ዋሊያዎቹ የአፍሪካ እግርኳስ ኮንፌዴሬሽን ካፍ ባወጣው መርሃግብር መሰረት የፊታችን ረቡዕ ዳሬሰላም ላይ ከታንዛኒያ አቻቸው ጋር ላለባቸው ጨዋታ ዛሬ ጠዋት ወደ ታንዛኒያ አቅንተዋል።
በካፍ መርሃግብር መሰረት የአፍሪካ ሀገራት ብሄራዊ ቡድኖች በሳምንቱ መጨረሻም የሚያደርጉት የማጣሪያ ጨዋታ ሲቀጥል ካዛብላንካ ላይ የሚደረገው የጋምቢያና የቱኒዚያ ጨዋታ ይጠበቃል። ጋምቢያ ስታዲየሟ በመታገዱም ለተቀጡ ሀገራት ደራሽ እየሆነች በምትገኘው ሞሮኮ ላይ የምትጫወት ይሆናል።
ይህን ጨዋታ እንዲመሩ የተመረጡት አርቢትሮች ደግሞ ኢትዮጵያዊያን ኢንተርናሽናል አርቢትሮች በአምላክ ተሰማ በዋና ዳኝነት ቴዎድሮስ ምትኩ በአራተኛ ዳኝነት ትግል ግዛውና ይበቃል ደሳለኝ በረዳት ዳኝነት የጨዋታው ኦፊሺያል መሆናቸውን ይፋ ካደረገ በኋላ የመሃል ዳኝነቱ ስፍራ ላይ ለውጥ ማድረጉን አስታውቋል።
ኢንተርናሽናል አርቢትሮቹ በቅርቡ በወሰዱት ኮርስ ላይ የአካል ብቃት ፈተና የወሰዱ ሲሆን ኢንተርናሽናል አርቢትር በአምላክ ተሰማ በጉዳት ፈተናውን አለመውሰዱ ታውቋል። ካፍም ጉዳቱንና ፈተናውን አለመውሰዱን ከግምት አስገብቶ ጨዋታውን በመሃል ዳኝነት እንዲመራ ኢንተርናሽናል አርቢትር ቴዎድሮስ ምትኩን መድቧል። ከራተነኛ አርቢትርነቱን በሰበር ለኢንተርናሽናል አርቢትር ዶ/ር ኃይለየሱስ ባዘዘው መስጠቱ ታውቋል። ካፍ የጨዋታው ኮሚሽነር ከሴራሊዮን መሆኑን ጭምር አሳውቋል።
- ማሰታውቂያ -
ኢንተርናሽናል አርቢትር በአምላክ ተሰማ በጉዳት ሌላዋ ኢንተርናሽናል አርቢትር ብርቱካን ማሞ ደግሞ የአካል ብቃት ፈተናውን ማለፍ ባለመቻሏ የወደቀች ሲሆን ሁለቱም ወደ ውድድሩ ለመመለስ ካፍ የኤም. ኤ ኮርስ የሚሰጥበት ሌላ የአፍሪካ ሀገር ሄደው መፈተን የሚኖርባቸው መሆኑ ይታወቃል።