*….. ከአራት ሚሊዮን ብር ቀላይ ይጠበቅባቸዋል….
“”አሰልጣኙ ድሬዳዋ ያሉት ያለብንን ሂሳብ ለመክፈልና ለማወራረድ እንጂ ተይዘው አይደለም”
አቶ አምበስ መገርሳ
- ማሰታውቂያ -
/ የአዳማ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ/
አዳማ ከተማ ያረፈበትን ሆቴል ትሪያንግል ክፍያ ባለመፈጸሙ ምክንያት የቡድኑ ምክትል አሰልጣኝ አብዲ ቡሊና የክለቡ ሰርቪስ ከሆቴሉ እንዳይወጡ መታገታቸው ተሰማ።
16ቱ የሊጉ ክለቦች በድሬዳዋ ሰባት ጨዋታ አድርገው በቀጣዩ ሳምንት በሀዋሳ ለማቀጥለው 23″ኛው ሳምንት ጨዋታ በሚዘጋጁበት በአሁኑ ወቅት ክለቡ መክፈል የነበረበትን ከ4 ሚሊዮን ብር በላይ በወቅቱ መክፈል ባለመቻሉ የአዳማ ምክትል አሰልጣኝና ሰርቪሱ በሆቴሉ እንዲቆዩ ከከተደረገ ዛሬ አራተኛ ቀን እንደሆነ ከታማኝ ምንጭ የተገኘ መረጃ ያስረዳል።።
መረጃዎች እንደሚገልጹት የሆቴሉ ማናጅመንት ሙሉ ቡድኑን ለማቆየት አስቦ የነበረ ቢሆንም አሰልጣኙ አብዲ ቡሊ አመራርም በመሆናቸው የቡድኑ አባላት እንዳይጉላሉ በሚል ሃላፊነተን ለመውሰድ በመወሰናቸው ሌሎቹ የቡድኑ አባላት ለተቀው ለቀጣዩ የሊጉ ፍልሚያ ሀዋሳ ይገኛሉ።
በጉዳዩ ዙሪያ ምላሻቸውን የሰጡት የክለቡ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ አምበስ መገርሳ ግን መረጃው ውሸት ነው አሰልጣኙ ድሬዳዋ ያሉት ያለብንን ሂሳብ ለመክፈልና ለማወራረድ ነው” ሲሉ አምላሽ ሰጥተዋል። ክለቡም ክፍያውን እንደሚፈጽም በደብዳቤ ማረጋገጫ ለሆቴሉ መስጠቱም ተሰምቷል።
አምናም በተመሳሳይ ሁኔታ በባህርዳር እና በድሬዳዋ ያረፉበት ሆቴል ዋና አሰልጣኙ ይታገሱ እንዳለን የያዘ ሲሆን አሁን ምክትል አሰልጣኙ አብዲ ቡለን በመያዣነት ማቆየቱ አነጋጋሪ ሆኗል።
በአሰልጣኝ ይታገሱ እንዳለ የሚመሩት አዳማዎች ከውስጥም ከውጪም ትልቅ ጫና ቢኖርባቸውም በእስካሁኑ 22 ጨዋታ 34 ነጥብና 4 ግብ ይዘው 6ኛ ደረጃ መገኘታቸው ትልቅ ሙገሳ እያስቻራቸው ነው።