ሁለቱ የፕሪሚየር ሊግ ክለቦች በዛሬዉ ዕለት የአቋም መፈተሻ ጨዋታ የሚያደርጉ ይሆናል !!

የቅድመ ዉድድር ዝግጅታቸውን በሀዋሳ ከተማ እያደረጉ የሚገኙት ሁለቱ የሊጉ ክለቦች ማለትም ድሬዳዋ ከተማ እና ሀዋሳ ከተማ በዛሬዉ ዕለት ከተለያዩ ክለቦች ከተሰባሰቡ ተጫዋቾች (ከስብስብ) ጋር የአቋም መፈተሻ ጨዋታቸዉን እንደሚያደርጉ ታዉቋል።

ከነሀሴ 21 ጀምሮ በቀን ሁለት ጊዜ ዝግጅቱን እያደረገ የሚገኘዉ ድሬዳዋ ከተማ ለአዲስ አመት ከተሰጣቸዉ ከእረፍት ቀናት መልስ መደበኛ ልምምዳቸውን አጠናክረው የቀጠሉ ሲሆን በዛሬዉ ዕለት ደግሞ የዝግጅቱ አንድ አካል የሆነዉን የአቋም መፈተሻ ጨዋታ በሀዋሳ ከተማ ከሚገኙ የተለያዩ የክለብ ተጫዋቾች (ስብሰብ) ጋር ረፋድ 4:00 ላይ የሚያደርጉ ይሆናል።

በተጨማሪም በአሰልጣኝ ዘርዓይ ሙሉ የሚመራዉ ሀዋሳ ከተማም በዛሬዉ ዕለት ከሰዓት 9:00 ላይ በሀዋሳ አርቲፊሻል ሜዳ በተመሳሳይ ከተለያዩ ክለቦች ከተሰባሰቡ ተጨዋቾች ጋር የአቋም መፈተሻ ጨዋታቸውን የሚያደርጉም ይሆናል።

በተያያዘም ሁለቱም ክለቦች በቀጣዩ ሳምት በሀዋሳ ከተማ የሚጀምረው እና ስያሜዉን ወደ የሲዳማ ካፕ የቀየረዉ ዉድድር ላይ ተሳታፊ መሆናቸዉ ይታወቃል።

Writer at Hatricksport

Facebook

Ermias Misganaw

Writer at Hatricksport