መሳይ አያኖ አዲሱ የኢትዮጵያ ቡና የግብ ዘብ ሆኗል።

በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የሚሳተፈው ኢትዮጵያ ቡና በሲዳማ ቡና የማይረሳ ጊዜ ያሳለፈውን የግብ ዘብ የግሉ አድርጓል። ከሀላባ ከተገኘ በኋላ በአርባምንጭ ከተማ በተለይ ደግሞ በሲዳማ ቡና ቤት አይረሴ ጊዜዎችን ያሳለፈው ይህ ግብ ጠባቂ መሳያ አያኖ በመቀጠል በሀድያ ሆሳዕና እና ወልቂጤ ከተማ መለያ በፕሪምየር ሊጉ ቆይታን ያደረገ ሲሆን አሁን ደግሞ የጋናዊውን ግብ ጠባቂ ዳላንድ ኢብራሂም ተፎካካሪ ለማድረግ በአንድ አመት ውል በእጁ አስገብቷል።
አስተያየት ይስጡ