በውጪ ሃገር የሚጫወቱ ኢትዮጵያዊያን ተጨዋቾች ፕሮፌሽናልነት ይዘው ስለሚመጡ አብረው መዘጋጀታቸው ጥቅሙ የበዛ ነው ሲል አሰልጣኝ ገብረመድህን ሃይሌ ተናገረ።
ዋሊያዎቹ በቀጣዩ ሳምንት ከሜዳ ውጪ ከታንዛኒያና ዲሞክራቲክ ኮንጎ ብሄራዊ ቡድን ጋር ላለባቸው ጨዋታ ያደረጉትን ዝግጅት በተመለከተ አሰልጣኝ ገብረመድህን ሃይሌ በሰጠው መግለጫ ” የተጨዋቾች የአካል ብቃት ወርዶ በመገኘቱ ባለፉት 13 ቀናት ለባላንስ ጠንካራ የአካል ብቃት ስራ ሰርተናል” ሲል ተናግሯል። አሰልጣኙ ይህን ቢልም በተቃራኒ የአካል ብቃት አሰልጣኝና የቪዱዮ አናሊስት የግድ አስፈላጊ አይደለም ማለቱ አነጌጋሪ ሆኗል።
አሰልጣኙ 21 ተጨዋች ይዘው ዝግጅት እንደጀመሩና አሁን 25 መድረሳቸው ከነገ በስቲያ 2 ተጨዋቾችን ቀንሰው 23 ተጨዋቾችን ይዘው እንደሚጓዙ ተናግሯል። እስከ አሁን ባለን መረጃ አቡበከር ናስር አቤል ያለውና መስፍን ታፈሰ በጉዳት ከቡድኑ ውጪ መሆናቸውን አሰልጣኝ ገብረመድህን ገልጿል።
” አቤል ያለው ጉዳት ላይ መሆኑን መረጃ ልኳል አቡበከር ግን እመጣለሁ ብሎ ባለቀ ሰዓት ነው ጉዳት አለብኝ ብሎ የቀረው እውነት ነው የሚለው መጣራት አለበት ውሸት ከሆነ ግን ለሱ ጥሩ አይሆንም ” ያለው አሰልጣኝ ገብረ መድህን ” በውጪ ሃገር የሚጫወቱ ኢትዮጵያዊያን ተጨዋቾች ፕሮፌሽናልነት ይዘው ስለሚመጡ ጠንክሮ መስራትን ስለሚያስተምሩ አብረው መዘጋጀታቸው ጥቅሙ የበዛ ነው ሲል ተናግሯል።
“የወዳጅነት ጨዋታን ሳናካትት ያደረግነው ጨዋታ አራት ነው ከሜዳ ችግር አንጻር አራቱም ከሜዳ ውጪ የተደረገ ሆኖ ለምን ግብ አይቆጠርም የሚለው ልክ አይደለም ይሄ የአጥቂ ችግር የአገሪቱ እግርኳስ ችግር ነው ዓለም ላይም አጥቂ ጠፍቷል እኛ ጋር ደግሞ የባሰ ነው ለውጡ በአንድ ጀምበር አይመጣም ለለውጥ አመታት ይፈልጋል ለዚህ ነው እንደ ቡድን ማጥቃት ያለብን ” ሲል ተናግሯል። ስለሁለቱ ቡድኖች አቋም የተወሰነ መረጃ እንዳገኙና ከአፍሪካ ዋንጫ የተለየ ግን መረጃ የለም ብዙም አዲስ ነገር የላቸውምም ብሏል።
- ማሰታውቂያ -
አሰልጣኙ በአዲሱ የደመወዝ ክፍያ ምክንያት ተጨዋቾችና ክለቦች ውዝግብ ውስጥ ገብተዋል ከዝውውር አንጻር ተጨዋቾቹ ገባ ወጣ እያሉ ነበር አራት ተጨዋቾች ለፊርማ ልምምድ አቋርጠው እንዲሄዱ ፈቅደናል ይሄ ራሱ ልምምድ ላይ መቸገራችንን ያሳያል ” ሲል አስረድቷል።
ዋሊያዎቹ በቀጣይ ረቡዕ ከታንዛኒያ ሳምንት ሰኞ ደግሞ ከዲሞክራቲክ ኮንጎ ጋር የማጣሪያ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል።