ከ 20 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን የኮቪድ ውጤት !

 

ከመጪው ህዳር 13 እስከ 27 ድረስ በታንዛኒያ አስተናጋጅነት በሚካሄደው የሴካፋ ከ 20 ዓመት በታች ቡድን የሚሳተፈው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በትላንትናው ዕለት ለ 30 ተጫዋቾች ጥሪ ማቅረቡ ይታወሳል ።

በብሉ ስካይ ሆቴል ማረፊያውን ያደረገው የ ኢትዮጵያ ከ 20 ዓመት በታች ቡድን የ ኮቪድ ምርመራ አስቀድመው በአዲስ አበባ ስታዲየም ማድረግ ሲችሉ ሁሉም የቡድኑ አባላት ከቫይረሱ ነፃ መሆናቸው ለማወቅ ተችሏል ።

ሀትሪክ ስፖርት ባገኘችው መረጃ ሁሉም ጥሪ የቀረበላቸው የቡድን አባላት በመልካም ጤንነት ላይ ሲገኙ ብሔራዊ ቡድኑ ከነገ ጀምሮ በአዲስ አበባ ስታዲየም በቀን ሁለቴ ልምምድ መስራት እንደሚጀምሩ ለማወቅ ተችሏል ።

Hatricksport website Editor

Twitter

kidus Yoftahe

Hatricksport website Editor