መነሻ ገጽ Uncategorized ፋሲል ከነማና ጅማ አባ ቡና ድል ቀንቷቸዋል
Uncategorized

ፋሲል ከነማና ጅማ አባ ቡና ድል ቀንቷቸዋል

አጋራ
አጋራ

በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የመጀመሪያው ዙር የማጠናቀቂያ ጨዋታዎች ዛሬ ተደርበዛሬው አለት በተካሄዱት የ15ኛ ሳምንት ጨዋታዎችም ፕሪምየር ሊጉን ዘንድሮ የተቀላቀሉት ፋሲል ከነማ እና ጅማ አባቡና ድል ቀንቷቸዋዛሬ በ9 ሰዓት ላይ በተደረገ ጨዋታዎች ድሬ ደዋ ላይ ድሬ ደዋ ከተማን የገጠመው ጅማ አባቡና ጨዋታውን በሰፊ የግብ ልዩነት በበላይነት ማጠናቀቅ ችሏል።

በዛሬው ጨዋታም ጅማ አባቡና ድሬ ደዋ ከተማን በመሜዳው 3ለ0 በሆነ ውጤት አሸንፈው ሙሉ ሶስት ነጥብ በመያዝ ተመልሰዋል።

በጨዋታውም ለጅማ አባ ቡና አሜ መሃመድ በ13ኛው ደቂቃ፣ በጊያድግልኝ ሴልያስ በ48ኛው ደቂቃ እንዲሁም ክሪዝቶም ንታምቢ በ56ኛው ደቂቃ የማሸነፊያ ጎሎችን ከመረብ አሳርፈዋል።

በተመሳሳይ በጎንደር ፋሲለደስ ስታዲየም አዳማ ከተማን ያስተናገደው ፋሲል ከነማ ድል ቀንቶታል።

በጨዋታውም ፋሲል ከተማ በሊጉ የደረጃ ሰንጠረዥ 2ኛ ደረጃ ላይ የሚገኘውን አዳማ ከተማን 1ለ0 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችሏል።

አምሳሉ ጥላሁን በ22ኛው ደቂቃ ለፋሲል ከነማ የማሸነፊያዋን ጎል ከመረብ አሳርፏል።

በአዲስ አበባ ስታዲየም 9 ሰዓት ላይ የተደረገው ሌላጨዋታ ደግሞ መከላከያን ከሲዳማ ቡና ያገናኘ ሲሆን፥ ጨዋታም ያለ ምንም ግብ በአቻ ውጤት ተጠናቋል።

እንዲሁም አርባ ምንጭ ላይ የተካሄደው የአርባ ምንጭ ከተማ እና የኢትዮጵያ ቡና ጨዋታም ያለ ምንም ግብ 0ለ0 በሆነ የአቻ ውጤት ተጠናቋል።

በ10 ሰዓት ላይ የተደረገው የደደቢት እና የወላይታ ድቻ ጨዋታ ደግሞ በደደቢት የበላይነት ተጠናቋል።

ደደቢት ጨዋታውን 3ለ0 በሆነ ውጤት ወላይታ ድቻን መርታት ችሏል።

አቤል እንዳለ በ20ኛው ደቂቃ፣ ጌታነህ ከበደ በ23ኛው ደቂቃ እንዲሁም ሽመክት ጉግሳ በ62ኛው ለደደቢት የማሸነፊያ ጎሎችን ከመረብ አሳርፈዋል። 

11 ሰዓት ከ30 ላይ በአዲስ አበባ ስታዲየም የተደረገው የኢትዮ ኤሌክትሪክ እና የሀዋሳ ከተማ ጨዋታም በኢትዮ ኤሌክትሪክ 2ለ0 አሸናፊነት ተጠናቋል።

በትናንትናው እለት ኢትዮጵያ ንግድ ባንክን በአዲስ አበባ ስታዲየም የገጠመው የሊጉ መሪ ቅዱስ ጊዮርጊስ 4ለ1 በሆነ ውጤት ማሸነፉ ይታወሳል።

እንዲሁም አዲስ አበባ ከተማ እና ወልዲያ ከተማ ያደረጉት ጨዋታ 1ለ1 በሆነ አቻ ውጤት ተጠናቋል።

በዚህም መሰረት ቅዱስ ጊዮርጊስ በ29 ነጥብ የደረጃ ሰንጠረዡን ሲመራ ደደቢት በ27 ነጥብ እንዲሁም አዳማ ከተማ በ26 ነጥብ ሁለተኛ እና ሶስተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል።

 
https://s.gravatar.com/avatar/46b974364d261d7e3712140a4fe6ef3b?s=80

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
Uncategorized

ቅዱስ ጊዮርጊስ የመቶ ሚሊዮን ብር ድጋፍ ተደረገለት

ዛሬ አንጋፋውን የቅዱስ ጊዮርጊስ የስፓርት ማህበር ከገጠመው የመፍረስ አደጋ ለመታደግ የተለያዩ አካላትን...

Uncategorized

ለዋልያዎቹ መጫወትን የሚመኘው የሴሪ ኣው ክለብ ተጫዋች ማነው ?

የጣሊያን ሴሪ ኣው ክለብ ቶሪኖ ንብረት ስለሆነው አስደናቂው የአጥቂ አማካይ ተጫዋች እንንገራችሁ።...

Uncategorized

ቡናማዎቹ ተጫዋች ለማስፈረም ተስማሙ !

  በዛሬው ዕለት ግብ ጠባቂ በማስፈረም ወደ ዝውውሩ የገቡት ኢትዮጵያ ቡናማዎች ዘካሪያስ...