ለሁለት ኢንተርናሽናል ኮታ 7 ኤሊት አርቢትሮች ተፋጠዋል

በ2022 በኢንተርናሽናል ዳኝነት ለመስጠት ባለው ሁለት ኮታ ላይ ለመግባት የሚደረገው ፍልሚያ አጓጊ ሆኗል።

ትላንት በተካሄደው ኩፐር ቴስት ኢንተርናሽናል አርቢትር ብሩክ የማነብርሃን በመውደቁ ኢንተርናሽናል አርቢትር አማኑኤል ሃ/ስላሴ ደግሞ ባለመፈተኑ በሁለቱ ቦታ ለመግባት ፌዴራል አርቢትር ተካልኝ ለማ፣ ፌዴራል አርቢትር ዳንኤል ግርማይ፣ፌዴራል አርቢትር ባህሩ ተካ ፤ ፌዴራል አርቢትር አሸብር ሰቦቃ፣ ፌዴራል አርቢትር ተፈሪ አለባቸው፣ ፌዴራል አርቢትር ቢኒያም ወ/አገኘሁና ፌዴራል አርቢትር ማኑኤ ወ/ጻዲቅ ተፋጠዋል።

ብሄራዊ የዳኞች ኮሚቴ አባላት ፊፋ ባስቀመጠው መመዘኛ መሠረት ምንም አይነት የቅርበትና የብሄረተኝነት ጫና ውስጥ ሳይወድቁ ተገቢ ባለሙያ የመመደብ ሃላፊነት ተጥሎባቸዋል በተለይ ፊፋ ባስቀመጠው የእድሜ እርከን ላይ ጥንቃቄ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል።

በፊት የነበረው ኮሚቴ አምና ለኢንተርናሽናል ረዳት ዳኝነት በላቸው ይታየውን ልኮ ከእድሜ ጋር ተያይዞ ፊፋ ውድቅ በማድረግ ኮታውን መቀነሱን በማስታወስ የሚላኩት ዳኞች ብቃት ብቻ ሳይሆን እድሜ ላይ ጥንቃቄ ማድረግ ይጠበቃል። እነልኡል ሰገድ በጋሻውና ግዛቴ አለሙ የመሰሉ ባለሙያዎቾ ከተመሳሳይ ስህተት ኮሚቴውን ይታደጉታል ተብሎ ይጠበቃል።

ፊፋ እድሜን በተመለከተ ለነባር አርቢትር ከ45 አመት የማይበልጥ ለእጩ አርቢትሮች ደግሞ ከ25 አመት ያላነሰ ከ38 አመት ያልበለጠ የሚል በመሆኑ ኮታው እንዳይቀነስ ትኩረት የሚያሻው ሆኗል።

Editor at Hatricksport

Facebook

ዮሴፍ ከፈለኝ

Editor at Hatricksport