የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ዋልያዎቹ በአሰልጣኝ ውበቱ አባተ እየተመሩ በዛሬው ዕለትም ልምምዳቸውን ሲሰሩ ለሁለተኛ ጊዜ በአዲስ አበባ ስታዲየም መስራታቸውን ለማወቅ ተችሏል ፡፡
በዛሬው ልምምድ ላይ አማኑኤል ዮሐንስ ካጋጠመው መጠናኛ ጉዳት በማገገም ዋናውን ቡድኑን በመቀላቀል ሙሉ ልምምድ ማድረጉ ሲታወቅ ከጥቂት ቀናት በፊት ጉዳት ያስተናገደው አጥቂው ሙጂብ ቃሲም ለብቻው ልምምድ እንዳደረገ ታውቋል ፡፡
ካለፈው ሳምንት ቅዳሜ በኋላ ለሁለተኛ ጊዜ ልምምዳቸውን በአዲስ አበባ ስታዲየም ያካሄዱት ዋልያዎቹ የእርስ በእርስ ግጥሚያዎቹ በዛሬው ዕለት ከነበሩ የልምምድ አይነቶች ሲሆን ጠንከር ያለ ልምምዳቸውን ቀጥለውበታል ፡፡
- ማሰታውቂያ -
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በመጪው አርብ ከሱዳን አቻቸው ጋር ለመጫወት በተደረገ የኢሜል ልውውጥ የተስማሙ ሲሆን ጨዋታው እንደሚካሄድ ይጠበቃል ፡፡