የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ከተጨዋቾች የዝውውር ደንብ ጋር ተያይዞ ለ2017 አዲስ ደንብ ስለሚጸድቅ አሁን እየተደረጉ ያሉ ድርድሮች ለጊዜው እንዲቆሙ ማዘዙ ተሰማ።
የፌዴሬሽኑ የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ በሰጠው ውሳኔ መሰረት ለ2017 ተጨዋቾችን ማዘዋወር የሚቻለው እየተዘጋጀ ያለው የፕሪሚየር ሊግ ክለቦች አዲሱ የክፍያ ስርአት መመሪያ ጸድቆ ተግባራዊ ከሆነ በኋላ በመሆኑ ከወዲሁ እየተደረጉ ያሉ ድርድሮች በነባሩ ደንብ ከሆነ የማይቻልና የማይፈቀድ በመሆኑ የ2017 ድርድሮችን እንዲያቆሙ አሳስቧል።
ከ250 ሚሊዮን ብር በላይ የሚፈስበትን የእግርኳሱ ኢንደስትሪ በተገቢው መንገድ የገንዘብ ፍሰት አይከወንበትም ተብሎ ይታማል። አዲሱ ደንብ የሚፈጥረው ለውጥ ብዙዎች እንዲጠብቁተ አድርጓል።