By using this site, you agree to the Privacy Policy and Terms of Use.
Accept
ሀትሪክ ስፖርት ኢትዮጵያሀትሪክ ስፖርት ኢትዮጵያ
  • መነሻ ገፅ
  • ዜናዎች
  • ፕሪሚየር ሊግ
    • ባህርዳር ከተማ
    • ወላይታ ዲቻ
    • ድሬዳዋ ከተማ
    • ፋሲል ከነማ
    • ሲዳማ ቡና
    • አዳማ ከተማ
    • ሀዋሳ ከተማ
    • ቅዱስ ጊዮርጊስ
    • ኢትዮጵያ ቡና
    • ጅማ አባጅፋር
    • ወልቂጤ ከተማ
    • ሰበታ ከተማ
    • ሀዲያ ሆሳዕና
  • ዋልያዎቹ
  • ውድድሮች
  • English Article
  • French Articles
  • ስለ እኛ
Reading: “አንዳንድ አዳዲስ ተጫዋቾች ካሰብኳቸው በላይ ሜዳ ላይ አግኝቻቸዋለሁ” “በአዕምሮ ደረጃ ጠንክረን ወደሚቀጥለው ጊዜ እንደምንሻገር እርግጠኛ ነን” “በመጀመሪያው አጋማሽ ጨዋታውን በበለጥንበት ሰዓት ጎሎች ብናገባ የተለየ ይሆን ነበር።” አሰልጣኝ ፋሲል ተካልኝ – የቅዱስ ጊዮርጊስ ዋና አሰልጣኝ
Share
Notification Show More
Latest News
ወላይታ ድቻ የሊጉን መሪ አሸንፏል
ኢትዮ-ኤሌክትሪክ ሲዳማ ቡና የጨዋታ ዘገባ መቻል የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ኢትዮጵያ ቡና ወልዋሎ ዜናዎች ቅዱስ ጊዮርጊስ
ኢትዮጵያ ቡና የፋይናስ ችግር እንገጠመው ተገለፀ
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ኢትዮጵያ ቡና ዜናዎች
“ኢትዮዽያ ቡናን ብትነኩ ከመቃብሬ ተነስቼ አጠፉቹሀለው” መቶ አለቃ ፍቃደ ማሞ
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ኢትዮጵያ ቡና ዜናዎች
ኢንተርናሽናል አርቢትር ማኑኤ ወ/ጻዲቅ ከአዳማ ተሰናበተ
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ዜናዎች የኢትዮጵያ እግርኳስ ዳኞች ማህበር
በረከት አማረ ወደ ቀደመ ክለቡ ሊመለስ ይችላል ?
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የዝውውር ዜናዎች ኢትዮጵያ ቡና ዜናዎች
Aa
ሀትሪክ ስፖርት ኢትዮጵያሀትሪክ ስፖርት ኢትዮጵያ
Aa
  • መነሻ ገፅ
  • ዜናዎች
  • ፕሪሚየር ሊግ
  • ዋልያዎቹ
  • ውድድሮች
  • English Article
  • French Articles
  • ስለ እኛ
  • መነሻ ገፅ
  • ዜናዎች
  • ፕሪሚየር ሊግ
    • ባህርዳር ከተማ
    • ወላይታ ዲቻ
    • ድሬዳዋ ከተማ
    • ፋሲል ከነማ
    • ሲዳማ ቡና
    • አዳማ ከተማ
    • ሀዋሳ ከተማ
    • ቅዱስ ጊዮርጊስ
    • ኢትዮጵያ ቡና
    • ጅማ አባጅፋር
    • ወልቂጤ ከተማ
    • ሰበታ ከተማ
    • ሀዲያ ሆሳዕና
  • ዋልያዎቹ
  • ውድድሮች
  • English Article
  • French Articles
  • ስለ እኛ
Have an existing account? Sign In
Follow US
  • Advertise
© 2023 Hatrick Spoert. Design by Tech-ethiopia.com All Rights Reserved.
ዜናዎችቅዱስ ጊዮርጊስየአዲስአበባ ከተማ ዋንጫአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫየአሰልጣኞች አስተያየትመቻልህዳሴ ዋንጫ

“አንዳንድ አዳዲስ ተጫዋቾች ካሰብኳቸው በላይ ሜዳ ላይ አግኝቻቸዋለሁ” “በአዕምሮ ደረጃ ጠንክረን ወደሚቀጥለው ጊዜ እንደምንሻገር እርግጠኛ ነን” “በመጀመሪያው አጋማሽ ጨዋታውን በበለጥንበት ሰዓት ጎሎች ብናገባ የተለየ ይሆን ነበር።” አሰልጣኝ ፋሲል ተካልኝ – የቅዱስ ጊዮርጊስ ዋና አሰልጣኝ

Habtamu Mitku
Habtamu Mitku 5 months ago
Share
SHARE

“ህዳሴ ዋንጫ” በሚል ስያሜ የሚደረገው 19ኛው የአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ በዛሬው ዕለት በይፋ ተጀምሯል።

በአዲስ አበባ ስታድየም በተደረገው የመክፈቻ ጨዋታ መቻል በሁለተኛው አጋማሽ ባስቆጠራቸው ግቦች ቅዱስ ጊዮርጊስን 4 ለ 0 አሸንፏል።

ከጨዋታዉ በኋላ ከሀትሪክ ስፖርት ድህረ ገፅ ጋር ቆይታን ያደረገው የቅዱስ ጊዮርጊሱ ዋና አሰልጣኝ ፋሲል ተካልኝ ስለ ጨዋታው ተከታዩን ብሏል።

“ጨዋታው ሁለት አይነት መልክ አለው ፤ የመጀመሪያ አጋማሽ በጣም ጥሩ የሚባል ነው። በሁለተኛው አጋማሽ ደግሞ ጎሎቹ ቶሎ ቶሎ መቆጠራቸው ተጫዋቾቻችንን ጫና ውስጥ ከቷቸዋል። እንደምታየው ወጣቶች ስለሆኑ በቀላሉ መመለስ አልቻሉም።በኋላ ደግሞ በቀይ ካርድም ወጣብን ፤ እነዛ ጨዋታውን ለውጠውታል ብዬ አስባለሁ።”

- ማሰታውቂያ -

“ግን በመጀመሪያው አጋማሽ ጨዋታውን በበለጥንበት ሰዓት ጎሎች ብናገባ የተለየ ይሆን ነበር። እኛ ልምምድ ከጀመርን አስር ቀናችን ነው። ስለዚህ አዳዲስ ተጫዋቾቻን ወጣቶቹን የት እንዳሉ ያየንበት ነው። በሁለተኛው አጋማሽ የአካል ብቃት ደረጃችን ሊወርድ እንደሚችል የሚጠበቅ ነው።”

የመጀመሪያው አጋማሽን የቡድኑ እንቅስቃሴ ጥሩ መሆኑን የጠቀሰው አሰልጣኝ ፋሲል አንዳንድ አዳዲስ ተጫዋቾች ከጠበቀው በላይ እንዳገኛቸው ተናግሯል።

አክሎም ወደዚህ ወድድር የመጣነው ዘግይተን ንግግር እንደመጀመራችን የተጫዋቾቻችን የአካል ብቃት እና የጨዋታ ዝግጁነት ከፍ ለማድረግ ነው ተጫዋቾቻችን በሚገባ አይተናል ብሏል።

በጨዋታው በሰፊ ውጤት መሸነፋቸው በቡድኑ ላይ የሚፈጥረው የስነ ልቦና ጫና ይኖር ይሆን ተብሎ ለቀረበለት ጥያቄም ይህን ብሏል።

“በዚህ ማልያ መሸነፍ አይዋጥም። ግን ስንመጣ ይህን ተነጋግረን ነው የመጣነው ካለንበት ደረጃ እና ከሸፈነው የልምምድ ጊዜ አንፃር መጥፎ ነገር እንኳን ቢያጋጥመንም በአዕምሮ ደረጃ ጠንክረን ወደሚቀጥለው ጊዜ እንደምንሻገር እርግጠኛ ነን።”

በጨዋታው በቡድኑ በኩል ያሉት የፊት መስመር ተጫዋቾች አቤል ያለው እና ቢንያም ፍቅሬ በጨዋታው መሰለፍ ያልቻሉት መጠነኛ ጉዳት ስላገጠማቸው አለመጫወታቸውን ተናግሯል።

አክሎም በቀጣይ ሀሙስ ከፋሲል ከነማ በሚያደርጉት ሁለተኛ ጨዋታ የመሰለፋቸው ነገር በማገገም ሁኔታቸው ላይ እንደሚወሰን ተናግሯል።

ቅዱስ ጊዮርጊስ በቀጣይ ሌሎች ተጫዋቾችን ወደ ክለቡ ተጨማሪ ተጫዋቾች ያስፈርም እንደሆነ ላቀረብንለት ጥያቄ ተከታዩን ብሏል።

“አንድ ግብ ጠባቂ እናመጣለን ብለን እናስባለን። ምናልባት ክፍት ቦታዎቻትን ላይ የምንጨምራቸው ተጫዋቾች ሊኖሩ ይችላሉ።”

በአዲስ አበባ ስታድየም ላይ በደጋፊዎቻችን ፊት በመጫወታችን ደስ ብሎናል ያለው አሰልጣኝ ፋሲል ቀጣይ የሊጉንም ጨዋታዎች እዚህ ሜዳ ስለምናደርግ ተጫዋቾንንም በዚህ ሜዳ ላይ ማየታችን ደስ ብሎናል ሲል ተናግሯል።

ይህ የቅድመ ውድድር ዘመን ዝግጅቱ አካል ነው ፤ የተጫዋቾቻችንን አቅም በአዕምሮም በአካልም ለማዘጋጀት እየሰራን ነው ሲልም አሰልጣኝ ፋሲል ተካልኝ ገልጿል።

You Might Also Like

ወላይታ ድቻ የሊጉን መሪ አሸንፏል

ኢትዮጵያ ቡና የፋይናስ ችግር እንገጠመው ተገለፀ

“ኢትዮዽያ ቡናን ብትነኩ ከመቃብሬ ተነስቼ አጠፉቹሀለው” መቶ አለቃ ፍቃደ ማሞ

ኢንተርናሽናል አርቢትር ማኑኤ ወ/ጻዲቅ ከአዳማ ተሰናበተ

በረከት አማረ ወደ ቀደመ ክለቡ ሊመለስ ይችላል ?

Share this Article
Facebook Twitter Email Print
By Habtamu Mitku
Follow:
Writer at Hatricksport
Previous Article “ሁለተኛው አጋማሽ ላይ መረጋጋት ብቻ ነው ያደረግነው” “ቅዱስ ጊዮርጊስ በፕሪሚየር ሊጉ ጥሩ ተፎካካሪ ይሆናል ብዬ አስባለሁ” አሰልጣኝ ሙሉጌታ ምህረት – የመቻል ዋና አሰልጣኝ
Next Article “የመጀመሪያው አጋማሽ ላይ ጎሎችን አስቆጠርን እንጂ እንቅስቃሴያችን ጥሩ አልነበረም” “አጥቂዎቻችንም ተገማች አለመሆናቸው ጥሩ ነገር ነው” አሰልጣኝ አብይ ካሳሁን – የኢትዮጵያ ቡና ዋና አሰልጣኝ

Follow US

Find US on Social Medias
127k Like
2.9k Follow
1.6k Follow
19.7k Follow

Weekly Newsletter

Subscribe to our newsletter to get our newest articles instantly!

ተነባቢ ዜናዎች
ሀትሪክ ስፖርትጋዜጣ

የእርስዎ ምርጫን ሀትሪክ ስፖርት ያንብቧት ሀትሪክ ስፖርት ዘወትር ማክሰኞ ለንባብ የምትበቃ ተወዳጅ ጋዜጣዎ ስትሆን በእዚህ ሳምንት የማክሰኞ እትሟ የሚከተለውን ዘገባ ይዛ ወጥታለች፡፡ ሀትሪክን ማክሰኞ በገበያ ላይ ሲያገኟት ለእናንተ ውድ አንባቢዎቿ ከምታስነብቦት የሀገር ውስጥ ዘገባዎቿ መካከል ከፍተኛ ተወዳጅነትን ባተረፈላት THE BIG INTERVIEW አምዷ የጋዜጣው ኤክስኪዩቲቭ ኤዲተር እና ጋዜጠኛ የሆነው ይስሃቅ በላይ በኢትዮጵያ እግር ኳስ ታሪክ ለበርካታ ዓመታት ማለትም ለ50 ዓመታት ያህል በስፖርቱ ውስጥ ከመቆየት ባሻገር ብዙ ዋንጫዎችን በማንሳት የመጀመሪያ አሰልጣኝ የሆኑትን ውጤታማውን አሰልጣኝ አስራት ኃይሌን በተለያዩ ርእሰ ጉዳዮች ላይ አናግሯቸው ምላሽን ሰጥቷል፡፡ አሰልጣኝ አስራት ምን ብለው ይሆን፤ ሀትሪክ በፕሪምየር ሊግ ዙሪያም የፋሲል ከነማ ተጨዋቾች የሁኑትን አይናለም ዓይለ እና በዛብህ መለዮን እንዲሁም የሲዳማ ቡናውን ሀብታሙ ገዛኸኝን አናግራም እነሱም በቡድኖቻቸው ዙሪያ የሚሉት አላቸው፡፡

Fitsum Nigusse By Fitsum Nigusse 7 years ago
የ2010 ኢትዮጵያ ኘሪሜየር ሊግ 17ኛ ሳምንት ተስተካካይ ጨዋታ በቀጥታ/ LIVESCORE/ ይከታተሉ
ዝውውር |​ ደደቢት ታደለ መንገሻና ፋሲካ አስፋውን የግሉ አድርጓል
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅጣት ተላለፈበት
ባህርዳር ከተማ የፍቃዱ ወርቁን ውል አራዘመ
- Advertisement -
Ad imageAd image
Global Coronavirus Cases

Confirmed

0

Death

0

More Information:Covid-19 Statistics
about us

Phone: 0993808668 Email: [email protected] .

Find Us on Socials

© Hatrick Sport 2023 All Rights Reserved.

Removed from reading list

Undo
Welcome Back!

Sign in to your account

Lost your password?