የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በታህሳስ ወር በሚጀመረው የምስራቅ እና መካከለኛው የአፍሪካ ዋንጫ ውድድር ተሳታፊ የሆነው የኢትዮጵያ ከ 17 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን የኢትዮጵያ መድን የቀድሞ ከ17 በታች እና የአሁን ከ 20 ዓመት በታች አሰልጣኝ እንድርያስ ብርሃኑን የቡድኑ ዋና አሰልጣኝ በማድረግ በአንድ አመት ውል አስፍርሟል።
አሰልጣኝ እንድርያስ ብርሃኑ የኢትዮጵያ መድን ከ17 ዓመት በታች ቡድን በ 2011 የተሻለ ተፎካካሪ እንዲሆን ማድረጋቸው ይታወሳል።
አሰልጣኙ በሴካፋ ውድድር የተሻለ እና ተፎካካሪ ብሔራዊ ቡድን እንዲሰሩ ግዴታ ውስጥ ገብተዋል ።
አስተያየት ይስጡ