በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የመጀመሪያው ዙር የመጨረሻ ተስተካካይ ጨዋታዎች ዛሬ ተካሂደዋል።
ጎንደር ላይ ወላይታ ዲቻን ያስተናገደው ፋሲል ከተማ ጨዋታውን 2 ለ 0 አሸንፏል።
የድል ጎሎችን ይስሃቅ መኩሪያ እና አብዱራህማን ሙባረክ አስቆጥረዋል።
በዚህም የሊጉን የመጀመሪያ ዙር በ26 ነጥቦች በሶስተኝነት አጠናቋል።
በአዲስ አበባ ስታዲየም 11 ከ30 ላይ በተደረገ ጨዋታ ደግሞ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከ ሃዋሳ ከተማ ተገናኝተዋል።
ጨዋታውን ሃዋሳ ከተማ ከእረፍት መልስ ባስቆጠራቸው ሁለት ጎሎች ማሸነፍ ችሏል፡

አስተያየት ይስጡ