ኢትዮጲያ መድን አሰልጣኝ ጸጋዬ ወንድሙ (አግሮን) ሾሟል፡፡

 

ከ34 በላይ አሠልጣኞች የተመኙትን የኢትዮጲያ መድን የአሰልጣኝነትን ቦታ የቀድሞ የክለቡ ም/ል አሰልጣኝ ጸጋዬ ወንድሙ (አግሮ) አግኝቶታል፡፡

የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማና የመከላከያ ሴት ቡድንን ያሰለጠነው አሰልጣኝ ጸጋዬ ወንድሙ የቀድሞ የክለቡ አሰልጣኝ አባይነህ ካሴ ምክትል ሆኖ አሰልጥኗል፡፡ በከፍተኛ ሊግ የሚወዳደረውን ክለቡን ወደ ፕሪሚየር ሊግ የማሳደግ ሀላፊነት ተጥሎበታል፡፡

የክለቡ ፕሬዝዳንት አቶ ተምትም አሠልጣኙን አውቀናል ነገር ግን የምናሳውቀው ሀሙስ ከምናደርገው ስብሰባ በኋላ ነው ቢሉም ከታማኝ ምንጭ ባገኘሁት መረጃ አሰልጣኝ ጸጋዬ ሃላፊነቱ እንደተሰጠውና በቅርቡ ስራውን እንደሚጀምር ተረጋግጧል፡፡

Editor at Hatricksport

Facebook

ዮሴፍ ከፈለኝ

Editor at Hatricksport