በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 27ኛ ሳምንት ዛሬ 4ጨዋታዎች የተደረጉ ሲሆን መሪዎቹ ጅማ አባጅፋር እና ቅዱስ ጊዮርጊስ ተጋጣሚዎቻቸውን በማሸነፍ ወደ ዋንጫው የሚያደርጉትን ጉዞ አጠናክረው ቀጥለዋል።
በቅድሚያ ከረፋዱ 4:00 ሲል የሊጉ ግርጌ ላይ የሚገኘው ወልድያ ስፖርት ክለብ እና የሊጉ መሪ ጅማ አባጅፋር አ/አ ስታዲየም ላይ ተገናኝተው ጨዋታው በጅማ አባጅፋር 2-0 አሸናፊነት ተጠናቋል።
ለጅማ አባጅፋርም ግቦቹን የሊጉ ኮከብ ግብ አግቢ እና የክለቡ ዋነኛ አጥቂ ኦኪኪ አፎላቢ በፍፁም ቅጣት ምት እንዲሁም አሮን አሞሀ በጨዋታ ማስቆጠር ችለዋል። በዚህም ጅማ አባጅፋር መሪነቱን ማስቀጠል ችሏል።ወልዲያ ከተማ መሸነፉን ተከትሎ ከፍተኛ ሊጉን ከሚቀላቀሉ ሶስቱ ቡድኖች ውስጥ አንዱ መሆኑ ተጋግጧል።
- ማሰታውቂያ -
በተመሳሳይ 4:00 ሲል ጎንደር ፋሲለደስ ስታዲየም ላይ የተገናኙት ፋሲል ከተማ እና ሲዳማ ቡና ሲሆኑ ጨዋታውም በባለሜዳዎቹ ፋሲል ከተማዎች 2-1 አሸናፊነት መጠናቀቅ ችሏል። በጨዋታው የግብ ማግባት ቅድሚያውን መውሰድ የቻሉት ሲዳማ ቡናዎች ሲሆኑ 15ኛው ደቂቃ ላይ ሐብታሙ ገዛኸኝ አስቆጥሮ መሪ ቢያደርጋቸውም መሪነታቸው ግን መዝለቅ የቻለው ለ14 ደቂቃዎች ብቻ ነበር። 29ኛው ደቂቃ ላይ በራምኬል ሎክ እንዲሁም ከ5 ደቂቃዎች በኋላ 34ኛው ደቂቃ ላይ ኤፍሬም አለሙ ግብ አስቆጥረው ከመመራት ተነስተው ማሸነፍ ችለዋል።
በሌላ የክልል ጨዋታ ወራጅ ቀጠና ውስጥ እየዳከሩ የሚገኙት ድሬዳዋ ከተማ እና ኢትዮ-ኤሌክትሪክ ተገናኝተው ጨዋታቸውን ያለግብ አጠናቀዋል።
በዚህም ሁለቱም ቡድኖች ከወራጅ ቀጠናው ለመውጣት ሳይችሉ ቀርተዋል። 10:00 ሲል አ/አ ላይ የተደረገው እና በጉጉት ተጠብቆ የነበረው የደደቢት እና የቅ/ጊዮርጊስ ጨዋታ በቅ/ጊዮርጊስ 3-0 በሆነ ሰፊ ውጤት አሸናፊነት ተጠናቋል። የሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ የመጀመሪያውን ግብ ለማስተናገድ የፈጀበት 4ደቂቃዎች ብቻ ነበር። 4ኛው ደቂቃ ላይ ተከላካዩ ሳላዲን በርጌቾ ግብ አስቆጥሮ ቀዳሚ ማድረግ ሲችል የመጀመሪያው አጋማሽ ሊጠናቀቅ 3 ደቂቃዎች ሲቀሩት 42ኛው ደቂቃ ላይ አማካዩ ሙሉዓለም መስፍን(ዴኮ) ሁለተኛ ግብ አስቆጥሮ በቅ/ጊዮርጊስ 2-0 መሪነት ወደ መልበሻ ቤት አምርተዋል። ከእረፍት መልስ ተቀይሮ የገባው ምንተስኖት አዳነ ሶስተኛ ግብ አስቆጥሮ ቡድኑን ጣፋጭ ድል እንዲያስመዘግብ አስችሎታል።
ውጤቶቹንም ተከትሎ ጅማ አባጅፋር በ48 ነጥቦች የሊጉ አናት ላይ ሲቀመጥ ቅ/ጊዮርጊስ በበኩሉ በተመሳሳይ 48ነጥቦች በ1 የግብ ክፍያ ተበልጦ 2ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል። ወራጅ ቀጠናው ላይ አርባምንጭ ከተማ በ27 ነጥቦች 15ኛ ደረጃ ላይ እንዲሁም ወልድያ ስፖርት ክለብ በ20 ነጥቦች የሊጉ ግርጌ ላይ ለመቀመጥ ተገዷል።
ደረጃ ሰንጠረዥ
[team_standings id=”6559″ title=”” number=”16″ columns=”p,gd,pts” show_team_logo=”1″ show_full_table_link=”1″ align=”right”]