በአለም አቀፉ የእግር ኳስ አስተዳዳሪ አካል (ፊፋ) የሚወጣው ወርሃዊው የሃገራት የእግር ኳስ ደረጃ ይፋ ሆኗል።
ኢትዮጵያም በወንዶች ባለፈው ወር ከነበረችበት ዘጠኝ ደረጃዎችን አሻሽላለች።
በዚህም ባለፈው ወር ከነበረችበት 112ኛ ደረጃ ወደ 103ኛ መምጣት ችላለች።
- ማሰታውቂያ -
የደረጃውን ሰንጠረዥ የደቡብ አሜሪካዎቹ አርጀንቲና እና ብራዚል ተከታትለው ይመሩታል።
አርጀንቲና 1ኛ ስትሆን ብራዚል እና ጀርመን ደግሞ ይከተላሉ።
ከአፍሪካ ግብጽ ቀዳሚ ስትሆን ሴኔጋል እና የወቅቱ የአፍሪካ ሻምፒዮን ካሜሩን ተከታዮቹን ደረጃዎች ይዘዋል።
በወሩ ካሜሩን 29 ደረጃዎችን በማሻሻል ቀዳሚ ስትሆን፥ ጋቦን 21፣ ቡርኪና ፋሶ 15 እንዲሁም ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኦፍ ኮንጎ ደግሞ በ12 ደረጃዎች ከፍተኛ መሻሻል አሳይተዋል።