እጩ ሆኜ መቅረቤን እንጂ ሌሎች ተፎካካሪዎች ለምን በፕሬዝደንትንት ለመወዳደር እንዳልቀረቡ የማውቀው ነገር የለም – አቶ ኢሳያስ ጅራ

ፊፋ የፌዴሬሽኑን መተዳደሪያ ደንብ መፈተሽ አለበት በሚል ሰዉ መድቦ በሰራዉ ስራ፣ ደንቡ ተሻሽሎ የምርጫ ዘመን ለሦስት ጊዜ እንዲሆን በጠቅላላ ጉባኤ ተወስኗል ሲሉ ገልፀዋል። በፊፋ የመተዳደሪያ ደምብ መሰረት የምርጫ ጊዜ ለሦስት ጊዜያት በመሆኑ የፌዴሬሽኑ መተዳደሪያ ደንብም በዚህ ተቀርፆ በጥቅላላ ጉባኤ የተሻሻለ እንጂ እኔ የቀየርኩት ነገር የለም ብለዋል። ፕሬዝዳንቱ በተሰጠው ስልጣን የስራ አስፈጻሚ አባላትን የሚመርጥ ይሆናል።አቶ ኢሳያስ ጅራ በእጩነት ያቀረብኩት የጀመርኳቸውን ስራዎች ከዳር ለማድረስ ነው ብለዋል። ካፍ እና በፊፋ የኮሚቴ አባል በመሆኔ የተጀመሩትን ዓለም አቀፍ ግንኙነቶች በመጠቀም የፌደሬሽኑን ጅምር ስራዎች ለማጠናቅቀ እጠቀምበታለሁ ሲሉ ተናግረዋል።
አስተያየት ይስጡ