ሉሲዎቹ ነገ ወደ ዩጋንዳ ያመራሉ

የኢትዮጵያ የሴቶች ብሔራዊ ቡድን (ሉሲዎቹ) ለ2022 የአፍሪካ ሴቶች ዋንጫ ለማለፍ የማጣርያ ጨዋታቸዉን ከዩጋንዳ አቻቸዉ ጋር ረቡዕ ዕለት ጥቅምት 10/2014 ዓ.ም በካምፖላ ለማድረግ ነገ ረፋድ ወደ ስፍራዉ እንደሚያቀኑ ታዉቋል።

ከመስከረም 14 ጀምሮ አያት አካባቢ በሚገኘዉ የካፍ የልህቀት ማዕከል ልምምዳቸዉን ሲያደርጉ የሰነበቱት ሉሲዎቹ በዝግጅታቸዉ ወቅትም ሶስት ያህል የአቋም መለኪያ ጨዋታን ያደረጉ ሲሆን ሁሉንም ጨዋታዎቻቸውንም በድል መወጣት ችልዋል።

በዛሬዉ ዕለት ረፋድ ላይ በሀገር ዉስጥ የመጨረሻ ልምምዳቸዉን የሰሩት ሉሲዎቹ ከልምምዳቸዉ አስቀድሞም ከውዳሴ ዲያጎነስቲክ ማዕከል በመጡ የሕክምና ባለሙያዎች የኮቪድ 19 ምርመራ ተደርጎላቸዋል።

የመጀመሪያ የማጣሪያ ጨዋታቸዉን የፊታችን ረብዑ ጥቅምት 8/2014 ካምፓላ ላይ ካደረጉ በኋላም ጥቅምት 18 የመልሱን ጨዋታ በባህርዳር አለም አቀፍ ስታዲየም የሚያደርጉ ይሆናል።

Writer at Hatricksport

Facebook

Ermias Misganaw

Writer at Hatricksport