በመቐለና መከላከያ ሚካሄድቱን 27ኛ ሳምንት ጨዋታዎችን በዳሰሳ ኣምዳችን እንመለከታለን ።
መቐለ ከ መከላከያ
መቐለ ለዋንጫ የሚያደርገውን ግስጋሴ ለማስቀጠል መከላከያም ከወራጅ ቀጠናው የበለጠ ለመራቅ ሚይደርጉት ጨዋታ በጉጉት ይጠበቃል።ካለፋት ሁለት ጨዋታዎች ማግኘት ከነበረበት 6 ነጥብ 1 ነጥብ ብቻ ያሳካው መቐለ ከላይ ያሉትን የዋንጫ ተፎካካሪ ቡድኖች ላይ ጫና ለመፍጠር የግድ ሥስት ነጥብ ማሳካት ይጠበቅባቸዋል።መከላከያዎችም 14ኛ ደረጃ ላይ ከተቀመጠው ኤሌክትሪክ ያላቸውን የ 4 ነጥብ ልዩነት ለማስጠበቅ ወይም ለማስፋት ጥንቃቄ መሰረት ያረገ ጨዋታ ሊጫወቱ እንደሚችሉ ይጠበቃል።
በ 4-2-3-1 የጨዋታ ስልት ሚታወቁት መቐለ ሜዳውን በመለጠጥ ከመስመር ከሚነሱ ኳሶች እንዲሁም ተጋጣሚ ቡድን ኳስ በሚይዝበት ግዜ በፈጣን መልሶ ማጥቃት የግብ ዕድሎችን ይፈጥራሉ።በተለይም በ 2ኛው ዙር መሃል ክፍላቸው ላይ የፈጠሩት ጥምረት ቡድኑ ተገማች እንዳይሆንና ብዙ ዕድል እንዲፈጥር ኣድርጎታል።መከላከያም ስዩም ከበደን በኣሰልጣኝነት ከቀጠሩ በኃላ መሻሻልን ኣሳይተዋል በተለይም ከሜዳቸው ውጪ ሃዋሳን ፋሲልን ማሸነፋቸው በድኑ ከሜዳው ወጥቶ ማሸነፍ እንደሚችል ማሳያ ናቸው።ከመቐለ ተመሳሳይ የጨዋታ ስልት ሚጠቀሙት መከላከያ ኣማካያቸው ዳዊት እስጢፋኖስ በቅጣት ማጣታቸው መሃል ሜዳቸውን ሊያሳሳው ይችላል።መከላከያዎች ፊት ላይ ፍፁም ሳሚኤል እና ምንይሉ ሚፈጥሩት ጥምረት ለጎል ምንጮቻቸው ናቸው።መሃል ላይ ብሃይሉ ሚየደርጋቸው እንቅስቃሴም ለቡድኑ የማጥቃት ሽግግር ወሳን ናቸው።
በመቐለዎች በኩል ከጋናዊው ኣጥቂ ቢስማርክ ውጪ ይህ ነው ሚባል የተጫዋች ጉዳት የለባቸውም።መከላከያዎች በቅጣት ምክንያት ተከላካዩ ኣዲሱ ተስፋዬ እና ኣማካዩ ዳዊት መጠቀም ኣይችሉም።
አስተያየት ይስጡ