18ኛው የአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ ከዛሬ ጀምሮ እስከ መስከረም አምስት ድረስ እንዲካሄድ ከቀናት በፊት መርሐግብር እንደወጣለት ይታወሳል።
በስድስት ክለቦች መካከል ይካሄዳል በተባለው ውድድርም አምስት የአዲስ አበባ ክለቦች እንዲሁም ፋሲል ከነማ በተጋባዥነት ይሳተፋሉ ተብሎ ነበር።
ነገር ግን ዛሬ ቀን 10:00 ላይ ከመቻል ጋር ለመጫወት መርሐግብር ወጥቶለት የነበረው ኢትዮጵያ ቡና በውድድሩ እንደማይሳተፍ ይፋ አድርጓል።
- ማሰታውቂያ -
በጉዳዩ ላይ በኢትዮጵያ ቡና በኩል እና በአዘጋጁ የአዲስ አበባ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በኩል ያሉ ሀሳባችን በቀጣይ እናቀርባለን።