የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር አመራርና ስነ-ስርዓት ኮሚቴ ሚያዝያ 16 2016 ዓ.ም ባደረገው ስብሰባ የተደረጉ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ግጥሚያ(ዎች)ከዳኞች እና ከታዛቢዎች የቀረቡለትን የዲሲፕሊን ሪፖርት ከመረመረ በኋላ ውሳኔዎችን አሳልፏል።
በሳምንቱ መርሃ ግብር በተደረጉ ስምንት መደበኛ እና አንድ የ19ኛ ሳምንት ተስተካካይ ጨዋታ ስድስት በመሸናነፍ ቀሪ ሶስቱ በአቻ ውጤት ሲጠናቀቁ 12 ጎሎች በ11 ተጫዋቾች ተቆጥረዋል። 45 ቢጫ ካርድ ለተጫዋቾችና ቡድን አመራሮች ሲሰጥ ሶስት ቀይ ካርድ ተመዝግቧል።
በሳምንቱ በተጫዋቾችና አሰልጣኝ ቡድን አባላት ላይ የተለያዩ የዲሲፕሊን ውሳኔዎች ተላልፏል። ወንድማገኝ ማዕረግ(ወልቂጤ ከተማ)፣ ፍቅሩ አለማየሁ(አዳማ ከተማ)፣ መናፍ ዐወል(ፋሲል ከነማ)፣ ቢኒያም ገነቱ(ወላይታ ድቻ) እና ዳንኤል ደምሴ(ወልቂጤ ከተማ) በሳምንቱ ጨዋታ አምስተኛ የጨዋታ ቢጫ ካርድ በመመልከታቸው ለፈፀሙት ጥፋት በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ መሰረት 1 ጨዋታ እንዲታገዱና በተጨማሪ የገንዘብ ቅጣት ብር 1500 /አንድ ሺ አምስት መቶ/ እንዲከፍሉ ተወስኗል።
ፍቅረየሱስ ተ/ብርሀን(ሲዳማ ቡና) ሁለተኛ ቢጫ ካርድ የሚያስጥ ጥፋት በመፈፀሙ በቀይ ካርድ ከጨዋታ ሜዳ የተወገደ ለፈፀመው ጥፋት በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ መሰረት 1 ጨዋታ እንዲታገድ፥ አጥናፉ ታደሰ(ሻሸመኔ ከተማ) ዳኛን አፀያፊ ስድብ በመሳድብ በቀይ ካርድ ከጨዋታ ሜዳ የተወገደ ሲሆን የቡድን አመራሩ ለፈፀሙት ጥፋት በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የውድድር ደንብ የውድድር ደንብ መሰረት 3 ጨዋታ እንዲታገዱና በተጨማሪ የገንዘብ ቅጣት ብር 10000 /አስር ሺ/ እንዲከፍሉ ፥ ፋሪስ አለው(ወልቂጤ ከተማ) ዳኛን አፀያፊ ስድብ በመሳድብ በቀይ ካርድ ከጨዋታ ሜዳ የተወገደ ለፈፀመው ጥፋት በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ መሰረት 3 ጨዋታ እንዲታገድ ና በተጨማሪ የገንዘብ ቅጣት ብር 3000 /ሶስት ሺ/ እንዲከፍል ተወስኗል።
- ማሰታውቂያ -
ሞሰስ ኦዶ /ቅዱስ ጊዮርጊስ-ተጫዋች/ የውሃ ፕላስቲክ ወደ ተጋጣሚ ቡድን ተጫዋቾች መቀመጫ ስለመወርወሩና አፀያፊ ስድብ ስለመሳደቡ ሪፖርት የቀረበበት ሲሆን ተጫዋቹ የውሃ ፕላስቲክ በመወርወሩ በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ መሰረት ብር 25 000 /ሃያ አምስት ሺህ /እንዲሁም አፀያፊ ስድብ በመሳደቡ 3/ሶስት ጨዋታ እንዲታገድና ብር 3 000 /ሶስት ሺህ / እንዲከፍል ፥ ግዛቸው ጌታቸው/ወላይታ ድቻ-ምክትል አሰልጣኝ/ የተጋጣሚን ቡድን ተጫዋች አጸያፊ ስድብ ስለመሳደባቸው ሪፖርት ቀርበባቸው ለፈፀሙት ጥፋት በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ መሠረት 6 /ስድስት/ ጨዋታ እንዲታገዱና ብር 5 000 /አምስት ሺህ/ እንዲከፍሉ እንዲሁም ጊት ጋትኩት(ሲዳማ ቡና) 10 ጨዋታዎች የቢጫ ማስጠንቅቂያ ካርድ የተመለከተ ለፈፀመው ጥፋት በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ መሰረት 2 ጨዋታ እንዲታገድና በተጨማሪ የገንዘብ ቅጣት ብር 2000 /ሁለት ሺህ/ እንዲከፍል ተወስኗል።