ትልቅ ራዕይን የሰነቀዉ ስፖርት ለሰላም በአዲስ አበባ ማህበር አሁንም በበጎ ስራዎቹ ቀጥሏል !!

ስፖርት ለሰላም ፣ ለወንድማማችነት ፣ ለጋራ ዕድገት በሚል ሀሳብ የአገራቸዉ ሊግ ላይ ይንፀባረቁ የነበሩትን ኢ-ስፖርታዊ ድርጊቶች ለማስቀረት ከኢትዮጵያ ቡና እና ከቅዱስ ጊዮርጊስ ደጋፊዎች ጋር በጋራ በመሆን አንድ ብለዉ ያቋቋሙት ማህበር ዛሬ ላይ ዘርፈ ቡዙ ስራዎችን ማከናወናቸውን ቀጥለዋል።

‘ስፖርት ለሰላም’ መስራት ከሚገባው በላይ ስራውን ደፍሮ ሰርቶ የቆመ ማህበር ሁልጊዜም አዲስ ነን ብሎ አይዘናጋም የሚሉት አባላቱ ከዚህ ቀደም የተለያዩ በጎ ስራዎችን መከናወናቸው ይታወሳል። ከነዚህ መካከልም:-

ከአዲስ አበባ ስፖርት ኮሚሽን ጋር በጋራ በመሆን የጎዳና ላይ ማስ ስፖርት እንዲሁም በዓይነቱ ልዩ የሆነ ”ሸገር ደርቢ በመስቀል አደባባይ” የሚል መሪ ቃል ያለውን እና በአህጉራችን አፍሪካ በቀዳሚነቱ ሪከርድ የያዘውን ታላቅ ማስ ስፖርት ያለምንም እንከን ደረጃውን እና ጥራቱን እንዲጠብቅ አድርገው በማዘጋጀት በሁለቱ ደጋፊዎች መሃከል የነበረውን ክፍተት ማቀራረብ መቻላቸው ይታወሳል።

ድሬዳዋ ላይ በጎርፍ የተጎዱ ወገኖቻቸውን ከአዲስ አበባ ስፖርት ኮሚሽን ጋር በመተባበር ስፍራዉ ድረስ ተጉዘዉ የተወሰኑ ቤቶችን ጠግነዉ ስፖርት ለሰላምን በድሬ መስርተው መመለሳቸዉም አይዘነጋም።

በተጨማሪም ‘ስፖርት ለሰላም’ አገራዊ ጥሪዎች አረንጓዴ አሻራን በመደገፍ ብቻ ሳይገቱ በተከታታይ በመሳተፍ ጉልህ ድርሻንም ተወጥተዋል። ‘ደሜን ለወገኔ’ በሚል አዲስ አበባ ስፖርት ኮሚሽን ባዘጋጀው መርሃ ግብር ላይም ተሳትፈዋል። በኮቪድ ምክንያት የእለት ጉርሳቸውን ያጡ ወገኖችንም በአዲስ አበባ ስታዲየም በመመገብ የወገን አልኝታነታቸዉን በተግባር ማሳየታቸዉ አይዘነጋም።

አሁን ደግሞ የኢትዮጲያ ስፖርት ለሰላም ማህበር በአዲስ አበባ ቃሊቲ ማረሚያ ቤት ለሚገኙ የህግ ታራሚዎች ግምቱ ከ25,000ብር በላይ የሚሆን የፅዳት ዕቃና አልባሳትን በስፍራው በመገኘት አስረክበዋል።

ይኽ ጅማሬያቸዉ እንጅ ከዚህ በተሻለ መልካም ራዕይ ያለው ማህበር እንዲሆን እና በቀጣይ ጠንካራ ተሳትፎው ለትውልዱ የሚበጅ ጥሩ መልዕክት ለማስተላለፍ የተዘጋጀ ከክልል ስፖርት ቤተሰብ ጋር በጋራ በመሆን ወንድማማችነት በመፍጠር እግር ኳሱ የሰላም መድረክ እንዲሆን በፅኑ የሚመኝ ማህበር መሆኑንም አባላቱ በአፅንኦት ይናገራሉ።

Writer at Hatricksport

Facebook

Ermias Misganaw

Writer at Hatricksport

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *