መነሻ ገጽ ሀትሪክ ስፖርትጋዜጣ የእግር ኳሱን መንደር ሲያምሱት የነበሩት አቶ ተኽለወይኒ አሰፋ በአፍ ወለምታ የትግራይ ውክልናን አጡ፤የእሳቸው ውክልና መነሳት ለእግር ኳሱ መንደር ትልቅ ኦፎይታን ፈጥሯል
ሀትሪክ ስፖርትጋዜጣየኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽንጠቅላላ ጉባዔ

የእግር ኳሱን መንደር ሲያምሱት የነበሩት አቶ ተኽለወይኒ አሰፋ በአፍ ወለምታ የትግራይ ውክልናን አጡ፤የእሳቸው ውክልና መነሳት ለእግር ኳሱ መንደር ትልቅ ኦፎይታን ፈጥሯል

አጋራ
አጋራ

ላለፉት አራት አመታት የፌዴሬሽኑ ምክትል ፕሬዘዳንት በመሆን የእግር ኳሱን መንደር ሲያምሱት የነበሩት አቶ ተኽለወይኒ አሰፋ ዛሬ በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ጠቅላላ ጉባኤ ላይ በፍፁም ጨዋነትና ባላቸው ስነምግባር ተለይተው የሚታወቁትን የትግራይ ክልል ሴቶችን የማይገልፅና የማይወክል አሳፋሪ አስተያየት በመስጠታቸው በገጠማቸው የአፍ ወለምታ ለቀጣዩ ምርጫ የትግራይ ክልል የሰጣቸው ውክልናን ተነጥቀዋል።
ዛሬ በተካሄደው ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ስፖርት የማይሽቱ ቃላትን
በመጠቀም የወከላቸውን ክልል ጭምር አንገት ያስደፍት አቶ ተኽለወይኒ ውክልናቸውን ለመነጠቃቸው ምክንያት ከሆነው የትግራይ ክልል ሴቶችን ክብር ከማይመጥነው እሳፋሪ ንግግራቸው ውጪ የተከበሩ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝን ክብር የሚነካ አስተያየት መስጠታቸው ውክልናውን ለመነጠቃቸው ተጨማሪ ምክንያት ተደርጎ ተወስዳል።ላለፉት አራት ዓመታት የእግር ኳሱን መንደር ሲያምሱት የነበሩት አቶ ተኽለወይኒ በዚህ መንገድ ዞር ማለታቸው ትልቅ እፎይታን የፈጠረ ሲሆን የዚህ አይነት ስብዕና ባለቤት ሆነው ኦሎምፒክ ኮሚቴንም በምክትልነት የመምራት ሞራልም የላቸውም የሚሉ እስተያየት ሰጪዎች እየበረከቱ ነው።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ዜናዎችየኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽንየኢትዮጵያ እግርኳስ ዳኞች ማህበርየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

ኢንተርናሽናል አርቢትር ማኑኤ ወ/ጻዲቅ ከአዳማ ተሰናበተ

በኣትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውጤት ለዋጭ ስህተት ሰርቷል የተባለውን ኢንተርናሽናል አርቢትር ማኑኤ ወ/ጻዲቅ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን

አሰልጣኝ ኤርሚያስ በቀለ እግርኳስ ፌዴሬሽኑን ከሰሰ…

አሰልጣኝ ኤርሚያስ በቀለ /ሮማሪዮ/ መብቴን ጥሷል ያለውን የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽንን በመደበኛ ፍርድ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽንየኢትዮጵያ እግርኳስ ዳኞች ማህበርየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

ብሄራዊ  ዳኞች ኮሚቴ ዳኞችን የለየ ውሳኔን አሳልፈዋል

ኢንተርናሽናል አርቢትር ባህሩ ተካን በማሰናበት ኢንተርናሽናል አርቢትር ቴዎድሮስ ምትኩን ባላየ ማለፉ አነጋጋሪ ሆኗል። ብሄራዊ...