መነሻ ገጽ ሲዳማ ቡና የሲዳማ ቡና ቡድን መሪ ታገደ
ሲዳማ ቡናዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

የሲዳማ ቡና ቡድን መሪ ታገደ

አጋራ
አጋራ

በዮሴፍ ከፈለኝ

የፕሪምየር ሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና የቡድን መሪው የቀድሞው ዳኛ ዕግድ ተጥሎባቸዋል።

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውድድርና ስነስርዓት ኮሚቴ የሲዳማ ቡና ቡድን መሪ የሆኑትን የቀድሞውን ኢንተርናሽናል ዳኛ ክንዴ ሙሴን ማገዱ ታውቋል።

ከታማኝ ምንጭ በተገኘ መረጃ በረዳት ዳኝነቱ የሚታወቀው የአሁኑ የሊጉ መሪ የቡድን መሪ ክንዴ ሙሴ በፕሪምየር ሊጉ ሲዳማ ቡና በሚያደርጋቸው ጨዋታዎችጨየዳኝነት ምደባን ቀድሞ ማወቁና መረጃውን ያቀበለውን የኮሚቴ አባል ወይም ሌላ ባለሙያን ስም አጋልጥ ሲባል ፍቃደኛ ባለመሆኑ ከቡድን መሪነቱ መታገዱን የደረሰን መረጃ ያስረዳል።

ከሁለት አመት በፊት ከዳኝነት አለም የተሰናበተው እና ባለፈው አመት የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌድሬሽን የብሄራዊ ዳኞች ኮሚቴ አባል እና የፊዚካል ኢንስትራክተር ሆኖ  ያገለገለው ክንዴ ከሌላው ወገን የተሻለ መረጃ የማግኘት ዕድል ቢፈጥርም አወዳዳሪ አካሉ ምንጩን ባለመግለፁ እርምጃ መውሰዱ ታውቋል። በቀጣይ የሊጉ ፉክክር ላይ ጥያቄ  እንዳይፈጥር አወዳዳሪ አካሉ ከብሄራዊ ዳኞች ኮሚቴ አመራሮች ጋር ጠንከር ያለ ውይይት ማድረግ እንደሚጠበቅበት ይታመናል።

ሲዳማ ቡና በሊጉ የ28ኛ ሳምንት መርሀግብር ዛሬ ከድሬዳዋ ከተማ ጋር ያደረገውን ጨዋታ  በአቤል ያለው ሁለት ጎሎች 2ለ0 በማሸነፍ መሪነቱን አጠናክሯል።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየዲሲፕሊን ውሳኔዎችዲሲፕሊን ውሳኔ

የ32ኛ ሳምንት የዲሲፕሊን ውሳኔዎች

የዲሲፕሊን ውሳኔዎች አህመድ ረሺድ (ድሬደዋ ከተማ) : በኢትዮጵያ ዋንጫ ውድድር 1 እንዲሁም...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሀምራዊ ለባሾቹ እና የጣና ሞገዶቹ ጣፋጭ ሦስት ነጥብን ወደ ቋታቸው ከተዋል

በሊጉ የሳምንቱ የሁለተኛ ቀን ጨዋታ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና ባህርዳር ከተማ ወሳኝ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሲዳማ ቡና ሲሸነፍ በተጠባቂው ጨዋታ መቻል በጎል ፌሽታ ነገሌን ረቷል

በሳምንቱ የመጀመሪያ ቀን ጨዋታ የሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና በሀድያ ሆሳዕና ሽንፈት ሲያስተናግድ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽንየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

ውጤት ለውጧል የተባለው ዳኛ ተባረረ

በዮሴፍ ከፈለኝ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውጤት ለውጠዋል የተባሉ አርቢትሮችን ወደመጡበት መመለሱን አሁንም ቀጥሏል። ከቀናት...