ሁለት ኢንተርናሽናል ዳኞች ወደቁ

– በሁለቱም ጾታዎች ተተኪዎቹ ነገ ይታወቃሉ

በየአመቱ የሚካሄደውና በኢንተርናሽናል ደረጃ ኢትዮጵያን የሚወክሉ ዳኞችን ለመምረጥ በተካሄደው ኩፐር ቴስት ሁለት ዳኞች ወደቁ።

ዛሬ በአዲስ አበባ ስታዲየም በተሰጠው ኩፐርቴስት በወንዶች ኢንተርናሽናል አርቢትር ብሩክ የማነብርሃንና በሴቶች ኢንተርናሽናል አርቢትር አስናቀች ገብሬ ኩፐርቴስቱን ሳያልፉ ቀርተዋል።

በተለይ አርቢትር አስናቀች በኬኔያ በተካሄደው የሴካፋ የክለቦች ሻምፒዮና ላይ ጨዋታዎችን መርታ ከተመለሰች ከቀናት በኋላ በተካሄደ ኩፐርቴስት መውደቋ አነጋጋሪ ሆኗል።
በወንዶች ከአርቢትር ብሩክ ውጪ ኢንተርናሽናል አርቢትር የሆነው አማኑኤል ሃይለስላሴም ኩፐርቴስቱን ባለመካፈሉ ከኢንተርናሽናል ባጅ ውጪ መሆኑም ተረጋግጧል።

በኢንተርናሽናል ደረጃ በወንዶቹ ሰባት በሴቶቹ አራት ሲሆን ኮታውን ለመሙላት በወንዶች ሁለት በሴቶች አንድ ተተኪ ዳኛ ነገ በሚደረገው የፌዴራል አርቢትሮች ኩፐርቴስት ተተኪዎቹና ተስፋ የሚጣልባቸው አራቱ ዳኞች ይተካሉ ተብሎ ይጠበቃል።

Editor at Hatricksport

Facebook

ዮሴፍ ከፈለኝ

Editor at Hatricksport

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *