የኢትዮጵያ የሴቶች ፕሪምየር ሊግ ውድድር በዛሬው እለት ፍጻሜውን አግኝቷል።በዛሬው የፍጻሜ ውድድር ላይ በሴቶች ፕሪምየርሊግ ውድድር ሀያላን የሆኑት ደደቢት እና የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ተጫውተው በደደቢት 2ለ0 አሸናፊነት ተጠናቋል።
በዚህም ደደቢት የ2009 የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ አጠቃላይ አሸናፊ መሆን ችሏል።
በደደቢት የተረታው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ውድድሩን በሁለተኝነት ማጠናቀቅ ችሏል።ለደረጃ በተደረገ ጨዋታ ደግሞ አ በአዳማ ከተማ 2ለ0 አሸናፊነት የተጠናቀቀ ሲሆን፥ አዳማ ከተማም የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየርሊግን በሶስተኝነት ማጠናቀቅ ችሏል።
አስተያየት ይስጡ