By using this site, you agree to the Privacy Policy and Terms of Use.
Accept
ሀትሪክ ስፖርት ኢትዮጵያሀትሪክ ስፖርት ኢትዮጵያ
  • መነሻ ገፅ
  • ዜናዎች
  • ፕሪሚየር ሊግ
    • ባህርዳር ከተማ
    • ወላይታ ዲቻ
    • ድሬዳዋ ከተማ
    • ፋሲል ከነማ
    • ሲዳማ ቡና
    • አዳማ ከተማ
    • ሀዋሳ ከተማ
    • ቅዱስ ጊዮርጊስ
    • ኢትዮጵያ ቡና
    • ጅማ አባጅፋር
    • ወልቂጤ ከተማ
    • ሰበታ ከተማ
    • ሀዲያ ሆሳዕና
  • ዋልያዎቹ
  • ውድድሮች
  • English Article
  • French Articles
  • ስለ እኛ
Reading: ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ነጥብ ሲጥል ፤ ሲዳማ ቡና ከተከታታይ ጨዋታዎች በኋላ ወደ ድል መጥቷል !!
Share
Notification Show More
Latest News
ኢትዮጵያ ቡና የፋይናስ ችግር እንገጠመው ተገለፀ
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ኢትዮጵያ ቡና ዜናዎች
“ኢትዮዽያ ቡናን ብትነኩ ከመቃብሬ ተነስቼ አጠፉቹሀለው” መቶ አለቃ ፍቃደ ማሞ
ኢትዮጵያ ቡና ዜናዎች የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ
ኢንተርናሽናል አርቢትር ማኑኤ ወ/ጻዲቅ ከአዳማ ተሰናበተ
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ዜናዎች የኢትዮጵያ እግርኳስ ዳኞች ማህበር
በረከት አማረ ወደ ቀደመ ክለቡ ሊመለስ ይችላል ?
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የዝውውር ዜናዎች ኢትዮጵያ ቡና ዜናዎች
አርባምንጭ ከተማ ሴኔጋላዊ አማካይ አስፈረመ
አርባምንጭ ከተማ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የዝውውር ዜናዎች ዜናዎች
Aa
ሀትሪክ ስፖርት ኢትዮጵያሀትሪክ ስፖርት ኢትዮጵያ
Aa
  • መነሻ ገፅ
  • ዜናዎች
  • ፕሪሚየር ሊግ
  • ዋልያዎቹ
  • ውድድሮች
  • English Article
  • French Articles
  • ስለ እኛ
  • መነሻ ገፅ
  • ዜናዎች
  • ፕሪሚየር ሊግ
    • ባህርዳር ከተማ
    • ወላይታ ዲቻ
    • ድሬዳዋ ከተማ
    • ፋሲል ከነማ
    • ሲዳማ ቡና
    • አዳማ ከተማ
    • ሀዋሳ ከተማ
    • ቅዱስ ጊዮርጊስ
    • ኢትዮጵያ ቡና
    • ጅማ አባጅፋር
    • ወልቂጤ ከተማ
    • ሰበታ ከተማ
    • ሀዲያ ሆሳዕና
  • ዋልያዎቹ
  • ውድድሮች
  • English Article
  • French Articles
  • ስለ እኛ
Have an existing account? Sign In
Follow US
  • Advertise
© 2023 Hatrick Spoert. Design by Tech-ethiopia.com All Rights Reserved.
ኢትዮጵያ ንግድ ባንክሲዳማ ቡናየጨዋታ ዘገባሻሸመኔ ከተማየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግዜናዎችድሬዳዋ ከተማ

ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ነጥብ ሲጥል ፤ ሲዳማ ቡና ከተከታታይ ጨዋታዎች በኋላ ወደ ድል መጥቷል !!

Ermias Misganaw
Ermias Misganaw 2 years ago
Share
SHARE

በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የአስራ ዘጠነኛ ሳምንት የመጨረሻ ዕለት የቀን 10:00 ሰዓት ጨዋታ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከድሬዳዋ ከተማ ጋር ጨዋታቸውን በአቻ ዉጤት አጠናቀዋል።

በተመጣጣኝ የሜዳ ላይ የጨዋታ ፉክክር በጀመረዉ የቀኑ መርሐግብር ሁለቱም ክለቦች የጨዋታዉን የበላይነት ለመውሰድ ሲጥሩ የተስተዋለ ቢሆንም ድሬዳዋ ከተማዎች ግን በሙከራ እና ጫና በመፍጠሩ ረገድ በንፅፅር የተሻሉ ሆነዉ ተስተዉለዋል። በዚህ ሂደት በጀመረዉ ጨዋታም ድሬዳዋዎች በ15ተኛዉ ደቂቃ ላይ መሪ መሆን የቻሉበትን ግብ አስቆጥረዋል። በዚህም ከመስመር በኩል መሐመድ አብዱልለጢፍ ያሻማዉን ኳስ ተከላካዩ ፈቱዱን መቆጣጠር ባለመቻሉ ምክንያት ኳሷን ያገኛት ቻርልስ ሙሰጌ ወደ ግብነት ቀይሮ ክለቡን መሪ ማድረግ ችሏል።

ገና በጊዜ መሪ መሆን የቻሉበትን ግብ ያስቆጠሩት ድሬዎች በድጋሚ መሪነታቸዉን ወደ ሁለት ከፍ ለማድረግ ተቃርበዉ ነበር ፤ በዚህም ግብ ጠባቂዉ ፍሬዉ ጌታሁን መሳሳቱን ተከትሎ የተገኘችዉን ኳስ አሜ መሐመድ ከኤፍሬም አሻሞ ጋር ተቀባብሎ ወደ ግብ ቢሞክርም ኳሷ ወጥታለች።

- ማሰታውቂያ -

እምብዛም ተደጋጋሚ የግብ ሙከራ ባላስመለከተን እና በአብዛኛዉ በሜዳዉ የመሐል ክፍል ላይ ትኩረት ያደረገን የተጨዋታ መንገድ ያስመለክቱን በነበሩት ሁለቱ ክለቦች ድሬዎች መሪ ከሆኑ ከደቂቃዎች በኋላ ዳግም በዘርዓይ ገ/ስላሴ አማካኝነት ተጨማሪ ግብ ለማስቆጠር ተቃርበዉ ሳይሳካላቸዉ ቀርቷል።

በአንፃሩ ሙሉ ለሙሉ ማለት በሚቻል መልኩ በተጋጣሚያቸው ቡድን ብልጫ የተወሰደባቸዉ ባንኮች በይበልጥ ረዣዥም ኳሶችን ወደ ፊት በመላክ የአቻነት ግብ ፍለጋ ላይ የነበሩ ሲሆን በመጨረሻም አሰልቺ ከነበረዉ ጥረታቸዉ በኋላ በ80ኛዉ ደቂቃ ላይ ግብ አስቆጥረዋል። በዚህም ኪቲካ ጀማ ያሻገራት ኳስ በግብ ዘቡ ስትመለስ ያገኛት ሲሞን ፒተር ኳሷን ወደ ግብነት በመቀየር ክለቡን አቻ አድርጎ ጨዋታው አንድ አቻ በሆነ ዉጤት ተጠናቋል።

* በአስራ ዘጠነኛዉ ሳምንት የመጨረሻ መርሐግብር ሲዳማ ቡና ከተከታታይ አራት ጨዋታዎች በኋላ ወሳኝ ድል አስመዝግበዋል።

በዋና ዳኛ ሄኖክ አበበ ፊሽካ ምሽት አንድ ሰዓት ሲል በጀመረዉ ጨዋታ ገና በመባቻዉ በ4ተኛዉ ደቂቃ ላይ ሲዳማ ቡናዎች መሪ መሆን ችለዋል። በዚህም ከግራ መስመር በኩል ማይክል ኪፖሩል ያሻማውን ኳስ የሻሸመኔዉ ተከላካይ ገዛኸኝ ደሳለኝ በራሱ መረብ ላይ አስቆጥሮ ሲዳማዎች ጨዋታውን መምራት ችለዋል።

ገና በጊዜ ግብ የተቆጠረባቸዉ ሻሸመኔ ከተማዎች ወደ ጨዋታው ለመመለስ ጥረት ሲያደርጉ በ17ተኛዉ ደቂቃ ላይም አብዱልከሪም ቃሲም ከሳጥኑ ውጭ ድንቅ ሙከራ አድርጎ የነበረ ቢሆንም መክብብ ደገፉ ኳሷን ተቆጣጥሯል። በዚሁ ቅፅበት በመልሶ ማጥቃት ያገኙትን ኳስ ይዘዉ ሳጥን ዉስጥ የደረሱት ሲዳማዎች በማይክል ኪፕሩል አማካኝነት ድንቅ ሙከራ ቢያደርጉም የግቡ ቋሚ ሙከራቸዉን አክሽፎባቸዋል።

ምንም እንኳን በሙከራ ረገድ ደካማ በነበረዉ ጨዋታ በእንቅስቃሴ ረገድ የተሻሉ የነበሩት ሲዳማዎች በመጀመሪያዉ አጋማሽ በአማካዩ በዛብህ መለዮ እና ይስሀቅ አማካኝነት ድንቅ ሙከራዎችን ማድረግ ሲችሉ በአጋማሹ መገባደጃ ወቅትም ሲዳማ ቡና ተጨማሪ ግብ ለማስቆጠር ተቃርበዉ ነበር ፤ በዚህም ሀብታሙ ንጉሴ ይስሀቅ ላይ የሰራዉን ጥፋት ተከትሎ የተገኘዉን ፍፁም ቅጣት ምት አምበሉ ደስታ ደሙ መትቶ የነበረ ቢሆንም ኳሷን የግቡ ቋሚ መልሷታል።

በሙከራ ረገድ ደካማ የሚባል እንቅስቃሴ ካስመለከተን የመጀመሪያው አጋማሽ በይበልጥ በሁለተኛዉ አጋማሽ በአጠቃላይ የጨዋታ እንቅስቃሴ ተቀዛቅዞ እና ለዕይታ ደብዝዞ ይህ ነዉ የሚባል ተጠቃሽ ሙከራ ሁለቱም ክለቦች ሳያደርጉ ጨዋታዉ እንድ ለዜሮ በሆነ ዉጤት በሲዳማ ቡና አሸናፊነት ተጠናቋል።

You Might Also Like

ኢትዮጵያ ቡና የፋይናስ ችግር እንገጠመው ተገለፀ

“ኢትዮዽያ ቡናን ብትነኩ ከመቃብሬ ተነስቼ አጠፉቹሀለው” መቶ አለቃ ፍቃደ ማሞ

ኢንተርናሽናል አርቢትር ማኑኤ ወ/ጻዲቅ ከአዳማ ተሰናበተ

በረከት አማረ ወደ ቀደመ ክለቡ ሊመለስ ይችላል ?

አርባምንጭ ከተማ ሴኔጋላዊ አማካይ አስፈረመ

Share this Article
Facebook Twitter Email Print
By Ermias Misganaw
Follow:
Writer at Hatricksport
Previous Article አማኑኤል ገብረሚካኤል ከውድድር ዓመቱ ውጪ ሆኗል
Next Article የ2016 ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አስራ ዘጠነኛ ሳምንት የዲሲፕሊን ውሳኔ!

Follow US

Find US on Social Medias
127k Like
2.9k Follow
1.6k Follow
19.7k Follow

Weekly Newsletter

Subscribe to our newsletter to get our newest articles instantly!

ተነባቢ ዜናዎች
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግዜናዎችሀዋሳ ከተማሪፖርት

ሪፖርት | ሀይቆቹ ከሜዳቸው ውጪ ከወልዋሎ ጋር ነጥብ ተጋርተዋል

ዳዊት ብርሀነ By ዳዊት ብርሀነ 6 years ago
የጨዋታ ዘገባ | አርባምንጭ ከተማ እና ሲዳማ ቡና ጨዋታቸውን በአቻ ውጤት አጠናቀዋል
የ16ኛ ሳምንት የዲሲፕሊን ውሳኔዎች
“ታገሱን … ለኢትዮጲያ ቡና ብቻ ሳይሆን ለሃገር የሚጠቅም አጨዋወት ይዘን መጥተናል”እንዳለ ደባልቄ/ኢትዮጲያ ቡና/
የ2016 ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አስራ ሁለተኛ ሳምንት የዲሲፕሊን ውሳኔ!
- Advertisement -
Ad imageAd image
Global Coronavirus Cases

Confirmed

0

Death

0

More Information:Covid-19 Statistics
about us

Phone: 0993808668 Email: [email protected] .

Find Us on Socials

© Hatrick Sport 2023 All Rights Reserved.

Removed from reading list

Undo
 

Loading Comments...
 

    Welcome Back!

    Sign in to your account

    Lost your password?