የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ከብሔራዊ ቡድን ጨዋታዎች መልስ በዛሬው ዕለት በአራተኛ ሳምንት ቀዳሚ ጨዋታዎች ወደ ውድድር ይመለሳል።
በድሬዳዋ ስታዲየም በሚቀጥለው የሊጉ ውድድር የግርማ ታደሰው ሀድያ ሆሳዕና ከዘርዓይ ሙሉው ሀዋሳ ከተማ ጋር ጨዋታውን ያደርጋል።
በውድድር ዓመቱ የመጀመሪያ ጨዋታ መቀሌ 70 እንደርታን በማሸነፍ የጀመረው ሀድያ ሆሳዕና በሁለተኛው ሳምንት አራፊ የነበረ ሲሆን ፤ በሶስተኛው ሳምንት በባህርዳር ከተማ የ2 – 0 ሽንፈት አስተናግዷል።
ሀዋሳ ከተማ በበኩሉ በቀዳሚው ጨዋታ በሮዱዋ ደርቢ ሲዳማ ቡናን አሸንፎ ፤ በሁለተኛ ሳምንት ከስሁል ሽረ ጋር በተጨማሪ ደቂቃ በተቆጠረ ግብ ነጥብ ተጋርቷል። ቡድኑ በሶስተኛው ሳምንት የዓመቱን የመጀመሪያ ሽንፈቱን በኢትዮጵያ ቡና በ3 – 1 ውጤት አስተናግዷል።
- ማሰታውቂያ -
ሀድያ ሆሳዕና
ባለፉት ሶስት ተከታታይ ዓመታት የአራተኛ ሳምንት ጨዋታዎች 0 – 0 በሆነ ውጤት ጨዋታዎቹን አጠናቋል
አምና በተመሳሳይ በመጀመሪያው ዙር ባህርዳር ከተማን ከገጠመ በኋላ ነበር ሀዋሳ ከተማ የገጠመው
አሰልጣኝ ግርማ ታደሰ ሀድያ ሆሳዕናን አምና ከዮሐንስ ሳህሌ ከተረከቁ በኋላ በሁሉም ውድድሮች 30ኛ ጨዋታቸው ነው
በጨዋታው የሚያስቆጥሩት ቀዳሚ ግብ በአሰልጣኝ ግርማ ታደሰ ስር የተቆጠረ 30ኛ የክለቡ የሊግ ግብ ይሆናል
ባሳለፍነው ዓመት የአራተኛ ሳምንት ጨዋታ ከሀምበሪቾ ዱራሜ ጋር ያለ ግብ ተለያይተዋል
ካለፉት አስር የሊጉ ጨዋታዎች በአንዱ ጨዋታ ብቻ ነው ግብ ያልተቆጠረባቸው
ቡድኑ ከአንድ የግብ ልዩነት በላይ የተሸነፈው(በባህርዳር ከተማ 2 – 0) ከ2015 የ29ኛ ሳምንት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው
ካለፉት ሁለት የ2 – 0 ሽንፈቶቻቸው በኋላ ባደረጓቸው ጨዋታዎች አሸንፈዋል
ባሳለፍነው የውድድር ዘመን በቅዳሜ ቀን ባደረጋቸው ጨዋታዎች በአንዱም አላሸነፈም
ሀዋሳ ከተማ
በሶስቱም ጨዋታዎች የተለያየ ውጤት ያስመዘገበው ሁለተኛው የሊጉ ቡድን ነው(ሌላኛው መቀሌ 70 እንደርታ)
በአሰልጣኝ ዘርዓይ ሙሉ ስር ያለፉት ሶስት የውድድር ዘመናት እና የዘንድሮው ከሶስት ጨዋታዎች በኋላ የተመዘገቡ ነጥቦች
2014 – 6
2015 – 3
2016 – 5
2017 – 4
ካለፉት ስድስት የውድድር ዘመናት የአራተኛ ሳምንት ጨዋታዎች ማሸነፍ የቻለው በአንዱ ብቻ ነው(በ2015 ወልቂጤ ከተማን 4 – 3)
ቡድኑ ባሳለፍነው የውድድር ዘመን ካደረጋቸው ሰባት የቅዳሜ ቀን ጨዋታዎች ያነሸነፈው በአንድ ብቻ ነው
ባሳለፍነው የውድድር ዘመን በአራተኛ ሳምንት ከኢትዮጵያ መድኅን ነጥብ ተጋርቷል
ካለፉት 25 የሊግ ጨዋታዎች በአንዱ ብቻ ነው ግብ ያላስቆጠረው
ከኢትዮጵያ ቡናው የ3 – 1 ሽንፈት በፊት ለመጨረሻ ጊዜ በተመሳሳይ ውጤት የተሸነፈው በ2014 25ኛ ሳምንት በተመሳሳይ በኢትዮጵያ ቡና ነበር
ቡድኑ አዳማ ከተማን ከመግጠሙ በፊት ባደረጋቸው ጨዋታዎች ለመጨረሻ ጊዜ የተሸነፈው በ2007 የውድድር ዘመን ነበር
አዳማ ከተማን ከመግጠሙ በፊት ባደረጋቸው ያለፉት 16 ጨዋታዎች በ9 አሸንፎ በ7 አቻ ተለያይቷል
እርስ በርስ
ሁለቱ ቡድኖች በሊጉ ለ12ኛ ጊዜ የሚያደጉት ጨዋታ ነው
ሀዋሳ ከተማ በሶስቱ ሲያሸንፍ በሰባት አቻ ተለያይተዋል በአንዱ ብቻ ሀድያ ሆሳዕና አሸንፏል
በነዚህ ጨዋታዎች ሀዋሳ ከተማ 16 ግቦችን ሀድያ ሆሳዕና ደግሞ 13 ግቦችን አስቆጥረዋል
የሀድያ ሆሳዕና ብቸኛ ድል በ2014 የውድድር ዘመን ሁለተኛ ዙር ላይ ነበር(ሀድያ ሆሳዕና 3 – 1 ሀዋሳ ከተማ)
በመጨረሻው ግንኙነታቸው ሀዋሳ ከተማ 2 – 1 ሲያሸንፍ እስራኤል እሸቱ እና ዓሊ ሱሌማን ለሀዋሳ ከተማ እንዲሁም ዳዋ ሆቴሳ ለሀድያ ሆሳዕና ኳስ እና መረብን አገናኝተዋል