ምዝገባው ከሰኔ 25 ጀምሮ ድረስ ሲከናወን የቆየ ሲሆን በዛሬው ዕለት ምዝገባ ይጠናቀቃል።
በቀነ ገደቡ ምዝገባ ያላጠናቀቁ ክለቦች በከፍተኛ የገንዘብ ቅጣት ለሦስት ቀናት የሚስተናገዱ ሲሆን በየቀኑ የገንዘብ ቅጣቱ እያደገ ይሄዳል።
ክለቦች ምዝገባቸውን እንዳጠናቀቁ በፕላትፎርሙ ያስገቡት መረጃን በክለብ ላይሰንሲንግ የተቋቋመው የፍትህ አካል (FIB) ከተመለከተ በኋላ ውሳኔ የሚያሳልፍ ሲሆን ሒደቱም እስከ ረቡዕ ሐምሌ 17 ድረስ ይቆያል።
በFIB ውሳኔ ቅሬታ ያላቸው ክለቦች በክለብ ላይሰንሲንግ ለተቋቋመው ይግባኝ ሰሚ አካል (AB) የማቅረብ መብታቸው የተጠበቀ ነው።
- ማሰታውቂያ -
ሙሉ ለሙሉ ምዝገባ ያጠናቀቁ ክለቦች
1 ቅዱስ ጊዮርጊስ
2 ኢትዮጵያ መድን
3 መቐለ 70 እንደርታ
4 ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ
5 ስሑል ሽረ
6 ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
7 ሲዳማ ቡና
8 ወላይታ ድቻ
9 ባሕር ዳር ከተማ
10 ፋሲል ከነማ
በከፊል ያጠናቀቁ
1 ወልቂጤ ከተማ
2 ኢትዮ ኤሌክትሪክ
3 ሀዲያ ሆሳዕና
4 ሀዋሳ ከተማ
5 ኢትዮጵያ ቡና
6 መቻል
7 ድሬዳዋ ከተማ
8 አዳማ ከተማ
የምዝገባ ሒደት ያልጀመረ
1 አርባምንጭ ከተማ