መነሻ ገጽ Uncategorized የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ በሰባት ስታዲየሞች ላይ ይደረጋል
Uncategorized

የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ በሰባት ስታዲየሞች ላይ ይደረጋል

አጋራ
አጋራ

ሊጉ የሚደረግባቸው ስታዲየሞች ታወቁ።

የ2019 የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ መስከረም 30/2019 እንደሚጀመር ይታወሳል። አስራ ስምንት ክለቦች በሚሳፉበት የሀገሪቱ ትልቁ የሊግ ዕርከን በሰባት ስታዲየሞች እንዲደረግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ አክሲዮን ማህበር በሦስት ዙር በየስታዲሞቹ ተዟዙሮ ከተመለከተ በኋላ ውሳኔ ማሳለፉን ሀትሪክ ስፖርት አረጋግጧል።

በዚህም መሠረት አዲስ አበባ ስታዲየም ፣ የአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ ስታዲየም ፣ የሀዋሳ ዩኒቨርስቲ ስታዲየም ባሉበት ሲቀጥሉ የባህርዳር አለም አቀፍ ስታዲየምም ከአመታት በኋላ የሊጉን ውድድር የሚያስተናግድ ሲሆን የሀላባ ስታዲየም ፣ የሆሳዕናው አብዩ ኤርሳሞ ስታዲየም ፣ የአርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ አባያ ካምፓስ ስታዲየም የ2019 የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግን ያስተናግዳሉ።

ስለሆነም ፕሪምየር ሊግ በስድስት ቋት ተከፍሎ በአንድ ሜዳ ላይ በደርሶ መልስ መልኩ የሚደረግ ሲሆን ይህም በአንድ ከተማ ረጅም የውድድር ጊዜን ከማሳለፉ ለክለቦች እፎይታን የሰጠ ጉዳይ መሆኑን ታውቋል።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
Uncategorized

ካሌብ በየነ ወሳኙን ግብ አስቆጥሮ ሸገር ሲቲን የድል ሦስት ነጥብ አስጨበጠ!

በአቤኔዘር አበበ በ2019 ዓ.ም የሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ በአዲስ አበባ ስታዲየም በተደረገው...

Uncategorized

“ግብ ጠባቂ ለኢትዮዽያ መምረጥ ከብዶናል” አሰልጣኝ ዮሐንስ ሳህሌ

በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ጠቅላላ ጉባኤ ላይ በመገኘት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ዋና...

Uncategorized

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ከስብስቡ አራት ተጫዋቾችን ከስብስቡ ቀንሷል።

በሀዋሳ ከተማ ዝግጅት እያደረገ የሚገኘው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ትላንት ሶስት ተጫዋቾችን የቀነሰ...

Uncategorized

አዳማ ከተማ ወደ ልምምድ ሊገባ ነው

አዳማ ከተማ የፊታችን ሰኞ ልምምድ ይጀምራሉ። በቀጣዩ የ2019 የውድድር ዘመን በኢትዮጵያ ፕሪምየር...