ሻሸመኔ ከተማ ከደመወዝ ክፍያ ጋር ተያይዞ ከቡድኑ ካምፕ የወጡትን 13 ተጨዋቾች ወደ ካሞፑ እንዲመለሱ አስጠነቀቀ።
ክለቡ በሰጠው ማሳሰቢያያ ከቡድኑ አባላት መሀል ምንተስኖት ከበደ ፣ አቤል ማሞ ፣ሀብታሙ ንጉሴ ፣ኢዮብ ገ/ማሪያም፣ አሸብር ውሮ ፣ ያሬድ ዳዊት ፣ቻላቸው መንበሩ፣ወጋየሁ ቡርቃ ፣ ሄኖክ ድልቢ ፣ አብዱልቃድር ናስር ፣ ያብሰራ ሙሉጌታ ፣ጌትነት ተስፋዬና አሸናፊ ጡሩነህ ቡድኑን እንዲቀላቀሉ ትእዛዝ ሰጥቷል።
በፕሪሚየር ሊጉ 23ኛ ሳምንት ከነገ በስቲያ ሃሙስ ከቀኑ 9 ሰዓት ከአዳማ ከተማ ጋር ጨዋታ ያለባቸው ሻሸመኔዎች በ21/8/2016 በላከው ደብዳቤ ተጨዋቾቹ በአስቸኳይ ወደ ቡድኑ ካምፕ ገብተው ለሀሙሱ ጨዋታ እንዲዘጋጁ ጠይቆ እስካሁን ባለመምጣታችሁ በክለቡ ላይ በሚፈጠረው ማንኛውም ችግር በህጉ መሰረት የሚመለከተው የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን እንዲያውቀው እያሳሰብን የጨዋታው ቀን ከመድረሱ አስቀድሞ ክለቡ ወዳዘጋጀው የመኖሪያ ካምፕ ተገኝታችሁ ከክለቡ ጋር እንድትነጋገሩ በጥብቅ እናሳስባለን” ሲል ማስጠንቀቂያ ሰጥቷል ።
በ14/8/16 እና በ16/6/2016 በተፈጠረው ችግር ዙሪያ ለመነጋነር ቀጠሮ ብንይዝም ፈቃደኛ ባለመሆን አልተገችሁም ሲል ለውይይት በሩ ክፍት መሆኑን ቢገልጽም አሰልጣኝ ዘማሪያም ወ/ጊዮርጊስ ለማስማማትና ደመወዛቸው እንዲከፈል ቢጥርም አለመሳካቱን የሚገልጹት ተጨዋቾቹ ክለቡ ያልከፈላቸው የ4 ወር ደመወዝ እንዳላቸው በመግለጽ የሚጠበቅበትን እንዲያደርግ ጠይቀዋል።