ተስፈኛው ሰመረ ሀፍታይ ስለ ሀገራዊው ጥሪ ይናገራል !

 

የዋልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርስቲ የመስመር ተጫዋች ሰመረ ሀፍታይ ለወጣቶች ዕድል መስጠት በማይታማው አሰልጣኝ ዮሐንስ ሳህሌ ስር ደምቀው መውጣት ከቻሉ ወጣት ተጫዎቾች መካከል ቀዳሚው ነው ።

ሰመረ ሀፍታይ በተለይም በብዙሀኑ የእግር ኳስ አፍቃሪ በሊጉ የመክፈቻ ጨዋታ በአመቱ ወደ ሊጉ ባደገው ሰበታ ከተማ ላይ ሀትሪክ በመስራት የውድድር ዓመቱን በስኬት መጀመር ችሎ ነበር ። ሰመረ በውድድር ዓመቱ ከ ፋሲል ከነማ ጋር በነበረው ጨዋታ ያጋጠመው ጉዳት ብቃቱን ዳግም እንዳንመለከተው አድርጎ ታይቷል ።

በአሰልጣኝ ተመስገን ዳና በሚመራው የኢትዮጵያ ከ 20 ዓመት በታች የብሔራዊ ቡድን ጥሪ የቀረበለት ሰመረ ሀፍታይ የተሰማውን ደስታ ይገልጻል ።

” በጣም ደስ ይላል አገርን ወክሎ መጫወት የብዙ ተጫዋች ምኞት ነው ፣ የእዚህ ዕድል ተካፋይ በመሆኑ ትልቅ ደስታ ፈጥሮብኛል ። ሀገሬን እንደምወክል በስልክ ተደውሎ ሲነገረኝ የተለየ ስሜት ፈጥሮብኛል ።

የቀረበልኝን ሀገራዊ ጥሪ ተቀብዬ ከፈጣሪ ጋር ሀገሬን የተሻለ ቦታ ለማስጠራት ጠንክሬ እሰራለው ” ሲል ለመጀመሪያ ጊዜ ከቀረበለት የብሔራዊ ቡድን ጥሪ በኋላ አስተያየቱን አካፍሎናል ።

Hatricksport website Editor

Twitter

kidus Yoftahe

Hatricksport website Editor