መነሻ ገጽ የአዲስአበባ ከተማ ዋንጫ በ 12ኛው የአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ ከምድብ ሀ ወደ ግማሽ ፍፃሜ አላፊ የሆኑት ቡድኖች ተለይተው ታወቁ።
የአዲስአበባ ከተማ ዋንጫ

በ 12ኛው የአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ ከምድብ ሀ ወደ ግማሽ ፍፃሜ አላፊ የሆኑት ቡድኖች ተለይተው ታወቁ።

አጋራ
አጋራ

በ 12ኛው የአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ የአምስተኛ ቀን ውሎ የምድብ ሀ የመጨረሻ ጨዋታዎች የተከናወኑ ሲሆን ኢትዬጵያ ቡና እና ጅማ አባጅፋር ግማሽ ፍፃሜውን መቀላቀላቸውን አረጋግጠዋል።
በቅድሚያ 8:00 ላይ የተገናኙት አ/አ ከተማ እና ተጋባዡ ጅማ አባጅፋር ሲሆኑ በጨዋታውም ተጋባዡ ጅማ አባጅፋር 2 -1 በሆነ ውጤት አሸናፊ መሆን ችሏል። እረጃጅም ኳሶች በተስተዋሉበት በዚህ ጨዋታ ግብ የማግባት ቅድሚያውን የወሰዱት ጅማ አባጅፋሮች ሲሆኑ 13ኛው ደቂቃ ላይ ሳምሶን ቀልቻ ሲያስቆጥር 72ኛው ደቂቃ ላይ ገናናው ረጋሳ አ/አ ከተማን አቻ ማድረግ ችሎ ነበር። ከ 8 ደቂቃዎች በኀላ ሳምሶን ቀልቻ ለራሱም ለቡድኑም ሁለተኛ ጎል በማስቆጠር ቡድኑን ወደ ግማሽ ፍፃሜ ማሳለፍ ችሏል።
በጨዋታው ሁለት ግቦችን ማስቆጠር የቻለው ሳምሶን ቀልቻ የጨዋታው ኮከብ ተብሎ ተሸላሚ መሆን ችሏል፡፡

10:00 ላይ የተገናኙት ኢትዬጵያ ቡና እና ደደቢት ጨዋታቸውን ያለምንም ግብ 0 – 0 ጨርሰዋል፡፡ ብዙም ማራኪ የሚባል እንቅስቃሴ ባልተስተዋለበት በዚህ ጨዋታ ኢትዬጵያ ቡና አጥቅቶ ለመጫወት ቢሞክርም ያገኟቸውን አጋጣሚዎች ከመረብ ጋር ማገናኘት ተስኗቸው አምሽተዋል። በጨዋታው ጥሩ ብቃት ያሳየው የኢትዬጵያ ቡናው አማካይ እያሱ ታምሩ የጨዋታው ኮከብ ተብሎ ተሸላሚ መሆን ችሏል፡፡

ሁለቱን የጨዋታ ውጤቶች ተከትሎ ኢትዬጵያ ቡና በ 5 ነጥብ ምድቡን አንደኛ ሆኖ በማጠናቀቅ እንዲሁም ተጋባዡ ጅማ አባጅፋር 4 ነጥብ ይዞ ብዙ ባገባ በሚለው ህግ መሰረት ደደቢትን ጥሎ ግማሽ ፍፃሜውን መቀላቀል ችለዋል።

ክለብ ተጫወተ አገባ ገባበት ጎል ነጥብ

ኢትዮጵያ ቡና 3 4 1 +3 5

ጅማ አባ ጅፋር 3 2 2 +0 4

ደደቢት 3 1 1 +0 4

አ/አ ከተማ 3 2 6 -4 3

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ኢትዮጵያ ቡናዜናዎችየአዲስአበባ ከተማ ዋንጫ

ኢትዮጵያ ቡና በአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ እንደማይሳተፍ አስታወቀ

  18ኛው የአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ ከዛሬ ጀምሮ እስከ መስከረም አምስት ድረስ...