መነሻ ገጽ Uncategorized የ2009 ዓ.ም የኮኮቦች ሽልማት ዓለም አቀፍ እና አህጉር አቀፍ ደረጃውን በጠበቀ መልኩ ለማካሄድ ተወሰነ
Uncategorized

የ2009 ዓ.ም የኮኮቦች ሽልማት ዓለም አቀፍ እና አህጉር አቀፍ ደረጃውን በጠበቀ መልኩ ለማካሄድ ተወሰነ

አጋራ
አጋራ

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ለበርካታ ዓመታት በተለያዩ ዲቪዚዮኖች ውድድሮችን እያካሄደ ሲሆን በ2009 ዓ.ም ቀደም ሲል ከነበሩት ውድድሮች ቁጥራቸውን በመጨመር የስድስት ሊጐች ውድድሮች በማደራጀትና ሂደቶቻቸው ደረጃቸውን በጠበቀ መልኩ እንዲከናወኑ የበኩሉን አስተዋጽኦ በማድረጉ በበጀት ዓመቱ እየተካሄዱ የሚገኙት ውድድሮች በመጠናቀቅ ላይ ይገኛሉ፡፡

በእነዚህ ውድድሮች አሸናፊና ኮከብ ለሆኑ ተወዳዳሪዎች ፣ አሠልጣኞች ፣ ዳኞች የዋንጫ እና የሜዳሊያ ሽልማት እንዲሁም የገንዘብ ሽልማት አሰጣጥ ስነ-ስርዓቶችን ለማከናወን ዝግጅቱን የተለያዩ ድርጅቶች ስፖንሰር እንዲያደርጉ በማድረግ የገንዘብ ማሰባሰብ ሥራ እየተሰራ ነው፡፡

ይህንኑ በተመለከተ በ2009 ዓ.ም እየተካሄዱ በሚገኙት ውድድሮች የኮኮቦችን ሽልማት በውድድሩ ፍፃሜ ከመስጠት ይልቅ በተሻለ ሥነ-ሥርዓት ማከናወን አስፈልጓል፡፡

ስለዚህ፣ 

1ኛ. እንደ ዓለም አቀፍና አህጉር አቀፍ ፌዴሬሽኖች ራሱን በቻለ ዝግጅት በደመቀና ባማረ ሁኔታ ደረጃውን በጠበቀ ሆቴል እንዲሆን ፣

2ኛ.  በተለያዩ ሊጎች ኮከብ የሆኑ ሁሉ በተናጠል ሳይሆን በአንድነት ተሰብስበው በአንድ ቦታ እንዲሸለሙ ለማድረግ ፣

3ኛ. የሚሰጠውን የገንዘብ ሽልማት መጠን ካለፉት ዓመታት በተሻለ መልኩ ከፍ ለማድረግ፣

4ኛ. የገንዘብ ሽልማት ለማበርከት የሚችሉ ድርጅቶችን በበለጠ ሁኔታ ከኮከብ ተሸላሚዎች ጋር ለማቀራረብና ቀጣይነት ያለው ድጋፍ እንዲያገኙ ለማስቻል፤ ይህንኑ በተማለከት ወደፊት ተወስኖ በሚገለጽ ቀንና ቦታ የሽልማት ሥነ-ስርዓት ይደረጋል፡፡

የዋንጫና የሜዳሊያ ሽልማቶን በተመለከተ በጨዋታው ፍፃሜ ላይ የሚሰጥ መሆኑን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ገልጿል፡፡ 

 

 

 

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን

 

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
Uncategorized

ቅዱስ ጊዮርጊስ የመቶ ሚሊዮን ብር ድጋፍ ተደረገለት

ዛሬ አንጋፋውን የቅዱስ ጊዮርጊስ የስፓርት ማህበር ከገጠመው የመፍረስ አደጋ ለመታደግ የተለያዩ አካላትን...

Uncategorized

ለዋልያዎቹ መጫወትን የሚመኘው የሴሪ ኣው ክለብ ተጫዋች ማነው ?

የጣሊያን ሴሪ ኣው ክለብ ቶሪኖ ንብረት ስለሆነው አስደናቂው የአጥቂ አማካይ ተጫዋች እንንገራችሁ።...

Uncategorized

ቡናማዎቹ ተጫዋች ለማስፈረም ተስማሙ !

  በዛሬው ዕለት ግብ ጠባቂ በማስፈረም ወደ ዝውውሩ የገቡት ኢትዮጵያ ቡናማዎች ዘካሪያስ...