By using this site, you agree to the Privacy Policy and Terms of Use.
Accept
ሀትሪክ ስፖርት ኢትዮጵያሀትሪክ ስፖርት ኢትዮጵያ
  • መነሻ ገፅ
  • ዜናዎች
  • ፕሪሚየር ሊግ
    • ባህርዳር ከተማ
    • ወላይታ ዲቻ
    • ድሬዳዋ ከተማ
    • ፋሲል ከነማ
    • ሲዳማ ቡና
    • አዳማ ከተማ
    • ሀዋሳ ከተማ
    • ቅዱስ ጊዮርጊስ
    • ኢትዮጵያ ቡና
    • ጅማ አባጅፋር
    • ወልቂጤ ከተማ
    • ሰበታ ከተማ
    • ሀዲያ ሆሳዕና
  • ዋልያዎቹ
  • ውድድሮች
  • English Article
  • French Articles
  • ስለ እኛ
Reading: “በዛሬው ቡድናችን ላይ ጨዋታውን መቆጣጠር የሚችሉ ተጫዋቾች እና አስፈሪ የአጥቂ ክፍል ነበረን” አሰልጣኝ ፋሲል ተካልኝ “የተስማሙት በአስተዳደር ላይ ያሉ ሰዎች ናቸው ፤ እኛ አሰልጣኞች ተሰብስበን አይደለም” አሰልጣኝ ዮሐንስ ሳህሌ
Share
Notification Show More
Latest News
ወላይታ ድቻ የሊጉን መሪ አሸንፏል
ዜናዎች ቅዱስ ጊዮርጊስ ኢትዮ-ኤሌክትሪክ ሲዳማ ቡና የጨዋታ ዘገባ መቻል የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ኢትዮጵያ ቡና ወልዋሎ
ኢትዮጵያ ቡና የፋይናስ ችግር እንገጠመው ተገለፀ
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ኢትዮጵያ ቡና ዜናዎች
“ኢትዮዽያ ቡናን ብትነኩ ከመቃብሬ ተነስቼ አጠፉቹሀለው” መቶ አለቃ ፍቃደ ማሞ
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ኢትዮጵያ ቡና ዜናዎች
ኢንተርናሽናል አርቢትር ማኑኤ ወ/ጻዲቅ ከአዳማ ተሰናበተ
ዜናዎች የኢትዮጵያ እግርኳስ ዳኞች ማህበር የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን
በረከት አማረ ወደ ቀደመ ክለቡ ሊመለስ ይችላል ?
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የዝውውር ዜናዎች ኢትዮጵያ ቡና ዜናዎች
Aa
ሀትሪክ ስፖርት ኢትዮጵያሀትሪክ ስፖርት ኢትዮጵያ
Aa
  • መነሻ ገፅ
  • ዜናዎች
  • ፕሪሚየር ሊግ
  • ዋልያዎቹ
  • ውድድሮች
  • English Article
  • French Articles
  • ስለ እኛ
  • መነሻ ገፅ
  • ዜናዎች
  • ፕሪሚየር ሊግ
    • ባህርዳር ከተማ
    • ወላይታ ዲቻ
    • ድሬዳዋ ከተማ
    • ፋሲል ከነማ
    • ሲዳማ ቡና
    • አዳማ ከተማ
    • ሀዋሳ ከተማ
    • ቅዱስ ጊዮርጊስ
    • ኢትዮጵያ ቡና
    • ጅማ አባጅፋር
    • ወልቂጤ ከተማ
    • ሰበታ ከተማ
    • ሀዲያ ሆሳዕና
  • ዋልያዎቹ
  • ውድድሮች
  • English Article
  • French Articles
  • ስለ እኛ
Have an existing account? Sign In
Follow US
  • Advertise
© 2023 Hatrick Spoert. Design by Tech-ethiopia.com All Rights Reserved.
ህዳሴ ዋንጫዜናዎችቅዱስ ጊዮርጊስየአዲስአበባ ከተማ ዋንጫአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫየአሰልጣኞች አስተያየትፋሲል ከነማ

“በዛሬው ቡድናችን ላይ ጨዋታውን መቆጣጠር የሚችሉ ተጫዋቾች እና አስፈሪ የአጥቂ ክፍል ነበረን” አሰልጣኝ ፋሲል ተካልኝ “የተስማሙት በአስተዳደር ላይ ያሉ ሰዎች ናቸው ፤ እኛ አሰልጣኞች ተሰብስበን አይደለም” አሰልጣኝ ዮሐንስ ሳህሌ

Habtamu Mitku
Habtamu Mitku 5 months ago
Share
SHARE

በህዳሴ ዋንጫ የምድብ አንድ ሁለተኛ ጨዋታ ቅዱስ ጊዮርጊስ ፋሲል ከነማን 4 ለ 1 አሸንፏል።

ከቀን 10:00 ጀምሮ በተደረገው ጨዋታ ፍፁም ጥላሁን ፣ አቤል ያለው ፣ ቡአይ ኩዬት እና ተገኑ ተሾመ የቅዱስ ጊዮርጊስን ግቦች ሲያስቆጥሩ ቃልኪዳን ዘላለም የፋሲል ከነማን ብቸኛ ግብ ከመረብ አሳርፏል።

ከጨዋታዉ በኋላ የሁለቱም ቡድን አሰልጣኞች የድህረ ጨዋታ አስተያየት የሰጡ ሲሆን የፋሲል ከነማው ዋና አሰልጣኝ ዮሐንስ ሳህሌ ውድድሩ ተጫዋቾችን ለማየት ዕድል የሚሰጣቸው መሆኑን ተናግረዋል።

የመጀመሪያ ጨዋታቸው መሆኑን ያስታወሱት አሰልጣኝ ዮሐንስ ሳህሌ ያሉባቸውን ችግሮች እና ክፍተቶች ለማየት እንደሚረዳቸው ገልጸዋል።

- ማሰታውቂያ -

በተለያዩ አሰልጣኞች ከተነሳው የደመወዝ ጣሪያ የፋይናንስ ስርዓት መመሪያው ጋር በተያያዘም አሰልጣኝ ዮሐንስ ሳህሌ ተከታዩን ብለዋል።

“ይሄ አስትዳደራዊ ጉዳይ ነው። እኔ በሜዳ ላይ ነው መመለስ የምችለው ፤ የተስማሙት በአስተዳደር ላይ ያሉ ሰዎች ናቸው። እኛ አሰልጣኞች ተሰብስበን አይደለም። ስለዚህ ከአሰልጣኞች ጋር ምንም አይገናኝም። ግነ ባለው ሁኔታ ላይ የሚያምኑ ከሆነ ክለቦቹ ካመኑበት እኛ ሜዳ ላይ የሚሰራውን ስራ ነው ፌር ነው አይደለም አላውቅም እንግዲህ የወሰኑት ሰዎች መነጋገር ያለባቸው።”

የቅዱስ ጊዮርጊሱ ዋና አሰልጣኝ ፋሲል ተካልኝ በበኩሉ ቡድኑ ሜዳ ላይ በነበረው እንቅስቃሴ ደስተኛ እንደነበር የተናገረ ሲሆን በዛሬው ጨዋታ ካለፈው ጨዋታ የተሻለ ነገር ስለመኖሩ ገልጿል።

“በሁለቱ ጨዋታ ሁለት ቡድን አዘጋጅተን ዓመቱን ሙሉ የምንጠቀምባቸውን ተጫዋቾች እዚህ ውድድር ላይ ማየት ነው የፈለግነው ፤ እሱ አንዱ ድላችን ነው ብለን እናስባለን።”

“ሁለተኛው በሁለቱ ቡድኖች መሀል የነበረው አንዱ ልዩነት ልምድ ነው። በዛሬው ቡድናችን ላይ ጨዋታውን መቆጣጠር የሚችሉ ከፊት በጣም ካገኙ ጎል ማግባት የሚችሉ አስፈሪ የአጥቂ ክፍል አለን። እሱ ትልቅ ልዩነት ነው ብለን እናስባለን። ለምን ? ባለፈው ጨዋታ በመጀመሪያው አጋማሽ ያገኘናቸውን የግብ ዕድሎች ብንጠቀም ምናልባት የበለጠ ጨዋታው ውስጥ እንሆን ነበር። ያ ነው ልዩነቱ ብዬ አስባለሁ።”

በአማካይ ክፍል ላይ እንደ በረከት ወልዴ እና አብርሃም ጌታቸው አይነት ተጫዋቾችን ያጣው ቅዱስ ጊዮርጊስ በወጣት እና ልምድ ያላቸው ተጫዋቾችን በማጣመር ጠንካራ የመሀል ክፍል ለመገንባት እየሰሩ መሆናቸውን አሰልጣኝ ፋሲል ተካልኝ ተናግሯል።

በጨዋታው ኮከብ ሆኖ ስለተመረጠው ሀብታሙ ጉልላትም አሰልጣኝ ፋሲል ይህንን ብሏል።

“ሀብታሙ ሁለገብ የምትለው አይነት ተጫዋች ነው። የራስ መተማመኑን በደንብ ከፍ ሲያደርግ ከዚህ የተሻለ ተጫዋች መሆን ይችላል። በቴክኒክም ሆነ በአካል ብቃት ጥሩ የሆነ ተጫዋች ነው። አዕምሮው ላይ እንሰራለን በራሱ እንዲተማመን የተሻለ መጫወት ይችላል። ሌሎችም በታዎች ላይ ብናስገባው ጥሩ መጫወት ይችላል ብለን እናምናለን። ዛሬ ኮከብ መሆኑ የበለጠ ከፍ ያደርገዋል። ኃላፊነቶች ይመጣሉ እንደዚህ አይነት ነገሮች እንዲረዳ ከኋላ ሆነን እናስተምረዋለን።”

በዛሬው ጨዋታ ከረጅም ጊዜ በኋላ ዳግም በቅዱስ ጊዮርጊስ ማልያ የተጫወተው አቤል ያለው ቡድኑን በአምበልነት እየመራ በመግባት ግብም ማስቆጠር ችሏል።

አቤል ያለው ትልቅ አቅም ያለው ተጫዋች መሆኑን ያነሳው አሰልጣኝ ፋሲል በቡድኑ ላይ የፈጠረውን መነቃቃት እንዲህ ገልፆታል።

“አቤል ያለውን ከፊት ማሰለፍ ለቡድኑ ትልቅ አቅም ነው። ሌሎች ተጫዋቾች እሱን እንደ አርአያ ነው የሚወስዱት የቅዱስ ጊዮርጊስን ባህል ከመረዳት አንፃር የበለጠ ከመጫወቱም ጎል ከማግባቱም በላይ እንደ መሪ በብዙ ነገር ይረዳናል ብለን እናስባለን። ዛሬ ከረጅም ጊዜ በኋላ ነው የተጫወተው ባሳየው ፐርፎርማንስ ደስተኛ ነኝ። የፊት ነስ ደረጃው ከፍ ሲል ሁሉም ሰው የሚያውቀውን አቤል ሜዳ ላይ እንደምናየው እርግጠኛ ነኝ።”

You Might Also Like

ወላይታ ድቻ የሊጉን መሪ አሸንፏል

ኢትዮጵያ ቡና የፋይናስ ችግር እንገጠመው ተገለፀ

“ኢትዮዽያ ቡናን ብትነኩ ከመቃብሬ ተነስቼ አጠፉቹሀለው” መቶ አለቃ ፍቃደ ማሞ

ኢንተርናሽናል አርቢትር ማኑኤ ወ/ጻዲቅ ከአዳማ ተሰናበተ

በረከት አማረ ወደ ቀደመ ክለቡ ሊመለስ ይችላል ?

Share this Article
Facebook Twitter Email Print
By Habtamu Mitku
Follow:
Writer at Hatricksport
Previous Article “በሚቀጥለው ዓመት 22 ቡድን ይሆናል ብዬ ነው የምጠብቀው” “በአዲሱ የደመወዝ ጣሪያ ምክንያት ቡድናችን ፈርሷል” “እኛ ማስፈረም አቅቶናል ሌላው እንዴት እንደሚያስፈርም ግልፅ አይደለም” አሰልጣኝ በፀሎት ልዑልሰገድ – የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዋና አሰልጣኝ
Next Article ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ አሰልጣኝ ቀጠረ !!

Follow US

Find US on Social Medias
127k Like
2.9k Follow
1.6k Follow
19.7k Follow

Weekly Newsletter

Subscribe to our newsletter to get our newest articles instantly!

ተነባቢ ዜናዎች
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየዝውውር ዜናዎችዜናዎችቅዱስ ጊዮርጊስ

ቡአይ ኩዌት ወደ ፈረሰኞቹ ቤት ለማምራት ተስማማ !

fitsum Wadu By fitsum Wadu 7 months ago
ነገሌ አርሲ ማስገረሙን ሲቀጥል ቀሪ ሁለት ጨዋታዎች በአቻ ውጤት ተጠናቀዋል
Bility looses appeal as CAS upholds ten year ban imposed by fifa
“የኢትዮጵያ እግር ኳስ አንድ ቀን እንደሚስተካከል ተስፋ አደርጋለሁኝ”
ኢትዮጵያ ቡና በረከት አማረና አቤል ከበደን አስፈርሟል
- Advertisement -
Ad imageAd image
Global Coronavirus Cases

Confirmed

0

Death

0

More Information:Covid-19 Statistics
about us

Phone: 0993808668 Email: [email protected] .

Find Us on Socials

© Hatrick Sport 2023 All Rights Reserved.

Removed from reading list

Undo
 

Loading Comments...
 

    Welcome Back!

    Sign in to your account

    Lost your password?