ፋሲል ከነማ ከዲሲፕሊን ጋር. ተያይዞ የመሃል ሜዳ ኮክቡ ታፈሰ ሰለሞን ላይ ርምጃ ወሰደ።
ክለቡ ለተጨዋቾቹ ለሁለት ቀናት የሰጠውን እረፍት ጨርሰው የተመለሱ ሲሆን ምሽት ላይ ቡድኑ ባረፈበት ሆቴል እራት እየበሉ ታፈሰ ሰክሮ በመግባት ረብሻ ሊፈጥር በመሞከሩና ተጨዋቾቹን በተለይ አሰልጣኝ አሸናፊ በቀለን በጠንካራ ቃላት በመተቸቱ በሃይል ወደ ክፍሉ እንዲገባ መደረጉ ታውቋል።
ክለቡ በብቃቱና በችሎታው አምኖ ቢያስፈርመውም የውጤት ቀውስ ባለበትና የተጨዋቹን ግልጋሎት በሚፈልግበት ወቅት ተጨዋቹ የፈጸመው አላስፈላጊ ድርጊት ክለቡን ማበሳጨቱ ታውቋል።
ተጨዋቹ ቀሪ የአንድ አመት ውል እያለውም ቢሆን በፈጸመው ስነምግባር የጎደለው ድርጊት በመቆጣት ከሆቴል አስወጥቶታል በቀጣይም በይፋ የሚወስደው እርምጃ ይጠበቃል።
- ማሰታውቂያ -
ፋሲል ከነማ በ26ኛ ሳምንት መርሃግብር እስካሁኑ 26 ጨዋታዎች 37 ነጥብና 4 ግብ አምስተኛ ደረጃን ይዟል።