መነሻ ገጽ ሀትሪክ ስፖርትጋዜጣ አሰልጣኝ አሰራት ኃይሌ ለስራ አስፈፃሚነት ሊወዳደር ነው፤የአንድ ከተማ አስተዳደርና የአምስት ክለቦችን ድጋፍ አግኝቷል
ሀትሪክ ስፖርትጋዜጣየኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽንጠቅላላ ጉባዔ

አሰልጣኝ አሰራት ኃይሌ ለስራ አስፈፃሚነት ሊወዳደር ነው፤የአንድ ከተማ አስተዳደርና የአምስት ክለቦችን ድጋፍ አግኝቷል

አጋራ
አጋራ

በ1958ዓ.ም ለዳርማር ህፃናት ቡድን በመጫወት የእግር ኳሱን ዓለም በይፋ የተቀላቀለው አሰልጣኝ ቀጣዩ የፌዴሬሽኑ የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል ለመሆን ተወዳዳሪ ሆነው ከቀረቡት ዕጩዎች አንዱ ሆነ።
ላለፉት 52 ዓመታት በክለብና በብሄራዊ ቡድን በተጫዋችነትና በአሰልጣኝነት ወርቃማ የእግር ኳስ ዘመን ያሳለፈው ውጤታማው አሰልጣኝ አስራት ኃይሌ(ጎራዴው)አሁን ደግሞ ፊቱን ወደ አመራርነት በማዞር የሀገሪቱን እግር ኳስ ለመታደግና የረዥም ዓመት ዕውቀቱና ልምዱን ለእግር ኳሱ በአመራርነት ለማበርከት ለስራ አስፈፃሚነት ዕጩ ተወዳዳሪ ሆኖ ብቅ ማለቱና ለዕጩ ተወዳዳሪነት የሚያበቃውን ደብዳቤ በዛሬው ዕለት ለፌዴሬሽኑ ማስገባቱ ታውቋል።
በኢትዮጵያ እግር ኳስ የገዘፈ ታሪክና በወርቅ የተፃፈ ስም ያለው አሰልጣኝ አስራት ኃይሌ በዋናነት የተወከለው በአዲስ አበባ መስተዳድር ሲሆን የአምስት ክለቦች ድጋፍንም ከአስት ኃያላን ክለቦች ለማግኘት የግማሽ ቀን ዕድሜ እንዳልወሰደበት ነው የተሰማው።
እንደታማኝ የመረጃ ምንጮቻችን ከሆነ ለአሰልጣኙ የድጋፍ ደብዳቤ የሰጡት አምስት ክለቦች ቅዱስ ጊዮርጊስ፣ኢት.ቡና፣ኢትዮ ኤሌክትሪክ፣መከላከያናኢት.ንግድ ባንክ ሲሆኑ ሁሉም ይገባሃል በሚል ስሜት ደብዳቤውን ለመፃፍ ሁለቴ እንኳን ማስብ እንዳላስፈለጋቸው ነው የተሰማው።
የአ.አ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ቀደም ሲል የ 52 ዓመት ልምድና ውጤት ላለው ለአሰልጣኙ የድጋፍ ደብዳቤን በመንፈጉ በርካታ ተቃውሞ የቀረበባቸው ሲሆን ግዙፍን ስህተታቸውን በዚህ መልክ ማረማቸው ብዙዎች በመልካም ጎኑ እንዲመለከቱት እድርጓል።ከዚሁ ከአ.አ የውክልና ዜና ሳንወጣ የተሰናባቹ ፌዴሬሽን ስራ እስፈፃሚና የቀድሞ የአ.አ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዘዳንት የነበሩትን አቶ ዮሴፍን በድጋሚ የወከለ ሲሆን ቀደም ሲል ደግሞ ኢንጂ.ኃይለየሱስን በተመሳሳይ ለስራ አስፈፃሚነት መወከሉ ይታወሳል።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ዜናዎችየኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን

የሚዲያ ኦፊሰሮች የአቅም ግንባታ ስልጠና በዛሬው ዕለት ተጠናቀቀ

ለፕሪምየር ሊግ እና ከፍተኛ ሊግ የኮሚኒኬሽን እና ማርኬቲንግ ስልጠና ተሰጠ የኢትዮጵያ እግር...

ኢትዮጵያ ንግድ ባንክወልዋሎዜናዎችየኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽንየዝውውር ዜናዎች

እዮብ አለማየሁ ለወልዋሎ እንዲጫወት ተወሰነ

እዮብ አለማየሁ ጉዳይ  ውሳኔ አገኘ። ከሀድያ ሆሳዕና ጋር የነበረው ውል መጠናቀቁን ተከትሎ...

መቻልኢትዮጵያ ቡናዜናዎችየኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽንየዝውውር ዜናዎች

ሁለቱ ተጫዋቾች ለመቻል እንዲጫወቱ ሲወሰን ቅጣትም ተጣለባቸው

አለምብርሀን ይግዛው እና አማካዩ አብዱልከሪም ወርቁ ጉዳይ ውሳኔ አገኘ። በያዝነው የክረምቱ የዝውውር...

ዜናዎችየኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን ፕሬዝደንት አቶ ኢሳያስ ጅራ ፌደሬሽኑን ለ3ኛ ጊዜ ለመምራት ብቸኛ እጩ ሆነው ቀርበዋል።

እጩ ሆኜ መቅረቤን እንጂ ሌሎች ተፎካካሪዎች ለምን በፕሬዝደንትንት ለመወዳደር እንዳልቀረቡ የማውቀው ነገር...