መነሻ ገጽ ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 11ኛ ሳምንት የዲሲፒሊን ውሳኔዎች
ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 11ኛ ሳምንት የዲሲፒሊን ውሳኔዎች

አጋራ
አጋራ

የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ውድድር አመራርና ስነ-ስርዓት ኮሚቴ ቅዳሜ ዕለት ባደረገው ስብሰባ የተደረጉ ግጥሚያ(ዎችን) ጨምሮ ሌሎች ከዳኞች እና ከታዛቢዎች የቀረቡለትን የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ጨዋታ ሪፖርቶች ከመረመረ በኋላ የተለያዩ ውሳኔዎችን ስጥቷል።

በ አስራ አንደኛው ሳምንት በተካሄዱ የ ቤት ኪንግ ኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ ጨዋታዎች አስራ አራት ጎሎች ከመረብ አርፈዋል ።
የ ኢትዮጵያው ቡናው አቡበከር ናስር በዚህኛው ሳምንት ብቸኛው ሶስት ግቦችን በማስቆጠር ሀትሪክ መስራት የቻለው ተጫዋች ሲሆን የጅማ አባ ጅፋሩ ተመስገን ደረሰ ሁለት ጎሎችን በማስቆጠር ቀዳሚው ተጫዋቾች ናቸው ።

በ አስራ አንደኛው ሳምንት ጨዋታዎች አስራ ስምንት ተጫዋቾች የማስጠንቀቂያ ካርዶችን ሲመለከቱ በድምሩ 280 የቢጫ ካርዶች በሊጉ ላይ ታይተዋል። በ አስራ አንደኛው ሳምንት ጨዋታዎች የቀይ ካርድ የተመለከተ አንድም ተጫዋች ሳይኖር ያለፈበት ሳምንትም ሆኖ አልፏል ።

የዲሲፕሊን ውሳኔ

የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ውድድር አመራርና ስነ-ስርዓት ኮሚቴ ቅዳሜ ጥር 29 2013 ዓ.ም ባደረገው ስብሰባ የተደረጉ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ግጥሚያ(ዎች) ከዳኞች እና ከታዛቢዎች የቀረቡለትን የዲሲፕሊን ሪፖርት ከመረመረ በኋላ

1. አቶ ወንድሙ ብሩ (የሲዳማ ቡና ቡድን መሪ) ቅዳሜ ጥር 22 2013 ዓ ም ክለቡ ከ ቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር ባደረገው የ10ኛ ሳምንት እግር ኳስ ጨዋታ በዕረፍት ሰዓት የዕለቱ ጨዋታ ታዛቢ የተቀመጡበት ቦታ በመምጣት ጨዋታውን በመሩት ዳኞች ዙሪያ አፀያፊ አስተያየት መስጠታቸው በጨዋታው ታዛቢ ሪፖርት ቀርቦባቸዋል። የቡድን መሪው ለፈፀሙት ጥፋት በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ ክፍል 3 ምዕራፍ 3 አንቀፅ 66 በተቁ 1 መሰረት 6/ስድስት/ ጨዋታ እንዲታገዱና በተጨማሪ የገንዘብ ቅጣት ብር 5000 /አምስት ሺ/ እንዲከፍሉ ወስኗል።

የ አስራ ሁለተኛ ሳምንት የ ቤት ኪንግ ኢትዮጰያ ፕርሚየር ሊግ ጨዋታዎች ከመጪው አርብ ሳምንት  ጀምሮ በተጠባቂ መርሀ ግብሮች በ ባህር ዳር አለም አቀፍ ስታዲየም መካሄዳቸውን ይቀጥላሉ ፡፡

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየዲሲፕሊን ውሳኔዎችዲሲፕሊን ውሳኔ

የዲሲፕሊን ውሳኔዎች

ገዛኸኝ ደሳለኝ (ሸገር ከተማ) : ክለቡ ከ ኢትዮጵያ ቡና ጋር ባደረገው የ26ኛ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

የሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና በዝናባማው ጨዋታ በመቻል ሲረታ የጣናው ሞገድም አሸንፏል

እጅግ በከባድ ዝናብ ታጅቦ በተደረገው ጨዋታ መቻል የሊጉን መሪ ሲዳማ ቡናን 3ለ1...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሀድያ ሆሳዕና ፣ ፋሲል ከነማ እና ወላይታ ድቻ ወሳኝ ድል አግኝተዋል

በሊጉ የሳምንቱ የሁለተኛ ቀን መርሀግብር ሀዋሳ ከተማ ወደ ሊጉ መሪ የሚጠጋበትን ዕድል...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ፈረሰኞቹ በድል ሲቀጥሉ ንግድ ባንክ እና ድሬዳዋም አሸንፈዋል

ቅዱስ ጊዮርጊስ ተከታታይ ድሉን ወደ ቋቱ ሲከት ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከጨዋታ ብልጫ...