ለሙያው የስፖርት ቤተሰቡና አጠቃላይ ህብረተሰቡ ከፍተኛ ሙያዊ ድጋፍ ያደረገው የፊዚዮቴራፒስቱ ይስሃቅ የምስጋና ፕሮግራም የፊታችን ግንቦት 29 /2016 በሆሊዴይ ሆቴል እንደሚካሄድ ተገለጸ።
ከመርሃግበሩ አዘጋጅ ኮሚቴ የተገኘ መረጃ እንደሚያስረዳው በገቢ ማሰባሰቢያው ላይ ተሳትፎ ያደረጉ ወደ 250 የሚጠጉ ሰዎች የሚጋበዙ ሲሆን ሌሎች መርሃግብሮች እንደሚኖረው ታውቋል። በመላው ኢትዮጵያ ተጀምሮ መላው አለምን ያዳረሰው የድጋፍና የምስጋና ርብርቡ ስኬታማ መሆኑ ታውቋል።
በፊዚዮቴራፒስቱ ይስሃቅ በሙያው በእጂ ያልተዳሰሰ ተጨዋች የሌለ ሲሆን ጉዳት ደርሶባቸው በእሱ ተፈወስን የሚሉ ሶፖርተኞች ቁጥር በጣም ብዙ ነው አሁንም የሁሉም ክለቦች ተጨዋቾች በጋራ የሚያመሰግኑት በእግርኳሱ በአጠቃላይ በስፖርቱ ማህበረሰብ ስመ ጥር የሆነ ባለሙ ያ ነው ። የአካባቢውን ሰው በነጻ እያከመ ላለው ፊዚዮቴራፒስቱ የተዘጋጀው የምስጋና ፕሮግራም የስፖርት ቤተሰቡ ዘንድ ትልቅ ተቀባይነት ያገኘ ሆኗል።