መነሻ ገጽ Uncategorized በኢትዮጵያ ዋንጫ መቐለ ወደ ግማሽ ፍፃሜው ተሻግሯል
Uncategorized

በኢትዮጵያ ዋንጫ መቐለ ወደ ግማሽ ፍፃሜው ተሻግሯል

አጋራ
አጋራ

በኢትዮጵያ ዋንጫ የሩብ ፍፃሜ የመጀመሪያ ቀን ጨዋታ መቐለ 70 እንደርታ የከፍተኛ ሊጉን ቦዲቲ ከተማን 3ለ2 በመርታት ወደ ግማሽ ፍፃሜው አልፏል።

ዘጠኝ ሰዓት ሲል በአዲስ አበባ ስታዲየም በኢትዮጵያ ዋንጫ የሩብ ፍፃሜ የመጀመሪያ ቀን መርሀግብር የፕሪምየር ሊጉን ክለብ መቐለ 70 እንደርታን በከፍተኛ ሊጉ ምድብ ለ ላለመውረድ እየታገለ ካለው ቦዲቲ ከተማ ጋር ያደረገውን ጨዋታ 3ለ2 በመርታት ወደ ግማሽ ፍፃሜውን መሸጋገር ችሏል። ቦዲቲዎች 25ኛው ደቂቃ ከግራ የማዕዘን ምት የተሻማች ኳስን በትዕዛዙ መንግሱ ሞክራ በግቡ ቋሚ ስትመለስ ሙሉቀን ተስፋዬ ወደ ጎልነት ለውጦ የአሰልጣኝ አዲሱ ዶይሶን ክለብ መሪ ማድረግ ችሏል። ግብ ካስተናገዱ በኋላ አቻ ለመሆን ጥረት ያደረጉት መቐለዎች 37ኛው ደቂቃ በጨዋታው የጎመራው ፍፁም አለሙ በጥልቀት ከቦና አሊ ጋር በነበረው ጥምረት የቦዲቲ ተከላካዮች ስህተት ታክሎበት ሞዓም አናብስቱን አቻ አድርጓል።

ከዕረፍት መልስ በይበልጥ በቆሙ እና በሽግግር ከሚነሱ ኳሶች ማጥቃታቸውን አጠናክረው የቀጠሉት መቐለዎች 71ኛው ደቂቃ ከፍፁም አለሙ መነሻዋን አድርጋ በተከላካይ እና በግብ ጠባቂ ተነካክታ የተመለሰችን ኳስ አዲሱ የክለቡ ፈራሚ ፕሪንስ ኦፊሬ የመሪነት ጎል አድርጓታል ከደቂቃዎች በኋላ ቦና አሊ ሦስተኛዋን ጎል ከመረብ ሲያሳርፍ ጨዋታው ሊጠናቀቅ በመጨረሻዎቹ አምስት ደቂቃዎች መነቃቃት የጀመሩት ቦዲቲዎች በቴዎድሮስ በለጠ አማካኝነት ጎል ቢያገኙም ከሽንፈት ማዳን ሳትችል ጨዋታው 3ለ2 የመቐለ አሸናፊነት መቋጨት ችሏል። መቐለም በግማሽ ፍፃሜው ከኢትዮጵያ መድን እና ቤንች ማጂ አሸናፊ ጋር ለፍፃሜ ለማለፍ ይፋለማል።

የኢትዮጵያ ዋንጫ ቀጣይ መርሀግብር ነገም ሲቀጥል መቻል ከ ወልዋሎ ዕርብ ኢትዮጵያ መድን ከቤንች ማጂ ቡና ቅዳሜ ደግሞ ነገሌ አርሲ ከ ሲዳማ ቡና ጋር ይፋለማሉ።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
Uncategorized

FIFA temporarily lifts transfer ban on St. George

Saint George's has had its transfer ban imposed by FIFA temporarily lifted...

Uncategorized

29ኛ ሳምንት የዲሲፕሊን ውሳኔዎች

የዲሲፕሊን ውሳኔዎች ዳግም ወንድሙ (ሀዲያ ሆሳዕና) : ክለቡ ከ መቐለ 70 እንደርታ...

Uncategorized

ሀይለየሱስ ባዘዘው ከዳኝነት አለም ራሳቸውን አገለሉ

ሀያ አምስት አመታቶችን በዳኝነት ያገለገሉት ዶ/ር ሀይለየሱስ ባዘዘው ከዳኝነት አለም በይፋ ማቆማቸውን...

Uncategorized

ወልዋሎ ወደ ግማሽ ፍፃሜው ማለፉን አረጋገጠ

በኢትዮጵያ ዋንጫ የሩብ ፍፃሜ የሁለተኛ ቀን መርሀግብር ወልዋሎ ዓ/ት ዩኒቨርስቲ በመለያ ምት...