ።
በታንዛኒያ ሲካሄድ በነበረው የሴካፋ ከ20 አመት በታች ሻምፒዮና ላይ ደካማ ውጤት ያስመዘገበው ቡድን ዙሪያ ዛሬ መግለጫ የሰጡት አሰልጣኙ” ውድድሩን ካየነው የ20 አመት በታች ሳይሆን የቻን የአፍሪካ ዋንጫ ይመስል ነበር ሁሉም ሀገራት በሚያስብል ደረጃ 20 አመት ተብሎ በትክክለኛ መንገድ የመጡ አይደለም” ሲሉ ቡድናቸውን ተከለክለዋል።
አሰልጣኝ ስዩም “ድክመት ቢኖርም አንገት የሚያስደፋ እንቅስቃቃሴ አላሳየንም
ቦክስ ላይ ተወዳዳሪው ሲቀጠቀጥጥ ፎጣ እንደሚያስወረውር ሁሉ ቡድኔ ደካማ አልነበረም
የተልከሰከሰ የዘቀጠ የወረደ ቡድን አልነበረኝም .. ውጤቱ ደካማ በመሆኑ ግን ቅር ብሎኛል
የሚዲያ አካላትን አስተያየት እሰማለሁ ለሀገር የነገ እድገት ለነገ ብሄራዊ ቁድን ማሰብ አለብን በቅንንነት ካያችሁት ሌሎቹ በእድሜ ይበልጡናል ከአሰልጣኞች ጋር ሳወራ ለብሄራዊ ቡድኖቻቸው የቀረበውን ቡድን ይዘው እንደመጡ ነግረውኛል” ብሏል።
በኢትዮጵያ ከ20 አመት በታች ሻምፒዮና ላይ አሸናፊ የሆነው ምክትል አሰልጣኙ ከራሱ ቡድን አንድም ተጨዋች ሳያካትት ስለመሄዱ የተጠየቀው አሰልጣኝ ስዩም ” እንኳን ቡድኔ ውስጥ ከ20 አመት ሊግ ውስጥ ውስጥ ከ20 አመት በታች ተጨዋቾች የሉም ይሄ መታረም አለበት በእድሜ ትልቅነት የሚገመቱና የሚጠረጠሩ ተጨዋቾች በሙሉ ፓስፖርታቸው ያጫውታቸዋል” ሲሉ ያልተጠበቀ ምላሽ ሰጥተዋል።
ዋሊያዎቹን በቀጣይ ልትረከብ እንደሆነ መረጃዎች እየወጡ ነው መረጃው እውነት ነው ወይ ..? የተባለው አሰልጣኝ ስዩም ” ከሀገሪቱ ምርጥ ሶስት አሰልጣኞች መሃል አንዱ እኔ ነኝ ሁለቱን ብትጠሩም አለሁበት ያለሁበት የትምህርት ዝግጅትም ጥሩ የሚባል ነው” ሲል ቀጣዩ የዋሊያዎቹ አሰልጣኝ ሊሆን እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል።
ለቡድኑ አቀባበል ስላለመደረጉ የተጠየቀው አሰልጣኝ ስዩም ” እውነት ነው አቀባበል አልተደረገልንም እግርኳስ በውጤት ስኬትና በመሸነፍ ውስጥ ያለ ነው ይህ ግን መለመድ አለበት ለምን አቀባበል እንዳልተደረገም አልገባኝም ” ሲል ተናግሯል።
አሰልጣኝ ስዩም ” እድሜና ጤና ይስጠኝ እንጂ ለሀገሬ እየለፋሁ እቀጥላለሁ በእስካሁኑ የሰልጣኝነት ህይወቴ ለብሄራዊ ቡድን የበቁ ተጨዋቾችና በአሁኑ ወቅት አሰልጣኝ የሆኑ ባለሙያዎች በማፍራቴ እኮራለሁ” ሲል አስተያየቱን ሰጥቷል።